Skip to main content

ምስራቅ ጉራጌ ዞን

                      የምስራቅ ጉራጌ ዞን ታሪካዊ መስህብ 

                            ኢሎል

 የኢሎል ዝግባ ነገስታቶች ይነግስበት የነበረና መካነ መቃብራቸው የሚገኝበት ⵑⵑ

ኢሎል በምስራቅ ጉራጌ ዞን በመስቃን ወረዳ በምዕራብ መስቃን ቀበሌ ከቡታጀራ ከተማ 15 ኪሎ ሜትር ርቆ ይገኛል ፡፡ ዕዚህ ስፍራ ላይ ብዙ ነገስታቶች ነግሰዋል በስፍራው ማንኛው ሰው ሹመት ሲያገኝ ይጠራበት የነበረው ስም በመተው በሹመት ስሙ ይጠራበታል፡፡ በጥቂቱ በአካባቢው የነበሩ ንጉሶች ታሪካቸውን ከብዙው በጥቂቱ ⵑⵑ

ከ14 ተኛው ክፍለ ዘመን በፊት ነው ያ  ማለት ከዛሬ 800 ዓ.ም እዚህ ስፍራ ላይ በባህላዊ አስተዳደር ስርአት በራሱ ህግ አበጅቶ ይተዳደር የነበረው፡፡ታዳ እዚህ ኣካባቢ ሹመትን የሚሰጡበት የራሳቸው የሆነ መስፈርት ነበራቸው ከነዚህም 

1/ በትግል ጎበዝ መሆን አለበት 

2/ በፈረስ ግልቢያ ና

3/ ጦርነት ዘምቶ ጠላትን ድል የነሳ መሆን አለበት ፡፡ 

ከላይ በጠቀስኳቸው መስረት መስፈርቱን የሚያሟላውን የጎሳ (በህር) መሪዎች ተሰብስቦ በመምከር ሹመቱን ይሰጠዋል ፡፡  ንግስናውን ያገኘው ንጉስ በወቅቱ በሚጠራው ጎንደሬ የሚባል የሳር ቀለበት በቀኝ እጁ ይደረግለትና የሚጠራበትን ስም በመተው የንግስና ስሙን ይቀበላል ፡፡ ቀጣዩን የሽማግሌዎቹ ስራ ስለሆነ  ህዝቡን በመሰብሰብ ሶስት ጊዜ ተቀበለነዋል ንጉሳችን ይሑን ብሎ ከመሰከረለት በኋላ ንግስናውን ያገኛል፡፡

በወቅቱ የነበሩት ሹማምንቶች የማዕረግ ስማቸው እንዲህ ነበር የሚጠሩት ⵑⵑⵑⵑ

1/ ድማም በጋሞ 

2/ ጎሽቶ ቀለምሶ

3/ ገራድ ባለከሽ 

4/ ላዝማ ማሬኖ

5/ አዝማ ሳሊሶ 

6/ ሱልጣን 

7/ ኢማም 

8/ አዝማች ሶብሀት እየተባለ ይጠራ ነበር፡፡ አዝማች ሶብሀት ከመምጣታቸው በፊት የዚህ ቦታ የመጀመሪያው መሪ የነበሩት የድማም የዘር ግንድ የነበራቸው ናቸው፡፡ ምክንያቱም ስልጣን በውርስ ይተላለፍ ስለሚተላለፍ የድማም  የዘር ግንድ የነበራቸው ድማም በጋሞ ለረዥም ዘመን እንደመሩ ይነገራል፡፡ ድማም በጋሞ እያስተዳደሩ በነበረበት ወቅት በእርጅና ምክንያት ደክምው ነበር የጎሳ መሪዎች ተሰብስበው  ድማም በጋሞ በወቅቱ በእርጅና ምክንያት በጣም ታመው ነበር። የሳቸው መታመም አይቶ ጠላት እንዳያጠቃቸው ልጃቸውን ጠርተው እንዲህ አሉት ! ልጄ ሆይ! ' 'እኔ ታምሜያለሁ ከዚህ በላይ አቅም የለኝም እኔ የድማም የመጨረሻው እኔ ነኝ ! የመሪነት ቦታው  በኔ ዘር ግንድ  እንዲቀጥል እፈልጋለሁ መሪነቱን ተረከብኝ አሉት' ' ልጃቸውም ታዳ የመለሰላቸው መልስ እንዲህ ነበር ያላቸው። አባቴ ከኔ የተሻለ ብቃት ያለው ሰው  በፈረስ ግልቢያ ጎበዝ የሆነ ፤ በትግል ማንም ሊወዳደረው የማይችል ፤በጦርነት ስልቱ በጣም የተዋጣለት ፤ ጠላትን ከአንድም ሀለት ሶስት ጊዜ በብቃት ድል የነሳ ጎሽቶ ቀለምሶ እሱ ቢሆን ይሻላል አላቸው። ድማም በጋሞ ንግግሩን ሳይቀበሉት ቀሩ ምክንያቱም ለሹመት የታጩት ከሌላ አካባቢ የመጡ ስለነበሩ ነው። ህመማቸው እየበረታባቸው ሄድ። የአካባቢውም ሰው ያለ መሪ መቅረቱ ስጋት ውስጥ ጣለው ። የዚህን ጊዜ ነበር ሁሉም የጎሳ መሪዎች 
ተሰብስበው ከድማም በጋሞ ጋር የመከሩት። አንተ እርጅናም መቶብሀል በዛም ላይ ህመምህ በርትቶብሀል ስልጣንህን ለልጅህ ብትሰጠው ይሻላል ብለው ምክር የሰጡት። ድማም በጋሞ በድጋሚ ለልጁ ይህን ጥያቄ በጎሳ መሪዎች ፊት ይህን ጥያቄ አቀረቡለት። ልጅዬው ግን ያንኑ መልስ ስለመለሰላቸው ።ድማም በጋሞ ጥያቄውን ሳይቀበሉት ቆዩ ። መሀከላቸው ብዙ ግዜ በመሪነት ጉዳይ አለ መግባባት ተከሰተ ። በህዝብ አቁመው ጠየቁት አልተሳካም መጨረሻ በሽማግሌ ተጠይቆ ስልጣኑ ለመጨበጥ ተስማማ በወቅቱ ሽማግሌ(ጉርዝ)  ይከበር ስለነበረ እቢ ብሎ ማለት አሰነዋሪ ስለሆነ እሺ አላቸው። በወቅቱ በነበረው ስርአት ሹመት ለመቀበል ንጉሱ በጠላት ከተሸነፈ አልያም ከሞተ ብቻ ነው ሌላ ተሿሚ የሹመት ስም የሚሰጠው። የድማም በጋሞ ልጃቸው የሹመት ስም ለመቀበል ድማም በጋሞ ከስልጣን መውረድ ነበረባቸው አልያም ደሞ በጠላት መሸነፍ ግድ ስለነበረ ። ድማም በጋሞ ደግሞ ሁለቱንም አልገጠማቸውም ። ለዛም ሲባል የድማም በጋሞ ልጃቸው በሳቸው ስም ለቀጥል የተገደደው።እየቆየ ሲሄድ ግን ህመማቸው በጣም ጠናባቸው ፤እርጅናው ደግሞ ምን መናገር እንዳለባቸው እስከ ማያውቁድረስአደረሳቸው።በመጨረሻም አይቀር የለምና ሞት የሚባለው መጣ ለልጃቸው በስሙ የንግስና ሹመት ሳይሰጡ በህመማቸው ሲሰቃዩ ከርመው ህይወታቸው አለፈ። የድማም በጋሞ ልጅ ብዙን ጊዜ አደን ፤ጦርነት የዘወትር ተግባሩ ነበር ።ለአደንም ይሁን ለጦርነት እየሄደ በጣም ብዙ ይቆይ ነበር  ይቆይ ነበር ።አንድ ቀን ይህ ጀግና ሹመት ሊሰጠው በታሰበ ቀን ጠላት መቶ ማጥቃት ጀመረ ።ውጊያውም  ቀጠለ ሰይፎች ተፍጩ አንገት ላንገት መሞሸላለቅ ወታደሩ ተያያዘው ጦርና ቀስቶች ይወረወራሉ ። ጦርነቱ ልያልቅ ጥቂት ቀረው ሁሉም ወጥረት ላይ ነው ። ሊያሸንፉ ጥቂት በቀራቸው ጊዜ ።በመሀል አንድ ጩኸት ብቅ አለ ። ወደ ዛ! ጩኸት ሰው ሁሉ አተኮረ ጦር ተወርውሮበት በደረቱ ቀዳ በጀርባው  የወጣቺው የድማም በጋሞ ያ! ደፋሩና ቆራጡ መሪ ነበር ። ጦርነቱ ቀድሞውኑ ሊጠናቀቅ የቀረበ የነበረው ቀለመሶ በድል አጀበው።ከድሉ በኋላ ነበሱን ለማትረፍ ቢጣርም ጀግናው ሊተርፍ አልቻለም። በዛ ጦርነት ህወቱ አለፈች ። በዚህ ጊዜ ባጭሩ የተቀጨው የድማም በጋሞ ልጅ በስሙ የንግስና ሹመት ሳያስቀምጥ ህይወቱ አለፈች ። በወቅቱ የነበረው ስርአቱ በሚፈቅደው መልኩ የጀግና የቀብር ስነስርአት ተደረገለት ።ዛሬም ድረስ መቃብሩ በጀግኖች መቃብር ቢዳራ ላይ ይገኛል፡፡

 

የጎይባን ትክል ድንጋይ

ከመዲናችን አዲስ አበባ 139.5 ኪ.ሜ. ከቡታጀራ ከተማ 9.5 ኪሎ ሜትር ርቆ በምስራቅ  ጉራጌ ዞን በመስቃን ወረዳ በጎይባን ቀበሌ ልዩ ስሙ በሸበሬር መንደር በግለሰብ ቤት ይገኛል ፡፡ ይህ ሀውልት የሚያመለክትው የወንድ ልጅ መካነ መቃብር እደሆነና በጀግንነት ከጠላት ጋር እየተፋለመ የተሰዋ መሆኑ ያመላክታል ፡፡ሀውልት በወቅቱ የሚሰራላቸው የንጉሳውያን ቤተሰብ ከሆኑና አልያ ደግሞ የጦር አበጋዞች ሲሆኑ ነው፡፡ የስልጣኔ ማማ ባልነበረበት በዚህ ወቅት ጀግንነተት መለኪያ የሆነው ሀውልትን ቀርፀው ልትውልድ በዚህ መልኩ አስተላፈዋል ፡፡ 

እድሜው ከ800 ዓ.ም በላይ ያስቆጠረ ሀውልትነው፡፡ እጅግ በጣም የቆየና እድሜ ጠገብ ነው ፡፡ በሀውልቱ ላይ ያሉት የኤክስ ምልክቶች በውቅቱ ብዙ ጠላትን ገድሎ እንደ ተሰዋ ያመልክታል ፡፡ በቦታው ብዙ ማህበረሰብ መኖሩንና የማህበረሰቡ ሹም ወይም መሪ እንደነበረው ያሳያል፡፡ ከለውጥ በኋላ መሬት ላራሹ ሲባል ሀውልቱ የሚገኝበት አካባቢ የሰፈሩ ሰዎች ሀውልቱ እንዳይጎዳ አንስተው የቀለም ቅብና የግንባታ ሲራ ሰርተውለት በዚህ መልኩ ይገኛል፡፡