Skip to main content

የስልጤ ብሔረሰብ የተፈጥሮ መስህቦች

                                          የስልጤ ብሔረሰብ የተፈጥሮ መስህቦች

የስልጤ ብሔረሰብ ታሪክና ባህል የሚመዘዝባቸው ጥንታዊ መስጊዶች፣ ዋሻዎች፣ ትክል ድንጋዮችና ልዩ ባህላዊና ሀይማኖታዊ ገፅታ ያላቸው ወቅትን ጠብቀው የሚከናወኑ ክንውኖችና ፌስቲቫሎችም ይገኙበታል፡፡ የስልጤ ዞን የሚገኘው በታላቁ ስምጥ ሸለቆ ውስጥና ምዕራባዊ ክንፍ የሚገኝ በመሆኑ የአስደናቂ ሐይቆች፣ ፍልውሃዎች፣ ወንዞችና የተለያየ አይነት መገለጫ ያላቸው ተራሮች ባለቤት እንዲሆን አስችሎታል፡፡ ዞኑ ከሀገሪቱ ዋና ዋና ከተሞች (አዲስ አበባና ሀዋሳ) ከ170-210 ከ.ሜ. ባልበለጠ ርቀትና የኢትዮጰያ ደቡባዊ የቱሪስት መስመር (The South Tourist Route) ከአ.አ-አ/ምንጭ-ጂንካ በተዘረጋው አስፓልት መንገድ ላይ የሚገኝ በመሆኑና የተለያየ ዓይነት ባሕሪይ ባላቸው ቱሪስቶችና ተመራማሪዎች ተመራጭ እንዲሆን አቅም ፈጥሮለታል፡፡

            የተፈጥሮ  መስህቦች 

የተፈጥሮ መስህቦችየሚባሉትየተለያዩኃይቆች፣ፓርኮች፣የዱርእንሰሳቶች፣ተፈጥራዊደኖች፣የዱርእንሰሳትጥብቅክልሎችናየቁጥጥርአደንቀበሌዎች፣ሸለቆዎች፣ ተራሮች፣ተፈጥራዊዋሻዎች፣እሳተጎመራዎች፣ የአፈርአይነቶች፣ፏፏቴዎች፣ፍልዉሃዎች፣ሜዳዎች፣ ሸንተረሮች፣ ወንዞች፣ ባህሮች፣ ዉቅያኖሶች፣ የተለያዩ ብርቂዬ ወፎች፣ ተሳቢዎች፣ የዉሃና የየብስ እንሰሳቶች፣ የተለያዩ አጥቢዎችና የአየር ንብረቶች(ደጋ፣ ወይና ደጋ፣ ቆላ ወዘተ…) ያካትታል።

                                               ሐረ ሸይጣን ሐይቅ

 ሐረ ሸይጣን ሐይቅ በቅበት ከተማ   የሚገኝ ሲሆን የገበቴ ቅርፅ ያለውና ከላይኛው የመሬት ንጣፍ በታች እንዲሁም ከለሩን በየጊዜው የሚቀያይር አስደናቂና በክልሉ ሌላ ቦታ የሌለ ሀይቅ ነው፡፡ አባያ(ጡፋ) ሀይቅ ደግሞ በስልጢና በላንፎሮ ወረዳ የሚገኝ ሲሆን በነፋሻማነቱ ሊሰጥ ከሚችለው ጠቀሜታ ሌላ ለጀልባ መዝናኛ፣ ለአሳ ማስገርና ለኢኮ-ቱሪዝም(ለሎጅ ኢንቨስትመንት) የሚመች ቦታ ነው፡፡ ሐይቁ ውሃን መሰረት አድርገው ለሚኖሩ የዱር እንስሳትና የስምጥ ሸለቆ መለያ የሆኑ አዕዋፍት መገኛም ነው፡፡ በዞኑ ከሚገኙ ታላላቅ ወንዞች ውስጥ ወይራና ዲጆ ወንዞች ዋና ዋናዎቹ ሲሆኑ ወንዞቹ ዞኑን መነሻ አድርገው የብዙ የሐገሪቱን ክፍሎች በተለያየ ስያሜ እየተጠሩ ረጃጅም ጉዞዎችን ይጓዛሉ፡፡ 

 

      

   አባያ/ጡፋ/ ሐይቅ/ Lake Abaya/Tufa

 የአባያ/ጡፋ/ ሐይቅ/ Lake Abaya/Tufa/፡- የሚገኘው በስልጢና በላንፉሮ ወረዳዎች መካከል ሲሆን የውሃ ዋና የሚችልና ነፋሻማ አየርና ሰፊ የውሃ አካል ማየት የሚፈልግ መኪናውን አዘጋጅቶ ከወራቤ በስተ ሰሜን ምስራቅ አቅጣጫ42 ኪ/ሜ ተጉዞ መድረስ ይችላል፡፡ የስልጢ ወረዳ ዋና ከተማ ቅበት ከደረሱ በኃላ 15 ኪ/ሜ  በምስራቅ አቅጣጫ ይርቃል ለጀልባ መዝናኛ ምቹ የአሳ ምርትም ያለዉ ነው፡፡ ሐይቁን የበለጠ ማራኪ የሚደረገው ደግሞ  የስምጥ ሸለቆ መለያ የሆነ አዕዋፋት በብዛት የሚገኙበትም በመሆኑ ነው፡፡ ባለሀብት ከሆኑም ቦታዉን ሲጎበኙ በኢኮ -ቱሪዝም (በሎጅ ኢንቨስትመንት) ለመሰማራት ምኞትናዕቅዱይኖሮታል፡፡

 

              
                        
 
                      ሙጎተራራ/Mugo Mountain/፡-ሙጎ /

ሙጎተራራ/Mugo Mountain/፡-ሙጎ ተራራየሚገኘዉ በምዕ/አዘርነት በርበሬ ወረዳ ከወራቤ 91 ኪ/ሜ ከወልቂጤ-ሆሳዕና በሚወስደው የመኪና መንገድ አጠገብ ሲሆን በዞኑ ሆነ በክልሉ ተጠቃሽ መሆን ያስቻለዉን  የበርካታ ብርቅዬ አእዋፍትና የዱር እንስሳት መገኛ ነው፡፡ ከተራራዉ ስር ደግሞ በርካታ ምንጮች ይፈልቃሉ፡፡ የተራራው ከፍታ 3277 ሜ ከባህር ጠለል በላይ ሲሆን የተራራው ሰንሰለት ወደታች ዝቅ ብሎ ነው የሚገኘው፡፡  አናቱ ላይ ሆነዉ የጉራጌ ፣ የሀድያና የከንባታ ዞኖችና  የስልጤ ዞን መንደሮችን እንዲሁም  ደግሞ ማታማታ የጅማ ከተማን  ያለተጨማሪ መርጃ መሳሪያ ማየት ያስችላል፡፡ በዚህም የተነሳ ይመስላል የጣሊያን ጦር የመመሸጊያና ስትራቴጂክ ቦታ አድርጎ የመረጠው፡፡ ተራራዉና አካባቢዉ በኢትዮጲያ ከሚገኙ 69 አበይት የአዕዋፍ መገኛ ቦታዎች አንዱ እንደሆነ የኢት.ተፈጥሮ ታሪክ ማህበር ጥናት ያረጋግጣል፡፡ የሙጎ ተራራ በአካባቢው አጠራር “ሚዳቻ” የሚባል ሲሆን ትርጉሙም የስልጤ ባህላዊ ምድጃ እንደማለት ነው፡፡ አሰያየሙ በአካባቢው የሚገኙትን ሌሎች አነስተና ከረብቶች መካከል ከፍ ብሎ የሚገኝ በመሆኑ እንደሆነ የአካባቢው ሽማግሌዎች ያስረዳሉ፡፡  እርሶም ተራራዉ አናት ላይ አይንዎ የቻለዉን፣ በተራራዉ ሰንሰለት ላይ ደግሞ አዕዋፋቱንና ዝማሬያቸዉን ይጎብኙ!

             

                        የብሌሌ ቦለት/ቦሌ/Bolet Mineral Soil/


 የብሌሌ ቦለት በስልጢ ወረዳ በአሹ ቡራቆ ቀበሌ ከወራቤ 39 ኪ/ሜ ከቅበት ደግሞ በ12 ኪ/ሜ ርቀት ላይከአሹቴ ፍል ውኃ አጠገብየሚገኝ ሲሆን  ሚንራሉ በብዛት ለከብቶች ምግብነት ለባህላዊ ምግብ(ዙቆ/ መስሪያና ለልብስ ማጠቢያነትያገለግላል፡፡ ሚንራሉ በተለምዶ የብሌሌ ቦለት የሚባል ሲሆን እንደፍልፈል አፈር ማታ ማታ ተከምሮ /በተለይ በክረምት/ የሚያድር ሲሆን በሴቶች ተሰብስቦ ለገበያ ይቀርባል፡፡ ዋጋውም እንደሚመረትበት ቦታ ርቀት ከ10-100 ብር በአንድ ማዳበሪያ ያወጣል፡፡ በአሁኑ ሰዓት በአሹቴ ፍል ውሃና የብሌሌ ቦለትን የአገልግሎት ክፍያ የሚያስከፍሉ የቀበሌው ሴቶች ማህበራት ተጠቃሚ እየሆኑበት ይገኛል፡፡

                                                                     

                           

 

                                         እመዣር ዋሻ/Emejar Cave/

የእመዣርዋሻ/Emejar Cave/፡- በምስ/አዘ/በርበሬ ወረዳ የሚገኝ ሆኖ የጥንት አባቶች አሻራና ጥበብ ይዞ የሚገኝ ዋሻነ ው፡፡ከአ/አበባ—ሆሳዕና—አ/ምንጭበሚወስደውመንገድላይ ከወራቤ ወደ ደቡብ አቅጣጫ የ33ኪ/ሜ ጎዞ በኋላ በስተምዕራብ 4.7 ኪ/ሜትርከወረዳዉ ዋና ከተማቂልጦ ደግሞ በ7 ኪ/ሜትርእመዣከተማ አጠገብ ያገኙታል፡፡ ከጉራቾ ወንዝ በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኘዉ ይሄው ዋሻ በዉስጡ የተለያዩ ክፍሎች /መደቦች/ ያሉት ሲሆን ዋናዉ መግቢያ በርጋር የዘበኞች ቤት፣ አለፍ ሲልም የህጻናትና የባለቤቶች መቀመጫ የነበሩ መደቦችን (ክፍሎች) ያገኛሉ፡፡

በአጠቃላይዋሻዉ ከሁለት መግቢያና መውጫ በሮች በላይ ያሉት ሲሆን አንዱ አሁን ባለው ይዘት ብቻ እንኳየ300 ሜትርውስጥለውስጥጉዞ በኋላ የሚያስወጣሲሆንሌላኛውመውጫገናበጥናት ያልተደረሰበትነው፡፡ጎብኚዎች ዋሻውን በእግር ለማቋረጥ የሚወስኑ ከሆነ የእጅ ባትሪ (ፓዉዛ) እና  የለሊት ወፎችን ጥፊ መቋቋም የሚያስችል መሸፋፈኛ  በነፍስ ወከፍ ዝግጅት ማድረግ ያስፈልጋል፡፡በዋሻዉን አቋርጠዉ ሲወጡ የመደነቅና የጀግንነት ስሜትይሰማዎታል፡፡ ጉብኝት ካለ አይቀር እንዲሁ ነው!

 

 

                        ባልጬተራራ/Balche Chain Mountain/

የባልጬተራራ/Balche Chain Mountain/፡-የሚገኘ ውበ ስልጤ ዞን በዳሎቻና በላንፉሮ ወረዳዎች መካከል ሲሆን ከአራት በላይ ቀበሌዎችንአቋርጦ የሚያልፍ ነው፡፡በዞኑ ከሚታወቁ ትልልቅ ተራሮች አንዱ ሲሆን 1675 ሄ/ርገደማ የሚሸፈንነው፡፡ ሰንሰለታማ ተራራው ታሪካዊ ክስተቶችንም ይዞ የሚገኝነው፡፡የባልጬ ተራራ ለደን ልማትና ለዱር እንሰሳት ጥበቃና እንክብካቤ የተመቻቸ ቦታ ነዉ፡፡ተራራው ሙሉ በሙሉ በተፈጥሮ ደን/ቁጥቋጦ ተሸፍኗል፡፡ በባልጬ ተራራ በርካታ ሀገር በቀል ዛፎችና ቁጥቋጦዎች የሚገኙ  ሲሆን በእፅዋቱ የተጠለሉ የዱር እንስሳዎችና ድንበር ዘለል ወቅታዊና ቋሚ የአዕዋፍ ዝርያዎችም በብዛት ይገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል ከዚህ ቀደም ጂኦተርማል ኢነርጂ በቦታው ሊኖር የሚችልባቸው ምልክቶች መታየታቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ፡፡

 

 

                        ገንቦ ዋሻ/Genbo caves/

ገንቦ ዋሻየሚገኘው በምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ በታች አዳዘር ቀበሌ ከሁልባረግ ወረዳ ድን በርላ ይ ሆኖ ከወረዳው ዋናከተማ በስተሰሜን ምስራቅ አቅጣጫ 13 ኪ/ሜትር ገደማ ላይ ይገኛል፡፡ዋሻውየተሰራውበአንድትልቅቋጥኝላይሲሆንከቋጥኙ ቁመቱ 10ሜትር ከፍታ ሲሆን 3በሮችና2መስኮቶችአሉት፡፡ይህ ቦታ ከየደጎጎ አነስተኛ ሰንሰለታማ ተራራ ላይ ሆነዉ አይንዎን ወደ ታች ቢወረዉሩ አካባቢው በቅድሚያ በቀላሉ ይታይዎታል፡፡ በዚህ ጊዜ ተፈጥሮ ያለ አንዳች የሰዉ ልጅ ማስተካከያና ማሽሞንሞን ለአንድ ትልቅ የመዝናኛ ፓርክና የቱሪስት መስህብነት መዋል የሚችለዉን ቦታ ለመድረስ የሚጓጉት፡፡ ወደ ቦታዉማ ሲጠጉ የተለያዩ ዛፎች መዓዛ፣ የተለያየ ዓይነትና ቅርጽ ያላቸዉ አእዋፋት ዝማሬ እንዲሁም የቆንቆያ ወንዝ ፏፏቴ ድምጽ መታጀብዋ እዉን ሲሆን ረጅም መንገድ አቋርጠዉ ቢሆን እንኳን አእምሮዎ ሀሴትን እንጂ ድካምን የሚያስታዉስበት ጊዜ አይኖረዉም፡፡ ወደ ዋሻዎቹ ሲዘልቁም የጦር ኢላማ መለማመድና ከፍ ወዳሉት ዋሻዎች ለመዝለቅ ይጠቀሙታል፡፡ 

 

 

             አብራኖፋን/ወይራፏፏቴ/Abrano water fall/ 

 

አብራኖፋን /ወይራ ፏፏቴ/Abrano water fall/ ፏፏቴው የሚገኘው በምስራቅ አዘርነት በርበሬወረዳ በታች አዳዘር ቀበሌ ከወረዳው ዋና ከተማ ቂልጦበ ስተ-ምዕራብአቅጣጫከ3 ኪ/ሜባል በለጠ ርቀት ላይ ነው፡፡የ8 ሜትርቁመትናየ2 ሜትርስፋት ገደማ ያለው ይህ ፏፏቴ“አብራኖ” የሚለውን ስያሜያገኘው በድሮጊዜ ባጠፋውጥፋት በፏፏቴው ውስጥ ተወርውሮ እርምጃ ተወስዶበት ከሞተው አብራኖ ከሚባል ልጅ ስም የተወሰደ መሆኑይነገራል፡፡ ከፏፏቴው ስር ባለው ውሃ የሚንሳፈፉ አዕዋፋት ኑና አብረን እንዋኝ የሚሉ ይመስላሉ፡፡ በወይራ ወንዝ ከአብራኖ ፏፏቴ በቅርብ ርቀት ሌሎችም ፏፏቴዎች በብዛት ይገኛሉ፡፡ 

 

 

                       አሹቴ ፍል ውኃ/Ashute Hot spring/

የአሹቴ ፍል ውኃ የሚገኘው በስልጤ ዞን በስልጢ ወረዳ በአሹቴ ቡራቆ ቀበሌ ከወራቤ 39 ኪ/ሜ ከቅበት ደግሞ በ12 ኪ/ሜ ርቀት ላይ ሲሆን የፍል ውኃው ዙሪያ በጣም ለጥ ያለ ስፍራና በዙሪያው የእሳተ ጎመራ ፍንዳታዎች የሚታይበት ነው፡፡ ፍል ውሃው ለተለያዩ በሽታዎች ፈውስነት አገልግሎት እየሰጠ ሲሆን የዉሀዉ መፍለቅ ጥራጥሬ እሸቶችንና እንቁላል ወዲያው ያበስላል፡፡ በፍል ውሃው ለፈውስነት የሚገለገሉ ሰዎች የሚመጡት ከዞኑና በብዛት የሚገኙት ቅዳሜና ዕሮብ ነው፡፡

 

                                      የብሌሌ ቦለት/ቦሌ/Bolet Mineral Soil/

የብሌሌ ቦለት በስልጢ ወረዳ በአሹቴ ቡራቆ ቀበሌ ከወራቤ 39 ኪ/ሜ ከቅበት ደግሞ በ12 ኪ/ሜ ርቀት ላይከአሹቴ ፍል ውኃ አጠገብየሚገኝ ሲሆን  ሚንራሉ በብዛት ለከብቶች ምግብነት፣ ለባህላዊ ምግብ(ዙብቆ/ መስሪያና ለልብስ ማጠቢያነትያገለግላል፡፡ ሚንራሉ በተለምዶ የብሌሌ ቦለት የሚባል ሲሆን እንደፍልፈል አፈር ማታ ማታ ተከምሮ /በተለይ በክረምት/ የሚያድር ሲሆን በሴቶች ተሰብስቦ ለገበያ ይቀርባል፡፡ ዋጋውም እንደሚመረትበት ቦታ ርቀት ከ10-100 ብር በአንድ ማዳበሪያ ያወጣል፡፡ በአሁኑ ሰዓት በአሹቴ ፍል ውሃና የብሌሌ ቦለትን የአገልግሎት ክፍያ የሚያስከፍሉ የቀበሌው ሴቶች ማህበራት ተጠቃሚ እየሆኑበት ይገኛል፡፡

 

 

                     

5 ጊስቲቻ ያረፉባቸው ድንጋዮች/The 5 Ancient Mothers` of Siltie People Sitting Place/

5ቱ ጊስቲቻ ያፎልቡይ ኤት  የሚገኘው በስልጤ ዞን በአልቾ ውሪሮ ወረዳ በቃዋቆቶ ከተማ  ከወራቤ 27 ኪ/ሜ ርቀት ላይ ነው፡፡ ድንጋዮቹ በቁጥር 5 ሲሆኑ ከነ ሐጅ አልዬ ጋር የመጡና የስልጤ ብሔረሰብ ቀደምት እናቶች እንደሆኑ የሚነገርላቸው ሴቶች በቃዋ ቆቶ ከተማ ላይ አረፍ ያሉባቸው ድንጋዮች እንደሆኑ ይነገራል፡፡ ከዚህ ጋር የተያያዙ በርካታ አፈ ታሪኮች ያሉ ሲሆን ለአሁኗ “ቃዋ ቆቶ” ለሚለው ስያሜ መነሻ እንደሆነ የሚነገር ሲሆን እኚሁ ሴቶች አረፍ ባሉበት ጌታቸውን ለምነው አጠገባቸው ላይ ቡና ስለከመረላቸው የከተማውን /የቦታውን ስያሜ “ቃዋ ቆቶ” ትርጉሙም የቡና ክምር /ዳገት ብለው እንደሰየሙት የሀገር ሽማግሌዎች ይናገራሉ፡፡ እኒዘህ እናቶች ጊስቲ ጣሂራት ፣ ጊስቲ መኪያ ፣ ጊስቲ ሙሉካ ፣ ጊስቲ ሸምስያ ና ጊስቲ ዘቡራ ናቸው፡፡ የነዚህ ሴት አያቶች በስማቸው የተሰየሙ መስጊዶች በተለያዩ ቦታዎችይገኛሉ፡፡

 

 

                   ጣንዤና መናኸሪያ ትክል ድንጋዮች/Tanzie and Menaheriya Stelae/

ጣንዤ ትክል ድንጋዮች በስልጤ ዞን ከአሊቾ ዉሪሮ ወረዳ ርዕስ ከተማ ቃዋቆቶ በስተ ምእራብ አቅጣጫ 8ኪ/ሜ ርቀት ላይ በጣንዤ ቀበሌ ልዩ ስሙ ስማኤል በሚባለዉ መንደር የሚገኝ ሲሆን ከጣንዤ ት/ቤት በስተ ደቡብ አቅጣጫ በ0.5 ኪ/ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ትክል ድንጋዮቹ በአንድ ቦታ የተተከሉና ረጅም ዕድሜ እንዳላቸዉ ያያቸዉ ሁሉ ይመሰክራል፡፡ ብዛታቸዉ ሁለት ሆኖ በሞላላ ቅርጽ ተሰርተዉ የበለጠ ልዩና ተደናቂ የሚያደርጋቸዉ ጡት መሰል ነገር ያላቸዉ መሆኑና በጎድን አጥንት መልክ የተጫሩ ጭረቶችም ለምን ታስበዉ እንደተቀረጹ የሚያመራምርና የሚያጠያይቅ ነዉ፡፡ በሌላ በኩል በስልጢ ወረዳ ወደ ወራቤ ከሚወስደው የአስፓልት መንገድ ከ1 ኪ/ሜ ባልበለጠ ገባ ብሎ ቦታ ከመናኸሪያ ከተማ በቅርብ ርቀት የመናኸሪያ ትክል ድንጋይ ይገኛል፡፡ ትክል ድንጋዩ በቁጥር አንድ ብቻ ሲሆን አሠራሩ በሳይንሳዊ አጠራሩ “ፋሊያ ስቴላ” የሚባለው ዓይነት ነው፡፡ 

 

 

      
 
 የጫንጮ ፏፏቴ/የፉርፉሮ ምንጭ/ Chancho Water fall/ Furfuro River Source/

የጫንጮ ፏፏቴ የሚገኘዉ በሁልባረግ ወረዳ ከኬራቴ ከተማ በስተ ምዕራብ አቅጣጫ በ10 ኪ/ሜ ርቀት በብርሀን ክትክታ ቀበሌ "በአይብ ገረን" መንደር ሲሆን የዚህ ፏፏቴ መፈጠሪያ የሆነዉ የፉርፉሮ ምንጭ ነው፡፡ ፉርፉሮ ወንዝ ለሁልባራግና ለሳንኩራ ወረዳ ህዝቦች የመዝናኛ፣ የመስኖ ልማታቸውና ከጠላት መመሸጊያ ምሽጋቸው የሚሆን ሲሆን ለበርካታ የዱር እንስሳትና አዕዋፍት ደግሞ የመኖሪያ ዋስትናቸው በመሆን እያገለገለ ኖሯል፡፡ እየኖረም ነው፡፡ ይህ ምንጭ መነሻዉ ከላይ በተጠቀሰዉ መንደር ከሚገኝ አንድ ትልቅ የግራር ዛፍ ስር ሆኖ ከዚሁ ዛፍ ላይ የሚገኝ ትልቅ ቋጥኝን ሰንጥቆ ወደ ላይ ከሚፍለቀለቅ የተፈጥሮ ዉሃ ነዉ፡፡ የዉሃዉን ትርዒት ልብ ብሎ ለሚመለከተዉ ሰዉ  በአእምሮዉ ላይ ልዩ የሆነ አግራሞትና እርካታን ይጭራል፡፡ የዚህ ምንጭ ዉሃ ወደላይ የማመንጭት ሀይሉ በሰኮንድ 150 ሊትር ነው፡፡ ከዚህ የተፈጥሮ ምንጭ ትንሽ ርቀት እንደተጓዙ ለአይንና ለአእምሮ ማራኪ የሆነዉ የጫንጮ ፏፏቴን ያገኛሉ፡፡ ይህ ፏፏቴ በተፈጥሮ ሞቅ ያለ በመሆኑ ለእግር መቁሰል በሽታ፣ለብርድ ህመም መፈወሻና ለመዝናኛነት አገልግሎት የሚዉል እንደሆነ ይታመናል፡፡

 

 

                                    ጉታና ጉጋቶ ዋሻዎች/Guta & Gugato Caves/

የሚገኙት በሁልባረግ ወረዳ በብርሀን ክትክታ ቀበሌ ልዩ ስሙ ሙርዳል ሲሆን ከኬራቴ ከተማ በስተ ምዕራብ አቅጣጫ 7ኪ.ሜ ርቀት ላይ ሲሆኑ ቁጥራቸዉ በርከት ባሉ በፉርፍሮ ወንዝ ዳርቻ ላይ የሚገኙ ናቸው፡፡ ወደ ዋሻዎቹ ለመዝለቅ ወንዙን በማቋረጥ በመሰላል ተጠቅመዉ መውጣት ግድ ይላል፡፡ ዋሻዎቹ በወንዙ ግድግዳ ከመሬት 7 ሜትር ከፍታ ላይ እንደመስኮት የተሰሩ ሲሆን ዉስጥ ለዉስጥ ከ15 ሜትር በላይውስጥ ለውስጥ የሚያስኬዱና የተለያዩ ሳሎን የሚመስሉ ክፍሎች አሏቸው::  በጥንት ዘመን ዋሻዎቹ ለመኖሪያነት ወይም ለጦርነት ጊዜ መሸሸጊያ  ማህበረሰቡ ይጠቀሙባቸዉ እንደነበር ያካባቢዉ ማህበረሰብ ያስረዳል፡፡ 

 

 

                                                  ብልጬ ሸለቆ/Biliche Valley/

ብልጬ ሸለቆ የሚገኘው በምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳና በምዕራብ አዘርነት በርበሬ ወረዳዎች መካከል ከቂልጦ በ4 ኪ/ሜ ገደማ ሲሆን የሸለቆው ርዝመት ከ1-5 ኪ/ሜ ና የጎን ርዝመቱ በአማካይ 150ሜትር ይሆናል፡፡ የሸለቆው አፈጣጠር በድንገት እንደ ብልጭታ መሆኑን አፈታሪክ የሚያስረዳ ሲሆን ስያሜውን ከዚሁ ነው ያገኘው፡፡ ሸለቆው በውስጡ የተለያዩ የኢግኒየስ ሮክ ዝርያ የሆኑ ድንጋዮች እና ግራና ቀኝ ክፍሉ የመሬትን (የአፈርን) የተለያዩ ክፍሎችና ቀለሞች  የተለያየ ከለር ፍንቱዉ አድርጎ የሚያሳይ ነው፡፡  በሸለቆዉ በአንደኛዉ ዳር በኩል  በተለምዶ ሙሽሮቹ እየተባሉ የሚጠሩና ጃንጥላ የያዘች ሴት የስልጤ ሙሽራ የሚመስሉ የአፈር ቋጥኞች ይገኙበታል፡፡ ለዚህም አፈታሪክ አለው፡፡ በጣም ማራኪና በሸለቆው ውስጥ የተለያየ መጠን ያላቸው ፏፏቴዎች ድምጻቸውን ያስተጋባሉ፡፡ ከሸለቆዉ በሰሜንና በደቡብ አቅጣጫ በረጅሙ የተዘረጋዉ የአዘርነት ሰንሰለታማ ተራራ ሀገር በቀል በሆኑ የአስታና ሌሎች ዛፎች የተሸፈነና በተለያዩ ብርቅዬ የዱር እንስሳት የታጀበ ነዉ፡፡ የሙጎ ተራራ ሰንሰለት እዚህ አካባቢ ነው የሚገኘው፡፡ 

 

 

                       ሀንዶሼ ተፈጥሯዊደን /Handoshe Natural Forest/

ደኑ የሚገኘዉ በሳንኩራ ወረዳ በመንዞ ቀበሌ ዉስጥ የዲጆ ወንዝ ተፋሰስን በመያዝ እስከ ሀላባ ልዩ ወረዳ ድረስ የሚደርስ የተፈጥሮ ሀብታችን ነዉ፡፡ ደኑ ከወረዳው ዋና ከተማ ዓለም ገበያ በ7 ኪ/ሜ ከወራቤ ደግሞ በ47 ኪ/ሜ ርቀት ላይ የሚገኝ ሆኖ በዉስጡ ብዙ አይነት ዝርያ ያላቸዉ የዱር እንስሳት እና አእዋፋት እንዲሁም እድሜ ጠገብ ሀገር በቀል ዛፎችና  የመድሀኒት እጽዋት በዉስጡ አካቶ የያዘ ነዉ፡፡ የሀንዶሼ ደን እየደረሰበት ያለውን ህገ-ወጥ የደን ጭፍጨፋ መከላከልና  በቀጣይነት ማልማት ከተቻለ በፓርክነት ሊያዝ የሚችል ቦታ ከመሆኑም ሌላ የዱር እንስሳትና አዕዋፋትን መጎብኘት ለሚፈልጉ ቱሪስቶች አመቺ ቦታ ነው፡፡ 

 

 

                                    የአጅራ ትኩስየእሳተ ጎመራ /Ajera Active volcanic site/

የአጅራ ትኩስ የእሳተ ገሞራ የሚገኘዉ በስልጢ ወረዳ ከቅበት በ12 ኪ/ሜ ርቀት ላይ በአጅራ ቀበሌ ሲሆን ከ2000 ጀምሮ እስካሁን ድምጽና ሽታ በተቀላቀለበት ሁኔታ እየፈነዳና በኋላም እየተፍለቀለቀ የሚገኝ ተፈጥሮአዊ ክስተት ነው፡፡በቦታው ድምጽ መሰማት የጀመረው የቆየ ቢሆንም ፍንዳታው ለመጀመሪያ ጊዜ  የተከሰተዉ በመኖርያ መንደሮች አካባቢ ባለው ረግረጋማ የግጦሽ መሬት ላይ ከላይ በተገለጸው ጊዜ ነበር፡፡ ፍንዳታዉ በአሁኑ ጊዜ መሬትን በመስመር መልክ የሰነጠቀና የተቃጠለ ዘይት አይነት ሸታ ይዘት ያለዉ ነዉ፡፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጂኦሎጂ ዲፓርትመንት ከፍተኛ ባለሙያዎች በምርምራቸዉ በሂደት ፍል ዉሃ እንደሚሆን ቦታው ድረስ በመገኘት አረጋግጠዋል፡፡ መስህቡ ለጉብኝት በጣም አጓጊ የሆነ ቦታ ነው፡፡

 

                               
   
 

ጋፋት-መጨረፋ ተራራ /Gafat-Mecherefa Chain Mount/

ጋፋት ተራራ የሚገኘዉ በዳሎቻ ከተማ አስተዳደር፣ በሁልባራግ እና በወራቤ ከተማ መካከል ሲሆን የተራራዉ ሰንሰለት ሀዲያ ዞን የሚደርስ ነው፡፡ ተራራው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተፋሰስ ልማት ዘርፍ እየተደረገለት ባለዉ እንክብካቤ የተነሳ ያለዉ የተፈጥሮ ደን ፣ የዱር እንስሳትና የልምላሜዉ ሁኔታ በመሻሻሉና ማራኪነቱን የሚጨምርለት በመሆኑ በቱሪስቶች ለጉብኝት የመመረጥ እድሉ ከፍ ያለ ነዉ፡፡ጋፋት ተራራ በውስጡ ያለዉ ተፈጥሯዊ የመሬት አቀማመጥ ፣ ሀገር በቀል ዛፎችና ብርቅዬ የዱር እንስሳት በቀላሉ ለእይታ ማቅረብ ይቻላል፡፡ በሌላ በኩል ለዳሎቻ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ከፍተኛውን ሚና እየተጫወተ የሚገኘው የመጨረፋ ምንጭ (የቀድሞው ፍል ውሃ) መነሻው ይኸው ተራራ ነው፡፡ በጋፋት ተራራ አናት ላይ አንገትን በማዟዟር የወራቤ ከተማን ጨምሮ በርካታ ትዝብቶችን አይንዎን ራቅና ቀረብ በማድረግ መዝናናት ያስችልዎታል፡፡

 

                                                                            ዘፎ ፏፏቴ/ፋን

    

ይህ ፏፏቴ የሚገኘው በዞናችን ዋና ከተማ በሆነችው ወራቤ አሊቾ በር አካባቢ የጠጠር መንገዱን ይዞ ወደ ምዕራብ አቅጣጫ በሚወስደው መስመር በ2.5 ኪ/ሜ ርቀት ላይ ከመንገዱ በስተቀኝ በኩል 300 ሜትር ገባ ብሎ የአይጦ ወንዝን መገኛው ያደረገው በዞኑ ውስጥ በእርዝመቱ ረጅሙ፣ ማራኪና ታይቶ የማይጠገብ ፏፏቴ ነው፡፡ ይሁንና ከከተማዋ ቢበዛ ከ15-25 ደቂቃ ብቻ የእግር ጉዞ የሚጠይቅ ነው፡፡ ወደ ፏፏቴው ሲጓዙ በግራና በቀኝዎ በኩል ባህላዊ መንደሮችን፣ የእንሰት ተክሎችን የጫት ዛፎችን ውብ የሆነ አቀማመጥ ያላቸውና በመስመር የተተከሉ ረጃጅም ዛፎች፣ ታይተው የማይጠገቡ የተለያዩ የወፍ ዝርያዎች የያዙ ሰፋፊና ትላልቅ ዋርካዎች(ሱብላዎች) እየጎበኙ ወደ ፏፏቴው ይጓዛሉ፡፡ ቀጣይ ወደ ፏፏቴው በቀረቡ ቁጥር በበርካታ የእፅዋት ዓይነት ታጅቦና ተውቦ ነው የሚገኘዉ፡፡ በተለይ በዙሪያው በሚገኘው ጥቅጥቅ ባለ ደን ውስጥ አጥቢዎች፣ ተሳቢዎች እና አዋፋት መቃኘት በሰፊው ይቻላል፡፡ እንዲሁም የአዋፋቱ ዝማሬ ሲንቆረቆርቦት ልዩ አግራሞትና ደስታ ይጭርቦታል፡፡ አካባቢው ለጥናትና ምርምር የሚጋብዝ በመሆኑ  ለጉብኝትና ምርምር ራሶዎን በማዘጋጀት እንቅስቃሴ ወደ ዘፎ ፏፏቴ ይሁን፡፡

 

 

                                                     የቡናር ክሬት/ሸለቆ/

 

የቡናር ሸለቆ የሚገኘው በወራቤ ከተማ  በስተምዕራብ አቅጣጫ 3ኪ/ሜ ርቀት የሚገኝ ሆኖ የሚገኝ ነዉ፡፡ሸለቆው በተፈጥሮው አሰራሩ በጣም የሚያስደንቅና የሚያስገርም ቢሆንም አካባቢውን አዕምሮዎ እስኪላመድ ድረስ በልቦ ፍርሃት ቢጤ ይሰማዎታል፡፡  የሸለቆው አሰራር ተፈጥሯዊ ቢሆንም በሰዉ እጅ የተሰራ እስኪመስ ድረስ አስገራሚ  አሰራር ያለው ነው፡፡ ይህን ሸለቆ ልብ ብለን ስንመለከተው የኮንሶው ኒዮርክ ዓይነት አሰራር ያለው ነው ማት ይቻላል፡፡በሸለቆው በር ገብቶ ወደታች ለመውረድ የቁጥቋጦዎችን እገዛና ድጋፍ ከመጠየቁም በላይ በውስጡ ወይም የታችኛውን ንጣፍ ለመድረስ የ20 ደቂቃ ቆይታ ይጠይቃል፡፡ ሸለቆውን ተፈጥሮ በራሷ ገፀ በረከቶች በማስጌጥ  የስዋበችዉ ሲሆን ከሸለቆው በታችኛው ክፍል ሆኖ ወደ ላይ ሲታይ የመሬቱን ንጣፍ ከሰማዩ ውበት ተዳምሮ ሌላ ዓለም ያሉ መስሎዎ እስኪታዮት ድረስ ውብ ነው፡፡ሸለቆው ከረጅም ዓመታት በፊት ጠባብ፣ጥልቅ ከመሆኑ የተነሳ የጦር ተዋጊዎች እንደ ምሽግ ይጠቀሙበት እንደነበር የአካባቢው ማህበረሰብ በሰፊው ይናገራል፡፡ ይህን ያህል መንገዱን ከመራኖት ለጉብኝቱ መልካም ጉዞ እንላለን! 

 

                               የላሞሬ ጋሮሬፋን/ፏፏቴ/

   የላሞሬ ጋሮሬ ፏፏቴ የሚገኘው በምስ/ስልጢ ወረዳ በበሎ ቀረሶ ቀበሌ ሲሆን ከሀዋሳ በ179 ኪ/ሜ ከአዲስ አበባ ደግሞ በ151 ኪ/ሜ ርቀት የሚገኝ ነዉ፡፡ጋሮሬና ለቦ ወንዞች አማከኝነት የሚፈጠር ፋፋቴ ሲሆን እነዚህ ሁለት ወንዞች   ወደ መገናኛ ቦታው ሲደርሱ በጋራ በአንድ ቦታ ላይ ወደ ቁልቁል በመወርወር አንድ ጉርጓድ ላይ በሚገቡ ወንዞች የሚፈጠር ፏፏቴ ነው፡፡ የዚህ ፏፏቴ ስም ከወንዞች ተቀራራቢ በሆነ ስም ነዉ፡፡ ወንዞቹ  በዚህ ጉድጋድ ዉስጥ መገናኛ ማድረጋቸው አስገራሚና አስደናቂ ያደርጋቸዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም አካባቢው በተፈጥሮ ገፀ በረከቶች የተዋበ በመሆኑ ለጉብኝትና ለአዕምሮ እርካታ በጣም አስፈላጊና አስደሳች ፏፏቴ ነዉ ማለት ይቻላል፡፡ እንዲሁም የአካባቢው አየር ሁኔታ በጣም ተስማሚና ማራኪ በመሆኑ የአይን ምስክርነቶን ለመስጠት በግልዎም ሆነ በሃገርህ እወቅ ስር ይታቀፉ እነላለን፡፡ 

 

 

                                           የወይራወገር ዘራማ (ድልድይ)

የወይራ ወገር ዘራማ በአሊቾ ውሪሮ ወረዳ ውስጥ በሚገኘው በወይራ ወንዝ ላይከአንድ ትልቅ የሃገር በቀል ዛፍ የተሰራ ሆኖ ከስልጤ እናቶች አንዷ በሆኑት አጃማት መኩላ አማካኝት የተጣለ እንደሆነና እድሜውም 600 ዓመት በላይ ያስቆጠረ መሆኑ ይገለፃል፡፡  እስከ አሁን ለአገልግሎት መዋሉና የጊዜ እርዝመቱን ስንመለከት በጣም የሚያስገርም ከመሆኑም በላይ ለጥናትና ምርምር የሚፈልጉ የሃገርና የውጭቱሪስቶች ጥሩ አጋጣሚ የሚፈጥርላቸዉ መስህብ ነው፡፡ ይህ እድሜ ጠገብ እንጨት በጣም አስገራሚ የሆነ ታሪካዊ ክስተት እንደሆነ የማያጠራጥር ሆኖ ቢያንስ ለ9 ትውልዶች አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል ማለት ይቻላል፡፡ እንጨቷ አንድ ወጥ ሆኖ ሰፋ ያለችና መሀል አካባቢ ጉርጉድ ብላ ትገኛለች፡፡ ወገር ዘራማ ከቋቁቶ ከተማ በ16 ኪ/ሜ ርቀት ላይ በስተሰሜን አቅጣጫ ትገኛለች፡፡በመስህቡ ዙሪያ ተፈጥሯዊ፣ ባህላዊና ታሪካዊ መስህቦችንበቀላሉ በአንድ ጀምበር በቅርብ እርቀት ማየት ይቻላል፡፡ሃገርንማወቅ ከአካባቢ ይጀምረል እንላለን!

 

                                    ናዞናበርበሮ /ባህላዊ የቤት ማስዋቢያ የቀለም አፈሮች/

የስልጤ ብሂረሰብ የሚያከናወናቸዉ የራሱ የሆነ በርካታ ታሪካዊ፣ በህላዊ፣ ወግ ፣ልማድ፣የሃዘን፣ የደስታ መገለጫዎችም ሆነ ሌሎች የተላያዩ ክንዋኔዎች አሉት፡፡ለነዚህ ሂደቶችም ማሳያና ማድመቂያ የሚሆኑ ነገሮችን በዙሪያዉ ከሚገኙ ነገሮች ይጠቀማል፡፡ከዚህ አንጻር ሁሉን በዚህ አጭር ፅሁፍ ሁሉንም መጥቀስ ስለማይቻል ለጊዜዉ ትኩረታችንን ‹‹ናዞና በርበሮ›› ላይ እናደርጋለን፡፡ እነዚህ የአፈር ቀለሞችበዞኑ በረካታ ቦታዎች ላይ የሚገኙ ቢሆንም በዋናነት በምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ  ታች ኡምናን ዚድር አካባቢና በስልጢ ወረዳ አልከሶአቅራቢያ ላይ በብዛት ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ሁለት ቀለሞች ከስልጤ ማህበረሰብ ጋር በቀላሉ የማይበጠስ የቅርብ ትስስር አላቸዉ፡፡ይህም ማለት በበዓላት ጊዜ በተለይ በዓረፋ ዋዜማ ህብረተ ሰቡ ቤቱን ለማስዋብና ለማስጌጥ እንዲሁም በበዓሉ መምጣት ደስተኛ መሆኑን ለመግለጽ በእነዚህ ቀለሞች ቤቱን ያስዉቧል፡፡ ከዚህ በተለየ መልኩ አንድ ቤት በበዓል ጊዜ በነዚህ ቀለሞች ካልተቀባ በቤተሰቡ ላይ ችግርና ሃዘን መኖሩን እንደማሳያነትም ያገለግላል፡፡በተለይ የስልጤ ህዝብ የአረፋን በዓል ለየት ባለ ድምቀት ነዉ የሚያከብረዉ፡፡ፋኖዉ ከያለበት የሚንቀሳቀሰዉ ዓረፋ ወር ሲቀረው ሆኖ ሁሉም እንደየ ድረሻዉና አቅሙ ለባዓሉ መድመቅ ዝግጅት ያደርጋል፡፡በሃገርቤት ደረጃ በዓሉን ለማድመቅ ሴቶች ሰፊዉን ድረሻ ይይዛሉ፡፡የበዓሉ ማድመቂያ አንዱና ዋነኛዉ ቤትን በናዞና በርበሮ መስዋብ ነዉ፡፡ይህ የቤት ማስዋቢያ ሁኔታ ብዙ ጥበብ የሚያርፍበት ነዉ ደስታንም አመላካች ነዉ፡፡ይሁንና በቱን በናዞና በርበሮ የመያስዉብ ሰዉ በቤቱ ወይም በቤተ ዘመዱ ላይ የሆነ ሃዘን እንዳለ የሚያሳይ ምልክት አድረጎ ይገለገልበታል፡፡ ይህንያህል ስለቀለሞቹ ባህላዊ ይዘት ካልን ለዘመናዊ ግንባታ የሚያገለግሉ ቀለሞች አንዱ ግኝታቸዉ የነዚሁ የአፈር አይነቶች በመሆናቸዉ ቀለሞቹን መስዋወቅና ጥበቃ መድረግ አስላጊነዉእንላለን፡፡

 

   የሶመኖ ቆቶ/ተራራ/

ይህተራራ የሚገኘዉ በምዕራብ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ከሌራ በስተ ሰሜን አቅጠጫ በ17 ኪ.ሜትር፣ ከሆስዕና 99ከ.ሜትርወልቂጤ ሆሳና በተዘረጋዉ የአፓልትና ፒስታ መንገድ፣ ከባህር ጠለል በላይ እስከ 3000 ሜትር የሚደርስ ሆኖ፣ ከሙጎ ተራራ በስተ ደቡብ ምስረቅ አቅጣጫ ሆኖ ከአ.አበባ -ሆሳና በተዘረጋዉ መንገድ በቅርብ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ይህ መስህብ መንገድ ዳር ላይ መገኘቱ ይበልጥ ለጉብኝት ተመራጭ ይሆናል፡፡ አካባቢዉ በተፈጥሮ ከፍታ የለዉ በመሆኑ በርቀት የተለያዩ ቦታዎችን ማየት ይቻላል፡፡ ወራቤን፤ ሆስዕናን፤ጅማ ከተማንጉራጌ ዞንንና ሌሎችንም አካባቢዎች ጭምር በቀላሉ መቃኘት ይቻላል፡፡ይሁንና የሶመኖ ቆቶ ለየት ያለ ዝርዝርና ረጅም ታሪክ ያለዉ በመሆኑ ለጥናትና ምርምር ፈላጊዎች ጥሩ ግብዓት ነዉ መለት ይቻላል፡፡ በተጨማሪ ለአድቬንቸር ቱር የሚመች በመሆኑ ለጉብኝቱ ይዘጋጁ እንላለን፡፡

 

የዳሃኖና የጋምቤላ ዋሻዎች

የዳሃኖና የጋምቤላታሪካዊዋሻዎች የሚገኙት በሁልባራግ ወረዳ በወራበት ሻማ ቀበሌ ጋምቤላ ተብሎ በሚጠራው መንደር የሚገኙ ሲሆን ከወረዳው ዋና ከተማ ኬራቴ 4 ኪ/ሜትር በስተ ምስራቅ አቅጣጫ ይገኛሉ፡፡እነዚህ ዋሻዎች መነሻቸዉ 1880ቹ ላይ ሲሆን በስልጤ በህላዊ መስተዳደር ላይ የተለያዩ የግዛት መስፋፋት ዘመቻዎችንና ጦርነቶችን ለመከላከል ሲሉ የተቆፈረ ነዉ፡፡በዘመኑ እነዚህ ዋሻዎች ለመሃበረሰቡ ለችግሩም ቀድሞ ደራሾች፤ ለደስታዉ ተጋሪዎች ነበሩ፡፡

 

 

 

 

የጠረጋ ሸለቆና ንፋሱ

የጠረጋ ሸለቆና ንፋሱ የሚገኘው በስልጤ ዞን በአልቾ ውሪሮ ወረዳ ከወራቤ በስተሰሜን አቅጣጫ በጉግሶ ቀበሌ ውስጥ ነው፡፡ የሸለቆውን ርቀት ስንመለከት ከሀዋሳ 243 ኪ/ሜ ከዞን ዋና ከተማ ወራቤ 43 ኪ/ሜ እና ከወረዳው ዋና ከተማ 15 ኪ/ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ይህን መስህብ ከሌሎች ለየት የሚያደርገው ተራሮች አናት ላይ ከፍተኛ የሆነ የንፋስ ኃይል መኖሩና ዓመቱን ሙሉ አረንጓዴ ሆኖ መገኘቱ ነው፡፡ ምናልባትም ጥናት ቢደረግበት ሀገራችን ለተያያዘችው የኃይል ማመንጫ መሆን የሚችል የንፋስ ኃይል ያለው ነው፡፡ ተራሮቹ አናት ላይ ከባድ ንፋስ ስላለ መኖሪያ ቤቶችን ማግኘት ይከብዳል ከዚህም የተነሳ መኖሪያ ቤቶች በሸለቆው ውስጥ ባህላዊ ይዘታቸው ይዘው ይገኛሉ፡፡ በዚህም የተነሳ ነው የአካባቢው ልዩ መጠሪያ ሹሉኬ ተብሎ የሚጠራው በሸለቆው ውስጥ አሞራዎች ይዘወተራሉ የአጥንት ሰበራም ያከናውኑበታል፡፡ ይህንም ልዩ ቦታ አምቦሰባር በመባል ይጠራል፡፡ መስህቡን ለመድረስ በተሽከርካሪ፣ በእንሰሳት ጀርባና በእግር መድረስ ይቻላል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በሸለቆው አካባቢ ቁጭ ብለው ቡታጅራን ከማየትም በተጨማሪ የተለያዩ የተፈጥሮ አጀቦችን መመልከት ይቻላል፡፡

 

የጎላ ኩሬ የጅብ ዋሻ

የንድን ብሄረሰብ ማንነት የሚገልጹ የተለያዩ ሰው ሰራሽ ታንጀብል(የሚዳሰሱናየሚጨበጡ) እና ኢንታንጀብል(የማይዳሰሱ) ቅርሶች ዋነኞቹ ናቸው፡፡ከነዚህም ውስጥየጎላ ኩሬ የጅብ ዋሻን እንመልከት፡-

የሚገኘው በስልጤ ዞን በዳሎቻ ወረዳ በጎላ ኩሬ ቀበሌ በቦዶ ወንዝ አጠገብ ይገኛል፡፡ዋሻው ከወረዳው ዋና ከተማ ዳሎቻ 15 ኪ.ሜ እና ከዞን ዋና ከተማ ወራቤ 29 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ይህ ዋሻ ጣሊያን ሀገራችንን በወረረችበት ጊዜ ራሳቸውን ከጥቃት ለመከላከል ብለው እነደቆፈሩት ታሪክ አዋቂ ሽማግሌዎች ይናገራሉ፡፡ይህን ዋሻ ያስቆፈሩት በጊዜው የነበሩት የስልጤ ጀግኖች እንደ አበጋዝ በርሄ፣ሁሴን ቄዳ፣አበጋዝ ኢመር፣ፌለ ሳቢሮን የመሳሰሉት አበጋዞች እንደሆኑም ታሪክ ይናገራል፡፡

 

                            የወዴሻ ተፈጥሯዊ ደን

የወዴሻ ተፈጥሯዊ ጥቅጥቅ ደን የሚገኘው በስልጤ ዞን በላንፉሮ ወረዳ በሰሶ ቆሻሜ ቀበሌ ሲሆን ወዴሻ ማለት የስልጥኛ ቃል ሲሆን ትርጉሙም ዋንዛ ማለት ነው፡፡ ደኑ ወዴሻ(ዋንዛ) የተባለው ከዚህ በፊት ማለትም ለመጀመሪያ ጊዜ በቦታው 3 ትላልቅ ዋንዛዎች ስለነበሩበት ነው ይላሉ የሀገር ሽማግሌዎች፡፡ የወዴሻ ደን በሰሜን ዳሎቻ ወረዳና ቸበላቴ (ጎጥ) በደቡብ ሳንኩራ ወረዳ፣ በምስራቅ የትንሳኤ ዘርፍ የእርሻ መሬት (ኢንቨስተር) ና በምዕራብ ሳንኩራ ወረዳ ያዋስኑታል፡፡

ከ200 ዓመት በላይ ዕድሜ ያስቆጠሩ የተለያዩ ትላልቅ ዛፎች ዝግባ፣ግራር፣ ቆንጥር፣ ዋርካ፣ ቀጋ፣ አጋም ክትክታ እና ሌሎች የዛፍ አይነቶችና የዱር አራዊቶች የአእዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ፡፡ ወዴሻ ደን ከዲጆ ወንዝ አጠገብ መገኘቱ ወንዙ ለደኑ የተለየ ውበትን በመስጠት ልዩና ማራኪ ያደርገዋል፡፡ በወዴሻ አካባቢ ከጨው በስተቀር ሁሉም አይነት የእህል አይነቶች ጥራጥሬ፣ ፍራፍሬና አትክልት አይነቶች በመብቀሉ 155 ቤት በላይ እንዲፈርሱና ቦታው ለደንና ለኢንቨስትመንት ስራዎች እንዲውል መደረጉን ታሪክ አዋቂ ሽማግሌዎች ይናገራሉ፡፡ በአጠቃላይ እኛ ይህን ያህል ካልንዎት በአካል ሄደው በመጎብኘት ተደስተው፣ ተዝናንተው መንፈሶን ያድሱ፡፡

 

                 ሀቡሌ ተራራ(ቆቶ]

ሀቡሌ ተራራ የሚገኘው በስልጤ ዞን በሁልባረግ ወረዳ አንበሪቾ ጊንባ ቀበሌ ሆኖ ተራራው የሚያልፋቸውን አካባቢዎች ላይኛው ሀቡሌ ታችኛው ሀቡሌ ለከቶ ሷሜ እና ቆዝ ናቸው፡፡ ነገር ግን የተራራው አብዛኛው ክፍል በላይኛው ሀቡሌና በታችኛው ሀቡሌ ይገኛል፡፡ በዚህም የተነሳ ተራራው የሀቡሌ ተራራ በመባል ይታወቃል፡፡ የተራራው ርዝመት 300 ሜትር በላይ ነው፡፡ ተራራው ከተቸኛው ጫፍ እስከ ላይኛው ጫፍ በተለያዩ ሀገር በቀል ዛፎች የተሸፈነ ነው፡፡ በተራራው ላይ የተለያዩ የዱር እንስሳት ጎሽ፣ ዝንጀሮ፣ ጦጣ፣ ሚዳቆ . . . ወዘተ ይገኛሉ፡፡ በድንጋይ ላይ ሶስት ዋሻዎች አሉ፡ ሁለቱ ዋሻዎች በተፈጥሮ በድንጋይ የተሰሩ ሲሆኑ አንዱ ዋሻ ግን በሰው የተቆፈረ ነው፡፡ ታዲያ በተራራው ላይ ሲወጡ የስልጤ ዞን አብዛኛውን ገጽታውን በቀላሉ መመልከት ይችላሉ፡፡ ከኬራቴ ከተማ ትንሽ አለፍ ብለው አምበሪቾ የሚያገኙት በመሆኑና ከመንገድ ዳር ሆኖ ለመዝናናት ምቹ በመሆኑ የሀቡሌ ተራራ ያዝናናዎታል፡፡ ስፍራው ታሪካዊ መሰረትም አለው፡፡

               የተፈጥሮ ድልድይ 

የአላሀ ዘራማ የሚገኘው በስልጤ ዞን በሁልባረግ ወረዳ በወራበት ሻማ ቀበሌ ሆኖ ከወረዳው በ15 ኬ/ሜ ላይ ርቆ ይገኛል፡፡ ድልድዩ በአካባቢው ህብረተሰብ መጠሪያ “የአለሀ ዘራማ ዋ ግንብ” በመባል ይታወቃል፡፡ ስፋቱ 18 ሜትር ገደማ እንደሚሆንይናገራል፡፡ ይህ ድልድይ ለወራበት ሻማ ቀበሌና ለዳሎቻ ወረዳ ህብረተሰብ የአካባቢን ከብት ወደ ግጦሽ ለመውሰድና ውሃ ለማጠጣት እንደ መሸጋገሪያነት በማገልገል ከፍተኛ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ ታዲያ የድልድዩን አሰራርን ስንመለከት ከዘመናዊ ድልድይ አሰራር ምንም የሚተናነስ ነገር የለውም ብንል ማገነን ኤይሆንም የአካባቢ ነዋሪዎች እንደሚናገሩት ድልድዩን የሰሩት ሰዒዱል አረፊን ናቸው ይላሉ፡፡ እኛ ይህን ያህል ካልንዎት እርግጠኞች ነን ጎብኝተው ተደምመውና ተደስተው ይመለሳሉ፡፡ በተመሳሳይ አዘር መረቦ ቀበሌ መዳረሻ በአጫሞ ሳቦላ መንገድ የሚገኝ የአላሀ ዘረማ በሚል የሚታወቅ ተፈጥሯዊ ድልድይ ይገኛል፡፡

 

              የቢላሎ ቆንቄተፈጥሯዊ እስታዲየም

የቢላሎ ቆንቄ የተፈጥሮ እስታዲየም የሚገኘው በምዕራብ አዘርነት በርበሬ ወረዳ በቢላሎ ቀበሌ ልዩ ስሙ ቆንቆ በተባለ ስፍራ ነው፡፡ ይህ ተፈጥሮ መስህብ ከክልላችን መዲና ሀዋሳ 203 ኪሜ ከዞናንችን ወራቤ 93 ኪ.ሜ ከወረዳው ርዕሰ ከተማ ሌራ በስተሰሜን 09 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ የቢላሎ የተፈጥሮ እስታዲየም ቆንቆ ፓርክ በመባልም ይጠራል፡፡ ይህን ስያሜ ሊያገኝ የቻለው በድሮ ጊዜ በስፍራው ቆንቆ የሚባል እሾሃማ አበባ ያለውና የሚበላ ተክል እንደነበረና አሁንም ድረስ በስፍራው መኖሩ ይናገራሉ፡፡ የአካባቢው ታሪክ አዋቂዎች እንደሚናገሩት የእስታዲየሙ የእርከን ስራ የተካሄደው በደርግ መንግስት በ1977 እንደሆነና እርከኑን የሰራው ከትግራይ የመጣና በሀዲያ ዞን ግብርና መምሪያ ይሰሩ የነበረ ኪዳኔ ብርሃኔ የተባለ ግለሰብ እንደነበረ ይናገራሉ፡፡

 

        የአገታ ትክል ድንጋዮች

የአገታ ትክል ድንጋዮች የሚገኙት በስልጤ ዞን አሊቾ ውሪሮ ወረዳ በስተሰሜን ምስራቅ 13 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በአገታ ቀበሌ ልዩ ስሙ ቀቤን በተባለ ቦታ ነው፡፡ ትክል ድንጋቹ በአንድ ቦታ የተተከሉ ሲሆን እረጅም እድሜ እንዳላቸው የሀገር ሽማግሌዎች ያስረዳሉ፡፡ አንዷ አነስ ስትል አንዷ ግን ተለቅ ትላለች ሁለቱንም ግን በሞላላ ቅርጽ የተሰሩ ሲሆኑ በግራኝ አህመድ አማካኝነት ለፈረስ ማሰሪያቸው በአንድ እጃቸው ወርውረው እንደ ተከሏቸው ታሪክ አዋቂ ሽማግሌዎች በአፈ ታሪክ ይናገራሉ፡፡

 

          ይንባብ ቆቶ ፍል ውሃ

የእንባብ ቆቶ ፍል ውሃ የሚገኘው በስልጤ ዞን በስልጢ ወረዳ ሲሆን የእንባብ ቆቶ ፍል ውሃ የተባለበት ምክንያት በድሮ ጊዜ መርዛማ እባቦች እዚያ በሚገኙ ድንጋዮች ስር ይገኙ ስለነበር ነው፡፡ የአካባቢ ሽማግሌዎች እንደሚሉት ከሆነ ሼክ አባሙናጃ የሚባሉ ሰው ቦታው ላይ ፀሎት(ዱዓ) ያደርጉ ነበር፡፡ እንባብ ቆቶ ዳገቱ ላይ ከብት አይገባም ሰዎችም እንጨት ገብተው አይቆርጡም ነበር፡፡ አባሙናጃ ይራገማሉ ብለው ስለሚያምኑ የአካባቢው ሰው አሁንም ድረስ ትዕዛዛቸውን አክብረው ከብት እንደማያስገቡ የአካባቢው ሽማግሌዎች ያስረዳሉ፡፡ በሼክ አባሙናጃ ፀሎት ከዳገቱ ስር የእንባብ ፍል ውሃው የፈለቀው ብለው ያምናሉ፡፡ ሼክ አባሙናጃ በፍል ውሃው ከመታጠባቹ በፊት ዉዱእ እና ጡሀራ ማድረግ አለባችሁ ብለው አዘዋል ይላሉ፡፡ አሁንም ድረስ የአካባቢው ህ/ሰብና ከሌላ አካባቢ የሚመጡ ህመምተኞች በፍል ውሃው በመታጠብና በመጠጣት ፈውስ ያገኛሉ፡፡ 

 

የጉንደ የተፋጥሮኣዊ ድልድይ

የጉንደ የተፋጥሮኣዊ ድልድይ የሚገኘው  በስልጤ ዞን በስልጢ ወረዳ በአጌዳሌ አንሻቤሶ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ውስጥ የሚገኘው ስሆን ከወረዳው ዋና ከተማ ቅበት  በ8 ኪ.ሜ ፣ከዞኑ ዋና ከተማ ወራቤ 22 ኪሜ እና ከሀዋሳ 221 ኪሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ እንደዚያውም ከአድስ አበባ ወደ አርባ-ምንጭ በታዘረጋው የአስፓልት መንገድ ከአልከሶ በስተምራቅ አንድ በኪ/ሜ ላይ በቅርብ ርቀት ይገኛል፡፡ የተፋጥራዊ ድልድይ ስፋቱ ወደ አንድ ሜትር  ነው ፡፡ ምን እሄ ብቻ ውሃ ከስሩ ክብ በሚመስል ቀዳደ ሾልኮ የሚያልፍ ስሆን የክብ ቀዳደው ስፋት  3 ሜትር ነው፡፡ የአካባቢ ሽመግሌዎች እንደምናገሩት የደምገራን ወንዝ ማፍሰስ በቆማች ጊዜ ድልድዩን የተሸከመው እንደ ምሶሶ የቆማ ድንገይ እንደለ ይናገራሉ፡፡ የድልድዩ ጥልቀት 7 ሜትር ያክል ይሆናል ተብሎ ይገመታል፡፡ሰዎ በማነኛውም ጊዜ ያለ ስጋት ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ እንደ መሸጋገሪያነት ይጠቀሙበታል፡፡ 

 

       ቶራ የፀበል/ምንጭ ዉሃ

ይህ የፀበል /ምንጭ/ ዉሃ የሚገኘዉ በቅበት ከተማ አስተዳደር በወሊያ ስድስት ቀበሌ የሚገኝ ሲሆን ከቀበሌዉ በስተምዕራብ በሚገኘዉ ተራራ እምብርት ስር የሚፈልቅ እና ንፁህ ተፈጥሮአዊ የምንጭ ዉሃ ሲሆን ከቅበት ከተማ በ3 ኪ/ሜ በስተፀሀይ መግቢያ ይገኛል፡፡ ይህ የተፈጥሮ የምንጭ ዉሃ ከጥንት ጀምሮ ከኮዞንና  ከተለያዩ አጎራባች አካባቢዎች   ለባህላዊ ህክምናና ለመጠጥ አገልግሎት በመዋልይታወቃል ፡፡የዚህ ባህላዊ መዳኒት አጠቃቀም  ዉሃዉን በመጠጣት ፣ጠጥቶ በማስመለስ እና በዉሃዉ በመታጠብ ነዉ፡፡በስፋት አገልግሎት የሚሰጠዉም ዘወትር ቅዳሜና እሮብ እስከ 4 ሰዓት ነዉ፡፡፡፡በባህላዊ ህክምናነቱ ከስፍራዉ በመምጣት ተፈዉሰዉና ተጠቅመዉ ይሄዳሉ!!

 

 

 

 

 

 

 

 

                             የቆንቃይ ፏፏቴ

 

ይህ ፏፏቴ እጅግ ሊገለጹ የሚያዳግት ታምራቶች አሉት፡፡ ፏፏቴው ማራኪና መንፈስን ሊያድሱ በሚችሉ ተፈጥሮአዊ ደን እና በአእዋፋት ዝማሬ በመታጀብ የተፈጥሮን  አስገራሚ ነት ሚስጥር አድርጎታል  እንደዚሁም ጥቅጥቅ ባለ ደን የተከበበና ወደ ውስጥ  ለመግባት የሚያስቸግር ከገቡም  መውጫውን ለመለየት የሚያዳግት ሲሆን ወረዳው ላይ ካሉት  ፏፏቴዎች የሚበልጥና የተለያዩ የዱር እንስሳቶች በፏፏቴው ዙሪያ ላይ ባለው ደን ውስጥ የሚኖሩ ከመሆኑም  በተጨማሪም የፏፏቴው ድምጽ የተለየ ግርማ ሞገስን አላብሶታል፡፡  የፏፏቴው ርዝመት ወደ ላይ  ከ25 ሜትር  በላይ  ከፍታ ያለው ሲሆን  አመጣጡም በሁለት ደረጃዎች እየተወናጨፈ በመወርወር መሬት ላይ ወዳለው  የገንዳ ውሃላይ ያርፋል ፡፡ የፏፏቴ ውሃዉ የሚያርፍበት ገንዳ ጥልቀቱ እስከ 28 ሜትር ድረስ እንደሚሆንና ከሌሎች ፏፏቴዎች ልዩ ያደረገው በዋሻዎች የታጀበና  የፏፏቴዉ እንፋሎት ነጭና ማራኪ መሆኑ ነዉ፡፡  በተለይ በክረምት መጥተዉ ቢያዩት አስገራሚነቱ ከበጋዉ የላቀ ነዉ፡፡

 

የዦሮዤ ዋሻውችና ምሽጎች       

 

እነዚህ ዋሻዎችና ምሽገውች የሚገኙት በምስ/አዘ//ወረዳ በዶዶ ቀበሌ በአዘኜ ጎጥ ልዩ ስሙ ሉመየር በሚባልበት ቦታ ከወረዳው ከተማ ቂልጦ ዶደ ወደ 500 ሜትር ገደማ ርቆ በምስራቅ  በኩል ዦሮዤ ወንዝ ዳር በሉመያ በር የተፈጥሮ ድን ውስጥ ይገኛል፡፡ ከነዚህ ዋሻዎች  ምሽጎች በቁጥራቸው በርካታ ብሎም ለእይታ ግልፅ ሆነው የሚታዩት 2 በተከታይ ያሉ ወጥ በሆን ድንጋይ ተፈልፍለው የተሰሩ ብዙ የተለያዩ መግቢያና መውጫ እና መስኮት አላቸው፡፡ የውስጥ ስፋታቸው 20 ሜትር ቁመታቸው  ከአንድ  ሜትር በላይ፣ እና  ከመሬት ጠለል ባለይ  20 ሜትር  ርዝመት  አለው፡፡ ለዚህ  ዋሻ መግቢያ የሚሆን ከላይ ከቡብዙ ሜትር ርቀት  ወደ ውስጥ የተወረወሩ የእንጨት ስራስሮች  አሉ እንዚህን ስሮችን በመጠቀም ወደ ውስጥ ገብቶ የሚኖሩ ዝንጀሮዎች ቢኖሩም ወደ ውስጥ ገብቶ ለማየትና ለመጎብኘት አይዳግትም ማለትም ዝንጆሮችም ሰው ወደ ዋሻው እየተጠጋ ሲመጣ  ያለምንም  ተንኮል ወይም ችግር ሳያደርሱ ቦታውን ለቀው ይሂዳሉ፡፡ 

 አከባቢው በተፈጥሮ ደን የተዋበ በደኑ ውስጥ ደግሞ  የተለያዩ  ብርቅዬ የዱር  አራዊቶችና  አእዋፋት  የታጀበ መንፈስን በሚድስ ነፋሻማ አየር የተሞላ፣ በወንዙ የተፈጠሩ ፏፏቴዎች የተከበበና አጠቃላይ ለየትኛውም ጎብኚ  የሚመች አይነት ነው፡፡በተለይም የተሰራበት ወጥ የሆነ  ትልቅ የድንጋይ ቁመትና በመሐል እንዴት እና በምን ቆሞ እንደፈለፈሉት ማንንም በጣም አጀብ የሚያስብል ነው፡፡

 

 

 አሳኖ ትክል ድንጋይ/Asano Stelae/

የአሳኖ ትክል ድንጋይ/Asano Stelae/ ፡-የአሳኖትክልድንጋይበስልጤዞንበስልጢወረዳከዋና ወራ
ቤ በሚወስደው መንገድ 8ኪ/ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ትክል ድንጋዮቹ በቁጥር ከ3 የሚበልጡ ሲሆን
የዋናዉ  ትክል ድንጋይመጠነ-ዙሪያ 1ሜትርናቁመቱ 2 ሜትርይገመታል፡፡የሰውልጅየሰውነትክፍልየሆኑት
ንዓይን፣አፍ፣እጅ፣ጡት፣ደረት፣ሆድየማይነበቡፅሁፎችናየስንቅወይምየጦርመሳሪያ  /መያዣ/ ወዘተ ...
ምስሎች ተቀርጸው የሚገኙበት ነው፡፡ በሌሎቹላይደግሞየመገልገያመሳሪያዎችየሚመስሉ ምስሎችየተቀረጸበ
ትነው፡፡ሌላውከዚሁአካባቢ ተወስዶ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ በክብር በግልጽ ቦታ
ተተክሎ የጥናትና ምርምር አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘው ትክል  ድንጋይ የዚሁ ትክል ድንጋይ አካል
እንደሆነ  አንዳንድ ጥናቶች አረጋግጠዋል፡፡ በጥቅሉ የአሳኖ ትክል ድንጋይ በጥንት  ጊዜ በአካባ
ቢው ላይ ይኖር የነበረውን ማህበረሰብ ስነ-ጥበብ የሚያንፀባርቅ ትክል ድንጋይ ነው ፡፡  ጎብኚዎ
ች ብዙ ሳይቸገሩ ከቅበት ወደ ወራቤ  ጉዞ ላይ አሳኖ ቀበሌ እንደደረሱ በመንገዱ ከ100ሜ ባልበ
ለጠ ጉዞ እነኚህን ድንጋዮች ማየት የሚችሉበት አጋጣሚ በመሆኑ የሰው ዘርንየሥነ-ጥበብ ውጤቶች ቁ
ልጭ                         ባለ ሁኔታ             ተረድተው  ይመለሳሉ፡፡