የምስራቅ ጉራጌ ዞን ተፈጥሯዊ መስህብ
በምስራቅ ጉራጌ ዞን ተፈጥሯዊ፣ ታሪካዊና ባሀላዊ ተብለው የሚመደቡ በርካታ የቱሪስት መስህብ ዓይነቶች ይገኛሉ፡፡
የአለልቱ ፏፏቴ

በምስራቅ ጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ ጢያ ቀበሌ የሚገኝ የመስህብ ስፍራ ነው።ፏፏቴው ከ100 እስከ 115 ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን ውብና ማራኪ በሆነው አረንጓዴ መልክአ ምድር የተከበበና በዙሪያው በሚገኝው ደን ውስጥ ጉሬዛ እነዲሁም የተለያዩ ቀለም ያላቸው አእዋፋትና ሌሎች የዱር እንስሳት ይገኙበታል።የአለልቱ ፏፏቴ ድባብ በክረምት ወቅት እጅግ የሚያምርና የሚስብ ሲሆን ከአናት ወደ ቁልቁለት እየተጋፋ የሚምዘገዘገው የውሃ ብዛት ውበትና ውሃው ከድንጋይ ጋር ሲጋጭ የሚፈጥረው ጪስ እንዲሁም የአካባቢው የተፈጥሮ ልምላሜ ለፏፏቴው ከወትሮ በተለየ ውበትና ግርማ ሞገስ ያላብሰዋል።
ባጃ ፏፏቴ

በምስራቅ ጉራጌ ዞን መስቃን ወረዳ ምዕራብ መስቃን ቀበሌ ይገኛል።ፏፏቴው ከቡታጅራ ከተማ 10 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን በበጋም ሆነ በክረምት ወቅት የውሃው ፍሰት የማይቀንስ አካባቢው እጅግ ውብና ማራኪ በሆነ መልክአ ምድራዊ አቀማመጥ የታደለ የመስህብ ስፍራ ነው።
ጉሎ ፏፏቴ

]ከወረዳው ዋና ከተማ ቡኢ 25 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ፏፏቴ በግምት ከ50 እስከ 65 ሜትር አካባቢ ካፍታ አለው ፏፏቴው በዙሪያ ውብና ማራኪ በሆነው የአረጓዴ መልዓ ምድር የተከበበ ነው፡፡በፏፏቴው ዙሪያ የሚገኘው ደን ውስጥ ጉሬዛ እና ሌሎች የዱር እንሰሳትና የተለያዩ ቀለማት ያላቸው አዕዋፋት ይገኛሉ፡፡የጉሎ ፏፏቴ ድባብ በክረምት ወቅት እጅግ የሚያምር እና የሚስብ ሲሆን ከአናት ወደ ቁልቁል እየተጋፋ የሚምዘገዘገው የውሃው ብዛት ውበትና ውሃው ከድንጋይ ስጋጭ የሚፈጥረው ነጣ ያለ ጪስ እንዲሁም ዙሪያውን የከበበው የተፈጥሮ ልምላሜ ለፏፏቴው ከወትሮ የተለየ ውበትና ግርማ ሞገስ ያላብሰዋል፡፡
ፋና ፏፏቴ(ፋና ዴራ)

በምስራቅ ጉራጌ ዞን መስቃን ወረዳ በየተቦን ቀበሌ ልዩ ስሙ አሸበብና አበቦት በሚባል ስፍራ የሚገኝ ከ400 አመት በላይ እድሜ ያስቆጠረ ውብና ማራኪ የሆነ ተፈጥሮአዊ መስህብ ነው።
ፏፏቴው ከዞኑ ከተማ ቡታጅራ 15 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን ዙሪያው በበርካታ ተራሮች፣ ደኖች እንዲሁም ወንዞችና ማራኪ በሆነ መልክአ ምድራዊ አቀማመጥ የተከበበ ነው።
ማለሲ/ጎለቲ/ ዋሻ

በምስራቅ ጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ ልዩ ስሙ ፍርሺ በሚባል ቦታ ከቡታጅራ ከተማ 37 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ ይገኛል።ዋሻው ያለምንም ቴክኖሎጂ እገዛ ተጠርበው በተዋቡ ድንጋዮች እንዲሁም ውስጠኛው ክፍሉ በጎጆ ቤት ቅርፅ መሰራቱ ልዩ ያደርገዋል።ማለሲ/ጎለቲ/ ዋሻ ረጅም እድሜ ያስቆጠረ እና ከተራራማ ስር ስለሆነ ከላይ በተለያዩ እፅዋቶች የተሸፈነ ሲሆን በጣሊያን ጦርነት ጊዜ እንደ ልዩ ምሽግ በመጠቀም በርካታ የጠላት ጦር ድባቅ እንደተመታ የአካባቢው እድሜ ጠገብ አባቶች ያስረዳሉ።
የዳዩ አቦ ተራራ
በሶዶ ወረዳ ከሚገኙ ከፍተኛ ተራራማቦታዎች በዋናነት ከሚታወቁትመካከልየዳዮአቦ ተራራና ማራኪ መልከአምድራዊ አቀማመጥ ዋነኛውና ተጠቃሹ ነውይህ ለአይን ማራኪና ውብ ቦታ በአማውቴ ግፍት ጌ ቀበሌ ይገኛል፡፡ የቦታው መገኛ በኮኦርዲኔት # Latitude 8.431/ Notrhing 08º25'52.375" # Elevation abovesealevel3024Mይገኛል።የመስብነትሁኔታማራኪ የመልከአ ምድርአቀማመጥ#ጥንታዊቤክርስቲያን#እድሜ ጠገብ ዛፎች# ምቹና ተስማሚ የአየር ፀባይ# በአመት ሁለት ጊዜ ጥቅምት 5 እና መጋቢት 5 የሚከበሩ የአቦዬ ክብረ በአላት በርካታ ቁጥር ያለው ምዕመናን ይታደማሉ እነዚህ ጉዳዮች የዳዮ አቦ ልዩ መገለጫዎች ናቸው።
