Skip to main content

የሀላባ ዞን ተፈጥሯዊ

በሀላባ ዞን ተፈጥሯዊ፣ ታሪካዊና ባህላዊ ተብለው የሚመደቡ በርካታ የቱሪስት መስህብ ዓይነቶች ይገኛሉ፡፡

                                                        ባህላዊ

የሀለባ ብሔረሰብ የቆሜ አስራር

Image removed.

የሀላባ ብሔረሰብ የራሱ የሆነ ባህል ፣ታሪክ ቅርስ ያለው ብሄረሰብ ሲሆን ብሄረሰቡ የራሱ የሆነ ቱባ ባህል ከመጠበቅ ከማስተዋወቅም በላይ ለዘመናዊ ቴክኖጂ መሰረት የሚሆኑና ዘመናዊ የህክመና ሳይንስ ከመምጣቱ በፊት በሰዎች ላይ የሚደርሰውን ራሰ በራሃነትን ለመቆጣጠር በሰዎች ላይ ፀሀይና ዝናብ ለመከላከል የሚረዳና የብሄረሰቡን ሆደ ሰፊነትና ሁሉን አቃፊ መሆኑን የሚያስረዳ ባህላዊ ባርኔጣ /ቆሜ/ አዘጋጅተው  በማስተዋወቃቸው ዛሬም ድረስ ከትውልዱን  ትውልድ እየተሸገረ ቆይቷል፡፡

 በዚህች አጭር ርዕስ ለመናገር እና  ለአንባቢያን ግንዛቤ ያህል ለማለት የፈለግነው በሀላባ ብሄረሰብ ልዩ የባህል ተምሳሌት ሆኖ የሚያገለግለውና ከመላው ኢትዮåያ አልፎ በተለያዩ የአለም ክፍሎች  ትኩረት እያገኝ ስላለው የሀላባ ብሄረሰብ ባርኔጣ/ቆሜ/ ትንሽ ቁም ነገር ለማስጨበጥ ነው፡፡

 ቆሜ የሀላባ ብሄረሰብ መገለጫ ሆነው ከሚታወቁት የዕደ ጥበብ ውጤቶች ውስጥ አንዱ ነው፡፡ በሀላባ ብሄረሰብ ዘንድ ቆሜ/ባህላዊ ባርኔጣ/ አሰራር ከጥንት ጀምሮ ከአባቶች ወደ ልጆች ሲወራረስ የመጣ እንድሆነ ይታመናል፡፡የሚሰራውም በአብዛኛው ጊዜ  እረኞች ከብቶቻቸውን ሲጠብቁ ብሄረሰቡ የሚኖርበት አከባቢ በአብዛኛው ደረቅ ወይነ ደጋማ በመሆኑ የፀሀይ ሙቀት በበጋ ወቅት ከብቶቻቸውን ከቦታ ወደ ቦታ እንደልብ ይዞ ለመንቀሳቀስ እንዲመቻቸው የፀሀይ ሙቀትና ዝናብ ለመከላከል ሲሉ የፈጠሩት የፈጠራ ውጤት መሆኑንን የአከባቢ ሹማግሌዎች፣ አዋቂዎችና የብሄረሰቡ ተወላጆች ይናገራሉ፡፡

 አሰራሩም ፡- በቆላና ወይነ ደጋ አከባቢ በሚበቅለው የስንደዶ አክርማ ነው፡፡ ይህ የስንደዶ አክርማ በአብዛኛው አከባቢ የሚበቅለው ከሀምሌ እስከ መስከረም ባለው ወቅት ሲሆን የሚሰበሰበውም በእርጥብነቱ  በእነዚህ ወራቶች ውስጥ ነው፡፡ ይህ የተሰበሰበው የስንደዶ አክርማ በአንድ ላይ ተጠራቅሞ ታስሮ ከቤት ውጪ በጎጆ ቤት ክዳን ላይ ፀሀይ እንዲያገኝና እንዲደርቅ ይደረጋል፡፡ከዚም በመቀጠል የደረቀውን አክርማ በመሰብሰብ በአንድ ላይ በቤት ውስጥ ጣሪ ላይ ይሰቀላል፡፡ ይህ የሚደረገው በአብዛኛው በዞኑ ውስጥ በሚገኙ ቀበሌያት ሲሆን የተረፈው ምርት ለገቢያ ሽያጭነት ጭምር ይውላል፡፡የቆሜ አሰራሩንም በተመለከት እያንዳንዱ የብሄረሰቡ አባል ከእረኝነት ጀምሮ ይስራል ስራውን በሚሰሩበት ወቅት እንደመዝነኛነት በመጠቀም የሚሰሩ ሲሆኑ አሁን አሁን ግን ያለው የገበያ ፍላጎት በመጨመሩ ምክንያ በማህበር በተደራጁ ባሙዎች እየተሰሩ ይገኛሉ፡፡ 

አሰራሩንም በዝርዝር ስንመለከት ቆሜ በመጀመሪያ ደረጃ የስንደዶ አክርማ /ዊጣ/ ይዘጋጃል፡፡የተወሰነ የስንደዶ አክርማ/ዊጣ/በተለያዩ ቀለማት ማለትም አረንጓዴ፣ቀይና ሰማያዊ ቀለማት እንዲዋብ በቀለም ይነከራል ከተነከረ በኋላ፣ይሰነጠቃል የተሰነጠቀው ደግሞ ፣ይገመዳል ገመዱም /ሜርቹ/ይባላል፡፡ ስራው ሲጀመር ቆሜ /ኢንታ/ሲባል ከጅምሩ በኋላ ያለው ደግሞ ቆሜ ሰሙታ ያባላል በመቀጠልም ኮርቦቦ የሚባል ሰያሜ ያለውና በስጨተመጨረሻ ያለው ከፀሀይ የሚከላከለው ክፍል /ቆሜ ጋሩታ/ ሲባል ስፋቱም እሰከ ትክሻ የሚደርስ ሲሆን በጥቅሉ ቆሜ/ባህላዊ ባርኔጣ/ ይባላል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የሀላባ ብሄረሰብ ባህላዊ ባርኔጣ/ቆሜ/ የብሄረሰቡ ባህላዊ ቁስ በመሆን ከማገልገሉ ሌላ በአሁን ሰዓት በብሄረሰቡ ተወላጆች እየሰጠ ያለው የኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ከፍተኛ ነው፡፡በተለይም በዞኑ በርካታ ስራ አጣ ወጣቶች በማህበር ተደራጅተው በቆሜ አስራር እና አመራረት ላይ በማሰማራት በአንድ ጊዜ በርካታ ባርኔጣዎች በማምረት ወደ ገበያ በማቅረብ በአንድ ቆሜ ከብር  ከ500 እስከ 800 ብር ድረስ በመሽጠና ገቢ በማግኝት ኑሯአቸውን እየለውጡ ይገኛሉ፡፡ በዚህም የዞኑ አስተዳደር በቆሜ አስራር በጥራትና በብዛት በማምረት የተጠቃሚውን ህብረተሰብ ፍላጎት ለማርካት መጠነ ሰፊ ስራ እያከናወነ ይገኛል፡፡ባርኔጣው ለአጠቃቀም ምቹ እና በተለይም ከጠራራ ፀሀይ በማስቀራት ሙቀት በመከላከል ጤናን ከማጎልበት ባለፈ በወንፊቱ ክፍል ንፋስ በማስገባት እንደ ቬንትሌተር በማገልገል ራሰበርሃነትን ከሚያስከትሉ ችግሮች በመከላከል አይነተኛ ሚና አለው፡፡

 

ዬዬ ባህላዊ መንደር 

Image removed.

የሀላባ ዞን በርካታ ባህላዊ፣ ታሪካዊ ተፈጥሮአዊ መስህቦች ባለቤት ስትሆን በተለይ የሀላባ ብሄረሰብ የራሱ የሆነ የተለያዩ የባህልና የታሪክ ሀብቶች ያሉት ከመሆኑም ጋር ተያይዞ ልዩ ያደርገዋል፡፡ በባህል ዘርፍ የተለያዩ ያልተነገረላቸው የባህል ሀብቶች ያሉ ቢሆንም በዚህ መረጃ ልናስተዋውቃችሁ የወደድነው ደግሞ የሀላባ ብሄረሰብ ካሉት ከሚዳሰሱ የባህል ሀብቶች ውስጥ አንዱ የሆነውን የዬዬ ባህላዊ መንደር ይሆናል፡፡ የ ባህለዊ መንደር በሀላባ ዞን በአቶቴ ኡሎ ወረዳበዬዬ ቀበሌ የሚገኝ ሲሆን ከዞኑ ዋና ከተማ ቁሊቶ በ 20 ኪ.ሜእንዲሁም ከወረዳው ዋና ከተማ ጉባ በ4 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ የ ባህላዊ መንደር የተለያዩ የብሄረሰቡን ማንነት የሚገልፅ ባህላዊ የቤት መገልገያ ቅርሶችን በውስጡ የያዘ ከመሆኑም በላይ በተለያዩ ባህላዊ የግድግዳ ላይ ስዕሎች መዋቡን ልዩ ያደርገዋል፡፡ የዬዬ ባህላዊ መንደር በቱሪስቶች ዘንድ እንደ ሀገር እውቅና አግኝቶ መጎብኘት ከጀመረ ሰንበትበት ብሏል፡፡ ይህ የባህል መንደር ከሻሸመኔ ሀላባ በሚወስደው ዋናው አስፓልት መንገድ ዳር ላይ መገኘቱ ደግሞ ይበልጥ በውጪና በሀገር ውስጥ ቱሪስቶች ተመራጭ ያደርገዋል፡፡ በሌላ መልኩ የዬዬ ባህለዊ መንደር በአንድ አከባቢ ላይ ተመስርቶ መኖሩ ደግሞ ይበልጥ የብሄረሰቡን  ባህላዊ እሴቶችን  አጉልቶ የሚያሳይ ዬዬ ባህላዊ መንደር መሆኑን ደግሞ ለባህሉ እድገት የሚኖረውን ሚና ከፍተኛ ያደርገዋል፡፡ በመሆኑም ይህንን ባህላዊ ሀብታችንን በመጎብኘትና ለትውልድ እንዲተላለፍ በማድረግ የበኩላችንን ሚና እንወጣ መልክታችን ነው፡፡