Skip to main content

ስልጤ ዞን

            የስልጤ ዞን ታሪካዊ ቦታዎች 

የስልጤ ብሔረሰብ ታሪክና ባህል የሚመዘዝባቸው ጥንታዊ መስጊዶች፣ ዋሻዎች፣ ትክል ድንጋዮችና ልዩ ባህላዊና ሀይማኖታዊ ገፅታ ያላቸው ወቅትን ጠብቀው የሚከናወኑ ክንውኖችና ፌስቲቫሎችም ይገኙበታል፡፡ የስልጤ ዞን የሚገኘው በታላቁ ስምጥ ሸለቆ ውስጥና ምዕራባዊ ክንፍ የሚገኝ በመሆኑ የአስደናቂ ሐይቆች፣ ፍልውሃዎች፣ ወንዞችና የተለያየ አይነት መገለጫ ያላቸው ተራሮች ባለቤት እንዲሆን አስችሎታል፡፡ ዞኑ ከሀገሪቱ ዋና ዋና ከተሞች (አዲስ አበባና ሀዋሳ) ከ170-210 ከ.ሜ. ባልበለጠ ርቀትና የኢትዮጰያ ደቡባዊ የቱሪስት መስመር (The South Tourist Route) ከአ.አ-አ/ምንጭ-ጂንካ በተዘረጋው አስፓልት መንገድ ላይ የሚገኝ በመሆኑና የተለያየ ዓይነት ባሕሪይ ባላቸው ቱሪስቶችና ተመራማሪዎች ተመራጭ እንዲሆን አቅም ፈጥሮለታል፡፡

 

 የጊስቲጣሂራትጥንታዊመስጂድ/Gisti Tahirat  Mosque/


የጊስቲ ጣሂራት ጥንታዊ መስጂድ/Gisti Tahirat Mosque/፡- ከዞኑ ዋና ከተማ ወራቤ በአሊቾ ውሪሮ በኩል ወደ ወልቂጤ በሚወስደው መንገድ 35ኪ/ሜ ርቀት ላይ በአገታ ቀበሌ ልዩ ስሙ ሶጃት ተብሎ በሚጠራ መንደር ከቃዋቆቶ ደግሞ በስተሰሜን ምስራቅ አቅጣጫ በ13 ኪ/ሜ ርቀት ላይ ያገኙታል፡፡ መስጂዱ በጥንት ጊዜ ከምስራቅ አቅጣጫ በመምጣት አካባቢው ላይ ሰፍረው ለዛሬው የስልጤ ብሔረሰብ ጎሳዎች ምንጭ ከሆኑት ታላላቅ ሴት አያቶች መካከል በአንዷ (ጊስት ጣሂራት) አማካይነት እንደተገነባ የሚነገር ሲሆን ከአገታ ተራራ ስር ከሚገኝ አንድ ቋጥኝ ተቦርቡሮ የተሰራ ነው፡፡ መስጂዱ ከ500 ዓመታት በላይ ዕድሜ እንዳለው የሚነገርለት የድንጋይ ፍልፍል መስጂድ ነው፡፡ መስጂዱ እሰካለበት  ለመድረስ በሀገር በቀል ቁጥቋጦዎች የተሸፈነዉን የአገታ ተራራ እየተንፋቀቁ በታላቅ ጀግንነትና የጎብኚነት ስሜት መውረድን ይጠይቃል፡፡አድቬንቸርቱር ይላል እንዲህ ነዉ!

 

                የሀጅአልዬና  የገን ስልጤ  መስጂዶች/HajiAliye&Gen Siltie Mosques/

 የሀጅ አልዬ መስጂድ የሚገኘው በምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ በታች ዑምናን ቀበሌ ከወራቤ በስተ ምዕራብ አቅጣጫ 54 ኪ/ሜ ርቀት ላይ ነው፡፡ ሀጅ አሊዬ ከስልጤ ቀደምት አባቶች መካከል በመሪነት ከመጡት አንዱ ሲሆኑ  የአብዛኛዉ የስልጤ ብሄረሰብ የዘር ሀረግ የሚመዘዝባቸዉ አባት እንደሆኑ የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ፡፡ ሃጂ አልዬ መጀመሪያ ያረፉትም ሆነ መጨረሻ የሞቱት እዚሁ አካባቢ መሆኑን ታሪክ አዋቂ ሽማግሌዎች ያስረዳሉ፡፡ከመስጂዱ ቅጥር ጊቢ ውስጥ በሃጅ አልዬ ጊዜ የሰላት ጥሪ አድራጊ /ሙአዚን/ የሚቆምበት ታሪካዊ ድንጋይ በመኖሩና በመደዳ የተደረደሩት ከውዱዕ በኋላ ለመረማመጃነት ያገለግሉ የነበሩ ድንጋዮች መገኘታቸዉ የቀድሞዉን ታሪካዊና ጥበባዊ ቅርሶች ለመመልከትና ብዙ ዓመታትን ወደኃላ ለማስታወስ እድል ይሰጣል፡፡ በልዩ ኪነ ህንጻ የተሰራው መካነ መቃብርም ሌላዉ ቅርስ ሆኖ መስጊዱ አጠገብ ይገኛል፡፡ የገን ስልጤ መስጂድም በአልቾ ውሪሮ ወረዳ ከኩተሬ ከተማ በስተሰሜን ምስራቅ አቅጣጫበ7 ኪ/ሜ ገደማ የሚገኝ ሲሆን መታሰቢያነቱ ለበርካታ የስልጤ ብሔረሰብ ጎሳዎች አባት ለሆኑት ገን ስልጤ የተሰራ በመሆኑ ከሐጅ አልዬ መስጊድ ጋር ተያይዞ በቅርስነቱ ይጠቀሳል፡፡

 

                   ዞናል የስልጤ የባህል ሙዚየም

የዞኑ በህል ሙዚየም  የሚገኛዉ በወራቤ ከተማ 02 ቀበሌ ዱና መንደር ሲሆን  የዞኑን ህዝብ ታሪካዊ፣በህላዊና ተፈጥራዊ ቅርሶችን/መስህቦችን/ በአንድ ማዕከል አቅፎ የያዘ ነዉ፡፡የስልጤ መህበረሰብ ራሱን የቻለ በህል፣ወግና ታሪክ  ያለዉ ህዝብ በመሆኑ ረሰብ በመሆኑ ሙዚያሙን ለጉብኝት ስራ እንዲዉል ተደርጋል፡፡ሙዚያሙ በዉስጡ አካቶ የያዛቸዉ ሃብቶች የስልጤ ህዝብ ከጥንት ጀምሮ ይጋላጋልባቸዉ የነበሩ ቅርሶን ሲሆን በየ አካበቢዉ ተበትነዉ ለመጎብኛት ምቹ ያልነበሩ ሃብችንና የስልጤ ህዝብ ኑሮዉን ለመሻሻል የተጠቀመባቸዉን የመገልገያ ቁሳቁሶች በአነንድ መዕከል ለጉብኝት እንዲመቹና ቅርሶቹ ጠፍተዉ እንዳይቀሩ ለማድራግ መሆኑ፡፡ሙዚያሙ በርካታ በህላዊ፣ታሪካዊና ሌሎችንም ቅርሶች በዉስጡ አጭቆ የያዘ ሙዚያሙን ዉስጡ ገብተዉ ሲጎበኙት የጥንቱን ማህበረሰብ ጥበብ፣አሻራና ስልጣኔ ምንደረጃ ላይ ደርሶ የነበረ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል፡፡ለዕያንዳንዱ አገልግሎት ይጠቀሙበት የነበረዉ የራሳቸዉ ጥረት በማከል ሃገር በቀል መሳሪያዎችን ና ዕዉቀቶችን መረዳት መሆናቸዉ ይቻላል፡፡ሙዚያሙ ያተሰራዉ በተለይ የዉስጥ አሰራሩ በበህላዊ ቤት አይነት ሲሆን ለስልጤ ቀደምት እናቶች መታሰቢያ ተደርጎ በጎንናጎን 5 የበህል ቤቶችን በስንደዶ የተከደኑ ሆነዉ ተሰርተዋል፡፡የስልጤ በህል ወግ፣በህላዊ የቤት አሰራር ይአዘትን ለማወቅ ከፈለጉ የጊዜ ብክነት ሳይፈጥር ስልጤ ማሃበረሰብ ያለፈበቸዉን መንገዶች በቀላሉ ማወቅ ይቻላል፡፡

 

                   የአልከሶመስጂድ/Alkeso Mosque/

የአልከሶመስጂድየሚገኘዉ በስልጤዞን በወራቤ ከተማ አስተዳደር በስተሰሜን አቅጣጫ 8ኪ/ሜ ርቀት ላይ ነው፡፡  2ኛከተማ አልከሶ ደግሞ በ3.8 ኪ/ሜትርርቀትላይ ገባ ብሎ ይገኛል፡፡ ከስልጤ ቀደምት ሀይማኖታዊ መሪዎች አንዱ ለሆኑት አልከስዬ መታሰቢያነት የተገነባ ጥንታዊና የብሔረሰቡን ስነ-ግንባታ ፍልስፍና /Architectural Design / የሚያንፀባርቅ ይዘት ያለው መስጂድ ሲሆን በየአመቱ የረመዳን ፆም ከመግባቱ 15 ቀን ቀደም ብሎ የሚዘጋጀውና በርካታ ባህላዊ ስነ-ስርዓቶችን የሚያካትተው መውሊድ ይስተናገድበታል፡፡ በ2004 የ105ኛው የአልከሶ መውሊድ በዓል ይከበራል፡፡ የአልከሶ መስጂድ በአሰራሩም ሆነ ባለው ታሪካዊ ባህላዊና ሀይማኖታዊ ገፅታ ታዋቂነትን ያተረፈ ጥንታዊ መስጂድ ነው፡፡ መስጂዱ የተሰራበት 3ሜ መጠነ ዙሪያ ያለዉ ምሰሶ  ከረጅም ርቀት በሰው ጉልበት ተጎትቶ መምጣቱና  ከምሰሶው የሚነሱ ወጋግራዎች ውስጡን ገብቶ የሚጎበኝ ሰዉ ሳይደነቅባቸዉ ከማይወጣባቸው ቅርሶች ውስጥ ተጠቃሾች ናቸው፡፡ መስጂዱን ለመጎብኘት ሲመጡ በመስጂዱ አስጎብኚዎች የሚነገሩ በርካታ አስገራሚ አፈታሪኮችና ገጠመኞች ይኖራሉ፡፡ የስልጤ ብሄረሰብን የሥነ-ጽሁፍና ሥነ-ጥበብ ሂደትም በውስጡ ይዟቸው በሚገኙ ባህላዊየመጻፊያ መሳሪያዎችና የሥነ-ጥበብ ዘዬዎች ማገናዘብ ይችላሉ፡፡

 

                  የኢማም ሱጋቶ ፎቅ /Imam Sugato Villa House/

የስልጤ ብሔረሰብ በታሪኩ ካለፋቸው የአስተዳደር እርከኖች ውስጥ ኢማም ሱጋቶ ዘይኔ ስልጤንና አካባቢውን “ጎጎት” በሚባል አንድነት በማሰባሰብ ያስተዳደረበት ጊዜ ይገኝበታል፡፡ ይህ ጊዜ ከ90 ዓመት በፊት ሲሆን በጊዜው ለመሪው መኖሪያና የአስተዳደሩ ማዕከል እንዲሆን ታስቦ የኢማም ሱጋቶ ፎቅ በአከባቢው በሚገኙ ማቴሪያሎች /በሀበሻ ጽድና በቀረከሃ/ የተሰራ ነው፡፡ ፎቁ ሲሆን በብዙ መልኩ ከጅማ አባጅፋር ቤተ-መንግስት ጋር ይመሳሰላል፡፡ ቤቱም ሲሰራ ከጅማ አባጅፋር እንደተጋገዙ በስፋት ይነገራል፡፡ ፎቁን ለማየት የሚፈልግ ከስልጤ ዞን ዋና ከተማ ወራቤ 83 ኪ/ሜ ተጉዞ የምዕራብ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ዋና ከተማ ሌራ ከደረሰ በኋላ 5 ኪ.ሜ ብቻ በተሸከርካሪ አሊያም በእግር ዱና ቀበሌ መጓዝ ብቻ ይጠይቃል፡፡ እርግጠኞች ነን ጎብኝተው ተደምመውና ተደስተው ይመለሳሉ፡፡ ፎቁ ባለአንድ ደረጃ ሲሆን 3 በሮችና 3 መስኮቶች አሉት፡፡ በአሁኑ ሰዓትም በኢማሙ ቤተ-ዘመዶች እንክብካቤ እየተደረገለት ይገኛል፡፡

 

                     ዳንጌመስጂድ/Dange Historical Mosque/

የዳንጌመስጂድ/DangeHistoricalMosque/ የዳንጌመስጂድየሚገኘውበዳሎቻወረዳበዳንጌ መተያ ቀበሌ ከዳሎቻ ከተማ 7ኪ/ሜ ርቀት ላይ ነው፡፡ መስጂዱ ከ100 አመት በላይ ዕድሜ ያለዉ ሲሆን በዉስጡ በእጅ የተጻፉ የእምነት ጉዳዮችን የሚያብራሩ መጽሀፎችና ሌሎች ባህላዊ የሐይማኖት ትምህርት መማሪያ ማቴሪያሎች ይገኙበታል፡፡ የዳንጌ ሸህ ታዋቂ ምሁር የነበሩ ሲሆን ጎለጫባ ሼህንና ደማለ ሼህን ጨምሮ ባጠቃላይ ከ250 በላይ ደረሶች በዚህ በዳንጌ ሼህ ተምረው (ቀርተው) ለአሁኑ የስልጤ ብሔረሰብ ሀይማኖት መሠረት እንደሆኑ ይነገራል፡፡የዳንጌ ሼህ መስጂድ በዞናችን ለመጀመሪያ ግዜ ጁምዓ መሰገድ የተጀመረበት እንደሆነም ይነገራል፡፡ የዳንጌ ሼህ መስጂድ እንደተቋም የእምነቱን ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ማህበራዊ አለመግባባቶችም የሚፈቱበት እንደሆነ በስፋት ይነገራል፡፡ ከተለያዩ ቦታዎች ለሚመጡ የእስልምና ዕምነት ትምህርት  ፈላጊዎች ስኮላርሺፕ በመስጠትም ይታወቃል፡፡ በአሁኑ ሰዓት መስጂዱን የሼሁ የሚያስተዳድሩት የልጅ ልጃቸው ናቸው፡፡

 

 

                የዚኮ ሼህ መስጂድ /Ziko Sheikh Mosque/

የሚገኘዉ በሳንኩራ ወረዳ በአደሻ ዚኮ ቀበሌ ዉስጥ ሲሆን በአለም ገበያ ከተማ ዳር   በ7ኪ.ሜ ርቀት ላይ ነው፡፡ የዚኮ ሼህ መስጂድ ታሪካዊና ጥንታዊ መስጂድ ሲሆን በዉስጡ ከ1120 ዓመት ዕድሜ  በላይ ያስቆጠረ በአሁኑ ሰዓት በስልጤ ባህል ሙዚየም የሚገ ከአንድ እንጨት ተፈልፍሎ የተሰራ ባህላዊ ሳጥን ያበረከተ ነው፡፡ በተጨማሪም ጥንታዊ የእጅ ጽሁፎች በግቢዉ ዉስጥ የሚያማምሩ ሀገር በቀል ዛፎች የሚገኙበት መስጂድ ነ፡፡ ጥንታዊ የእስልምና ሃይማኖት ማዕከል በመሆን እንዳገለገለ የሚነገርለት ሲሆን የሃይማኖቱ ተከታዮች ከጉራጌ፣ ከሀላባና ከጅማበመመላለስ ይማማሩበት እንደነበር ይነገራል፡፡

 

              ሸበርከሌ መስጂድ/Sheberkele Mosque/

የሚገኘዉ በአሊቾ ዉሪሮ ወረዳ በአገታ ቀበሌ ዉስጥ ሲሆን ከወራቤ 49 ኪ.ሜ እና ከቃዋቆቶ 22 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ነው፡፡ መስጂዱ  ከጉራጌ ዞን መስቃን ወረዳ ድንበር አካባቢ የሚገኝና ከሰማይ ሚፎካከር በሚመስል ተራራ ስር ነዉ  የሚገኘው፡፡ ሸበርከሌ መስጂድ ከሌሎች የሚለየዉ ስልጤ ዞን ከመጡት አምስት ቅድመ አያቶች መካከል  በአንዱ የተመሠረተና ሙሉ በሙሉ ከድንጋይ ፍልፍል የተሰራ የዋሻ ውስጥ መስጂድ መሆኑ ነዉ፡፡ ወደ መስጂዱ ለመድረስ ረጅሙን ተራራ መሃል ለመሃል ሸለቆዉንና ሸንተረሩን በታላቅ ድፍረትና ቆራጥነት በእግር ማቋረጥን ይጠይቃል፡፡ በመስጂዱ አከባቢ እንደጊስት ጣሂራት መስጂድ ፣ ጠረጋ ሸለቆና ማራኪ የተፈጥሮ የመሬት አቀማመጦች አካበውት ይገኛሉ፡፡በዛ ጭው ባለውና ግራና ቀኝ በማይታይበት ሸለቆ ውስጥ ቤት ንብረት አፍርተው የሚኖሩ ሰዎች አኗኗር ደግሞ ከምንም በላይ አስገራሚ ሆኖ ይታያል፡፡

 

 

              የሶርጋን መስጂድ/Sorgan Mosque/

የሚገኘዉ በአሊቾ ውሪሮ ወረዳ በዉሾ ቀበሌ ከወረዳዉ ዋና ከተማ ቃቆቶ በስተ-ምዕራብ አቅጣጫ በ12 /ሜ ርቀት ዳገት ተጠግቶ ፡፡ ከዕድሜው መርዘም የተነሳ በዘመናዊ ማቴሪያሎች እንደገና ፈርሶ የተሰራ ሲሆን ታሪካዊነቱ ከስልጤ ቀደምት ሴት አያቶች (ከ5ቲ ጊስቲቸ) አንዷ ከሆነችው ከአጃሞቴ መኩላ የተያያዘ መሆኑ ነው፡፡ በመስጂዱ ውስጥ ባለረጅም ዕድሜ ባህላዊ የመገልገያ ቁሳቁሶች የሚገኙ ሲሆን ወቅትን ጠብቆ ባህላዊ የህዝብ መሰባሰቢያ ስነ-ስርዓቶች መውሊድ ይካሄዱበታል፡፡ በሌላ በኩል መስጂዱን ተገን በማድረግ የሚኖሩ ልዩ ልዩ የዱር እንስሳት  አዕዋፋትም ይገኙበታል፡፡

 

 

 

 

 

 

የአንፋር የአሞራ አጥንት ሰበራ ትርዒት

    ይህ ቦታ የሚገኘው በም/አ/በርበሬ ወረዳ በአንፋር ቀበሌ አንዘጎጄ ተብሎ በሚታወቀው ስፍራ ከሌራ በ12 ኪ/ሜ ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን የአሞራ አጥንት ሰበራ ትርዒት የሚደረገው በተለይ እርድ በሚፈፀምበት በኣረፋና በመስቀል ወቅት በሰፊዉ ሆኖ ትርዒቱ በህብረት በመሆን የከብት ቅልጥም አጥንት ካገኙበት ቦታ አምጥቶ አየር ላይ ሲለቁት እየተምዘገዘገ ወርዶ በሙጎ ተራራ አካባቢ በሚገኘው አምዘ ጎጂ የድንጋይ ቋጥኝ ላይ እንዲሰበር ያደርጉታል፡፡ ካልተሰበረም ምልልሱን በመደጋገም ሆኖ እስኪሰበር በመቀጠል ሲሰበር መቅኒ(አምቦ) ለመመገብ መሆኑ ነው፡፡ 

 

                     

 

                        የኢማም ሲዴ መካነ መቃብር

 ኢማም ሲዴከስልጤ ቀደምት አባቶች አንዱ እንደሆኑ በአፈ ታሪክ በሰፊው እየተነገረነው፡፡የስልጤ፣ የአላባና ቀቤና ህዝቦች የጋራ አባት መሆናቸውን በሁሉም በኩል ከመናገሩም በላይ እነዚህ ብሄረሰቦች የሀዲያ ሱልጣኔት አባል የነበሩ ከመሆኑም በላይ ሰፊ ታሪክ የላቸዉ ናቸው፡፡ይሁንና የኢማም ሲዴ መካነ መቃብር ስልጤ ውስጥ ምዕ/አ/በርበሬ 

በግምት ከሌራ 8 ኪ/ሜ ርቀት ላይ ደን ጋወር ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ከአንድ ትልቅ ዋርካ ስር የሚገኝ ሆኖ ብዙ ታሪክ ፀሐፊዎች በተለይ ተክለ ፃዲቅ መኩሪያ በሰፊው እንደገለፅው የአፄ ዩሀንስን ጦር ዋቤ ወንዝ ላይ ገጥመው ድል ያደረጉ ሰው መሆናቸውን የግራኝ አህመድ በሚለው የታሪክ መፃሀፋቸው ላይ አስቀምጠውታል፡፡በአፈ ታሪክ እንደሚነገረው ኢማም ሲዴ የሀጂ አልዬ ወንድም የነበሩ መሆኑን ይነገራል፡፡ ይሁንና መቃብራቸው ከ500 ዓመት እድሜ በላይ እንዳስቆጠረ በመሃበረሰቡ በሰፊዉ ይነገራል፡፡ይሁንና ይህ ቦታ ለገብኚዎች/ ለታሪክ ተመራማሪዎች ወሳኝ ቦታ ነዉ፡፡

 

 

 

         

   

                     የዋርካ ውስጥ ፎቅ

የዋርካ ውስጥ ፎቅ የሚገኘው በስልጤ ዞን በስልጢ ወረዳ በሳዳ በራንጎ ቀበሌ ከአባያ ሀይቅ በስተ ደቡብ ጫፍ ላይ ነው፡፡የተሰረውም በ1969አመት አካባቢ በአቶ ሀሚድ በተባሉ ግለሰብ ነው፡፡ፎቁ ተፈጥሯዊና ታሪካዊ ይዘት የለው ነው፡፡ዋርካው በሶስት ደረጃ ተከፍሎ(ጂ+2)ነው፡፡ የፎቆችን ሁኔታ ስንመለከት የመጀመሪያው ክፍል ፈረስን ማስቆም ሚችል ስፋት ሲኖረውየመጀመሪያው ፎቅ ሰውዬው የሚቀመጥበትና 15 ሰዎችን ሚይዝ ሲሆን የመጨረሻው ፎቅ 5ሰዎችን የመያዝ አቅም አለው፡፡በመጀመሪያ አካባቢ በዋርካው መጨረሻ ክፍል(ፎቅ)ላይ ዘንዶዎች ይኖሩበት እንደነበረ የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ፡፡በጊዜ ሂደት ግን ቦታውን ለቀው ሄደዋል፡፡የዋርካው ርቀት ከሀዋሳ 190 ኪ.ሜ፣ከዞን ዋና ከተማ ወራቤ 42 ኪ.ሜ እና ከወረዳው ዋና ከተማ ቅበት15 ኪ.ሜ ርቀት ላይይገኛል፡፡በስህቡንም ለመድረስ ተሸከርካሪ፣የቤት እንሰሳት እና እግር መጠቀም ይቻላል፡፡መስህቡን ከሌሎች ለየት የሚየደርገው ፎቆቹ የተሰሩት በሚበቅልዛፍ መሆኑና አሁንም ድረስ ፎቁን የሚንከባከበው ግለሰብ ጭምር  መኖሩ ነው፡፡

 

 

 

 

 

 

                   ታሪካዊ የኬራቴ ገደል

ታሪካዊ የኬራቴ ገደል የሚገኘው በስልጤ ዞን በስልጢ ወረዳ ከወራቤ በስተሰሜን-ምስራቅ  ቅበት ከተማ ውስጥ ነው፡፡ይህ ገደል የተቆፈረው በቀደምት የስልጤ የጦር አበጋዝ በነበሩት አዝማ ጤሮ ነው፡፡ለዚህም ገደል መቆፈር ምክኒያቱ በዚያን ጊዜ ስልጤና ማረቆዎች በተለየዩ ጥቅማጥቅሞች የተነሳ እርስበርስ ግጭት ነበራቸው፡፡በዚህም የተነሳ ማረቆዎች በደረሱት ድንገተኛወረራ የአዝማ ጤሮን ልጅ ጨምሮ ብዙ የስልጤ ተወላጆችን ገድሎ ከብቶችን በመማረክ እና ቤቶችን በማቃጠል ከፍተኛ ጉዳት አደረሱ፡፡አዝማ ጤሮም የአጸፋ እርምጃ በመውሰድ የልጃቸውን አስክሬን ከማስመለስም በላይ ብዙ ማረቆዎቸዎን በመግደለና በመማረክ ተመለሱ፡፡በዚህ መካከል ሁለቱም ላይ ከፍተኛ ጉዳት በመድረሱ ጦር የማቆም ስምምነት ደረሱ፡፡ነገር ግን አዝማ ጤሮ የልጃቸው መሞትና የደረሰባቸው ጉዳት ስላብከነከናቸው አንድም የስልጤ ተወላጅ ሳይሞት ማረቆዎችን የሚበቀሉበትን ስልት ነደፉ፡፡ለዚህም ሁነኛ ዘዴው ገደል ቆፍሮ ሳር ማልበስ ሆኖ አገኙት፡፡በዘህም የተነሳ የኬራቴን ገደል ስፋቱን ሰንጋ ፈረስ በማይዘለው ሁኔታ ቁመቱ 18 ሜትር ርዝመቱ 1.5 ኪ.ሜ ያህል ለ9ኝ ወር የፈጀ ገደል በምስጥር ወንዶች በመቆፈር ሴቶች አፈር በማውጣት አጠናቀው ገደሉን ሙሉ በሙሉ በሸንቦቆና በሳር በመሸፈን የጦር ማቆም ስምምነቱን ማፍረሳቸውን ለማረቆዎች መልክት ሰደዱ፡፡ማረቆዎችም በመናደድድንገተኛ ወረራ እንደ ሚያካሄዱ በመገንዘብ አዝማ ጤሮ ጦረቸውን ገደሉ አካባቢ በማስፈር ማረቆዎች ሲመጡ የፈሩ በመምሰል ሲሸሹ ማረቆዎች ፈረሰኞች በሙሉ ሸንቦቆና ሳር በለበሰው ገደል በመግባት ከማለቃቸውም በተጨማሪ የተቀሩት መሬት ተሰንጥቃ ዋጠችን በማለት የየዙትን ነገር በሙሉ በመጣል ነብሴ አውጪኝ በማለት ሀገራቸውን ተመልሰው ለስልጤዎች ትልቅ ድል ሆኖ ተመዝግቦዋል፡፡

 

 

               የሀድር ሼህ መስጂድ

የሀድር ሼህ መስጂድ የሚገኘው በስጤ ዞን በአሊቾ ውሪሮ ወረዳ በፈቻሌ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ውስጥ ሲሆን ከወረዳው ዋና ከተማ በሰሜን ምስራቅ ዋናውን መንገድ ይዞ በቅርብ ርቀት ይገኛል፡፡የሀድር ሼህ መስጅድ የተሰራው በአፄ ሚኒሊክ ዘመን በሼህ ስራጅ አህመድ ራሀሜነበር ይሁንና ሁለት ጊዜ ባልታወቀ ምክንያት ቃጠሎ የደረሰበት ሲሆን በምትኩ አሁን የሚገኘውን መስጂድ ጣሊያን ኢትዮጵያ ከመግባቱ በፊት 1920 አካባቢ የሀድር ሼህ ይህን መስጂድ ሲገነቡ በድጋሚ ቃጠሎ እንዳይደርስበት በሚል ሙሉ በሙሉ ከፅድ እንጨት ከጉራጌ ዞን ሙህር ከሚባል ቦታ በማምጣትናየቦለት(የቦሌ) አፈር መርገው እንደከደኑት የሀገር ሽማግሌዎች ይገልፃሉ፡፡ የሀድር ሼህ በአካባቢው ህ/ሰብ ከፍተኛ ተወዳጅነትና ተሰሚነት የነበራቸው ሲሆኑ የዕስልምና ሀይማኖት ያስተማሩና እስካሁንም ድረስ በእጅ የተፃፉት ኪታቦች በዚሁ ስራቸው ህያው ምስክር ሆነው ይገኛሉ፡፡ እኛ ይህን ያህል ካልንዎት እርስዎመጥተው ምስክርነትዎን ይስጡ!!

 

            

                  ገባባ ቤተዕምነቶች

የገባባ ቤተክርስቲያን የሚገኘው በስልጤ ዞን በላንፉሮ ወረዳ ሲሆን ታሪካዊና ሃይማኖታዊ የመስህብ ስፍራ ነው የተመሰረተው ከዛሬ አንድ መቶ አርባ ስድስት ዓመት በፊት መሆኑን የአካባቢው ሽማግሌዎችና የሃይማኖት መሪ አባቶች ይናገራሉ፡፡ በውስጡ የተለያዩ በብራና የተፃፉ እድሜ ጠገብ የፀሎት መጹሃፍት መኖራቸውንም ይነገራል፡፡ ቦታው ከደቡብ ክልል መዲና ሀዋሳ በ219 ኪ.ሜ፣ በስልጤ ዞን ዋና ከተማ ወራቤ በ51 ኪ.ሜ እና የወረዳው ዋና ከተማ ከሆነችው ጦራ በ19 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኘው ይህ ስፍራ በሰንሰለታማ ተራራ ላይ የሚገኝ የጡፋ አባያ ሀይቅ በቅርብ ርቀት ይገኛል፡፡ ምንም እንኳን ቤተክርስቲያኗ የምትገኘው በላንፉሮ ወረዳ ቢሆንም በወረዳው ካሉት የክርስትና እምነት ተከታዮች በተለያዩ ክብረ በዓላት ጊዜ ወደ ስፍራው ይጓዛሉ፡፡

 

              

 

               የከሊሙላ መስጂድ

የከሊሙላ መስጂድ የሚገኘዉ በስልጤ ዞን ላንፍሮ ወረዳ በገባባ ቀበሌ ሲሆን ከሀዋሳ 215 ኪ/ሜ ከወራቤ 55 ኪ/ሜ ከወረዳው ዋና ከተማ ጦራ 15 ኪ/ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ከሊሙላ ማለት የሰዉ ስም ሲሆን የዘር ሀረጉም በአካባቢው ህ/ሰብ ዘንድ በጣም ታዋቂና የማህዲ ልጅ ማለትም የአልከስዬ የልጅ ልጅ ናቸው፡፡ መስጂዱ አመታዊ መውሊድናበየወሩ ሀሙስ ሀሙስ(ዩሪከምስ) መውሊድ ይከበርበታል፡፡ከተለያዩ ቦታዎች በመጡ ሰዎች በታላቅ ስነ-ስርዓት ይከበራል፡፡ዓመታዊ መውሊድ ከመከበሩ ከ3.4 ወራት ዝግጅት ተጀምሮ በታላቅ ድምቀት ዕሁድ ቀን ማታ በተለያዩ ዝህረ(ዜማዎች ተከብሮ ማክሰኞ የሽኝት ቀን(የስልስ ዓያም) በመባል በድምቀት ይከበርና የመውሊድ ስነ-ስርዓቱ ያበቃል፡፡

 

             የወራቤ ስፔሻላይዝድ ኮምፕርሄንሲቭ ሆስፒታል

የወራቤ ስፔሻላይዝድ ኮምፕርሄንሲቭ ሆስፒታል ለአይን በሚስብ መልኩ በ14 ሄ/ር ቦታ ላይ ያረፈ ሲሆን የእንግዳ መቀቢያዎች (guest house) 11 ትልልቅ (ባለፎቅ) ህንፃዎች/ብሎኮች/፣ መደበኛ የሆኑ ብቻ 584 አልጋዎች እንዲሁም በ2ኛ የግንባታ ምዕራፍ የነርሶች ማሰልጠኛኮሌጅይኖረዋል፡፡ የወራቤ እስፔሻላይዝድ ኮምፕርሄንሲቭ ሆስፒታል በርካታ ክፍሎችን የያዘ ሲሆን 3 ዓይነት ፋርማሲዎችንም በውስጡ ይዟል፡፡ የመጀመሪያው ፋርማሲ እንደማንኛውም ሆስፒታል መደበኛ ፋርማሲ ሲሆን 2ኛው ደግሞ ትልቅና እንደከነማ ፋርማሲዎች ሆኖ የሚያገለግል ነው፡፡ 3ኛው ፋርማሲ ደግሞ በስልጤ ልማት ማህበር የሚደጎምና ከውጪ የሚገቡና በአካባቢው በቀላሉ የማይገኙ መድሀኒቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ የሚያቀርብ ነው፡፡ሆስፒታሉ የተጎዱ ታካሚዎችና መደበኛ /ተመላላሽ/ ታካሚዎች የሚገቡባቸው የተለያዩ መግቢያ በሮች አሉት፡፡ ከዚህም ሌላ የኤሌክትሮኒክስና የኬሚስትሪ የሚባሉ 2 ላብራቶሪዎች ያሉት ሲሆን ቀዶ ጥገና ክፍሉ በአንድ ጊዜ 4 ሰው ማስተናገድ ይችላል፡፡ ኢንቴንሲቭ ኬር ዩኒት/ICU/ የሚባለው 72 ክፍሎች ያሉት ሲሆን በድምሩ 694 ዘመናዊ የታካሚ መኝታ ክፍሎችን ይዟል፡፡ ክፍሎቹ ግድግዳ ላይ ኦክስጂን የሚያቀርቡ መሳሪያዎች የተገጠሙለት ሲሆን አካል ጉዳተኞችን በቀላሉ የሚያስተናግድ መሆኑም ልዩ ያደርገዋል፡፡ ይህ ሆስፒታል በህዝብ ተሳትፎ በስልጤ ልማት ማህበር አስተባባሪነት የተገነባ እጅግ ዘመናዊና የህዝብ አሻራ ያረፈበት ብቻም ሳይሆን በሀገራችን health tourism(የጤና ቱሪዝምን) ለማስፋፋት አስተዋጽኦ የጎላ እንደሚሆን የሚጠበቅ ሆስፒታል ነው፡፡ ለመጎብኘት የሚመጡ እንግዶች በርካታ መሆናቸው የጤና ቱሪዝም ዘርፉን ተቋሙ የሚያካትት መሆኑን አመላካች ነው

 

 

                 ታሪካዊዋ የኮምበል ዛፍ

የሚገኘው በስልጤ ዞን በምዕራብ አዘርነት በርበሬ ወረዳ በሌራ ከተማ  ውስጥ የሚገኝ ስሆን  ከአድስ አበባ -ሆሳና በተዘርጋው  የአሰፓልት መንገድ በስተ ምስራቅ 50 ሜትር ወደ ውስጥ ገባ ተብሎ ነው፡፡ ከዞኑ ዋና ከተማ ወራቤ 85 ኪሜ እና ከሀዋሳ 285 ኪሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ በዚህች ዛፍ በስር እማም ሱጋቶ በተለያዩ ጊዜ የተለያዩ ስብሰባዎችን  ለማካሄድ ይጠቀምባት እንደነበረ የሀገር ሽማግሌዎች ይናገራሉ፡፡ ማለትም  ከሀዲያ እና ጉራጌ ጋር  ጦርነት ስለነበረው የስልጤን ማህበረሰብ ጦርነት ከሚያመጣው የህይወት መጥፋት ና የንብረት መውደም አሰቀድሞ ለመከላከል እና ከዚህም በተጨማሪ ጦነቱን በድል ለመወጣት መሃበረሰቡ በስሩዋ አልፎ አለፎ በመሰብሰብ የተለያዩ አዋጆችንና መመሪያዎችን የስተላልፍበት እንደነበረ የታሪክ አዋቂዎች የስረዳሉ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ሌራ ተብለ የሚትጠራዋ ከተማ  በድሮ ጊዜ ከምበል ታብለ ኢንደምትጠራ የአካባቢው ማህ/ሰ  ይናገራሉ ፡፡

 

                   

 

                       የአጋዎ  ሼክ መስጅድ

የአጋዎ ሼክ መስጅድ የሚገኛው በስልጤ ዞን በላንፉሮ ወረዳ ስሶ ቆሻሜ ቀበሌ ስሆን ለያት በለው ስሙ የሚታዋቀው አገዎ ተብሎ በሚጠራው መንደር ውስጥ ነው፡፡ከወራቤ ከተማ 80 ኪ/ሜ  ርቀት ከወረዳዋ ዋና ከተማ ጦራ 37 ኪ/ሜ፣ ከሚቶከተማ 14 ኪ/ሜ ርቀት ና ከጦንባቴ ከተማ 1ኪ/ሜ ላይ በቅርብ ርቀት ይገኛል ፡፡ አገዎ ማለት የቦታ ስም  ስሆን ሼክ ማለት በእስልምነ እምነት የቁርኣን እውቀት ያለው ሰው መሆኑንን ለመግለጽ የሚጠቀሙበት ቃል ነው፡፡ ፡፡የአካባቢው ሽመግሌዎች እንደሚነገሩት የአገዎ  ሼክ መስጅድ የተመሰረተው 150 ዓመት ይሆነል ተብሎ ይታሳበል፡፡ይህ  ታርካዊ መስጅድ የውስጥ ስፈቱ 15 ሜትር ነው፡፡ የአገዎ ሼክ መስጅድ ከሌለው ለያት የሚያደርገው ባበህላዊ የቤት አሰራር የተሰራ በመሆኑ ና በግብው ውስጥ የሼክ ኢሳ ውሎ ና የኣበታቸው መቀብር በግቢ ውስጥ መኖሩ፡፡ የአካባቢው ሽመግሌዎች እንደሚነገሩት አንድ ጀበና ቡና ተጠጥቶ እስከሚያልቅ አንድም ቴክኖሎጂ ባልነበረበት  ጊዜ አንድ ኪታብ በእጃቸው  ይጽፉ እንደነበረ ታሪክ አዋቂዎች ይናገራሉ፡፡

 

 

 

        የአዳዘር አካባቢ ትክል ድንጋይ

 

የአዳዘር አካባቢ ትክል ድንጋይ የሚገኛው በስልጤ ዞን በምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ በአዳዘር ሼበል ቀበሌ ስሆን ከወረዳዋ ዋና ከተማ ቂልጦ 10 ኪ/ሜ ከዞኑ ዋና ከተማ ወራቤ 55 ኪ/ሜ እና ከሀዋሳ ከተማ 256 ኪ/ሜ ርቀት ላይ ይገኛል ፡፡ በአካባቢው የተለያዩ ትክል ድንገዮች የሉ ስሆን ይህሄኛው ከሌሎች የሚለይ ስሆን ቁመቱም  1.7 ሜትር ና ስፋት ደግሞ 0.50 ሴንቲ ሜተር ነው፡፡ የአካባቢው ሽመግሌዎች እንደምናገሩት አህመድ ግራኝ ና ሀጅ አሊዬ በጦርነት ጊዜ በዚህች ድንጋይ ፈረሳቸውን እንደሚያሰሩባ ሪታክ አወቂዎች የስራዳሉ፡፡ ይምጡ ይጎብኙ ራስዎን አዝናንተው ይመለሱ፡፡