Skip to main content

ስለ ቢሮው

የባህል ቱሪዝም ቢሮ የኋላ ታሪክ

በቀድሞ የደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የባህልና ቱሪዝም ቢሮ እንደነበረ ይታወቃል፡፡ በክልላችን ከተነሳዉ የህዝባዊ ጥያቄ ዉስጥ አንደኛዉ የኤፌድሪ ሕገ-መንግሥት ለብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ባህል፣ ቋንቋና ታሪክ ሕገመንግሥታዊ እውቅና በመስጠት ባህላቸውን፣ ቋንቋቸውን እና ታሪካቸውን እንዲያለሙ፣ እንዲጠብቁና በማንነታቸው እንዲኮሩ፤ እኩል የመልማት ዕድል እንዲያገኙና የዜጎች መሰረታዊ መብቶች እንዲከበሩ ደንግጓል፡፡ በዚህ መነሻነት በ2012 ዓ.ም የሲዳማ ክልል በ2013 የደቡብ ምዕራብ ክልል ከነባሩ ክልል በመዉጣት በክልልነት መደራጀታቸዉ ይታወቃል፡፡

የተቀረዉ የደቡብ ብ/ብ/ህ/ክ/መ በነባሩ መዋቅሮች ይነሱ የነበሩ የአደረጃጀትና ሌሎች የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ምላሽ ለመስጠት በ2015 ዓ.ም የደቡብ ክልል ለብቻዉ ክልልነትን መስርቷል፡፡ የተቀረዉ መዋቅርም የቀድሞዉን አደረጃጀት አሰራሮችን በማሻሻል የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በማለት የክልሉን ህገ-መንግስት በማፅደቅ በ2016 ዓ.ም ተደራጅቷል፡፡ይህንን አደረጃጀት በመከተል የባህልና ቱሪዝም ቢሮ  በክልሉ ውስጥ የሚኖሩ ብሄረሰቦችን ባህል ታሪክና እሴታቸውን የማልማት በሌላ ጎኑ ደግሞ በክልሉ የቱሪዝም እንዱስትሪ በማጎልበት ዜጎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቃሜታ እንዲያገኙ በክልሉ የአስፈፃሚ ተቋማትን ለማቋቋም በወጣው አዋጅ ቁጥር 199/2015 የተቋቋመ የአስፈፃሚ መስሪያ ቤት ነው፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ባህል ቱሪዝም ቢሮ መቀመጫዉን ሳጃ ከተማ በማድረግ ቢሮው በሀገራችን በፍጥነት እያደገ የመጣውን የባህል ልማትና የቱሪዝምዘርፍ በማጎልበት የክልሉን ተፈጥሮአዊ መስህቦች በማልማትና በማስተዋወቅ በክልሉ ገፅታ ግንባታ ዙሪያ ተገቢውን ሚና እየተጫወተ ከመሆኑም ባሻገር የክልሉን ኢኮኖምያዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ክልላዊ እንቅስቃሴ በማገዝ ረገድ የራሱን አስተዋፅኦ እንዲያበረክት ብሎም በክልሉ ውስጥ የሚገኙ ባህላዊ፣ተፈጥሮአዊ፣ሰውሰራሽና ሀይማኖታዊ የቱሪዝም አቅሞችንና ፀጋዎችን በይበልጥ በጥናት በመለየት ጠንካራየማርኬቲንግና የፕሮሞሽን ሥራ ለመሥራትና ለክልሉ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ተገቢውን ድርሻ ለመወጣት ዝግጅቱን በ2016 ዓ.ም አጠናቋል፡፡