የቀቤና ልዩ ወረዳ
ህላዊ መስህብ
የቀቤና ብሄረሰብ የባህል ማዕከል

ይህ ግዙፍ ባህል ማዕከል የሚገኘው በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በቀቤና ልዩ ወረዳ ወልቂጤ ከተማ ሲሆን ከአዲስአበባ በ 150 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል። ማዕከሉ ግንቦት 27/2015 ዓም ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።ባህል ማእከሉ በውስጡ ከ 1000 ሰው በላይ በአንድ ጊዜ ማስተናገድ የሚችል ደረጃውን የጠበቀ የስብሰባ አዳራሽ፣ለኪነጥበብ ዝግጅት እና ለአነስተኛ ስስብሰባዎች የሚያገለግሉ ሁለት መጠነኛ አዳራሾች፣የቀቤና ብሄረሰብ የባህል ሙዝየም፣መስጂድ ፣የቀቤንኛ ቋንቋ ማበልፀግያ ማዕከል፣የእንግዳ ማረፊያዎች እና ለልዩ ልዩ አገልግሎት የሚውሉ ቢሮዎችን ያካተተ የክልላችንን ገፅታ የሚያጎላ ግዙፍ የባህል ማዕከል ነው።
በመሆኑም ማዕከሉ በአዲስ አአበባ እና በሆሳና አማካይ ቦታ ላይ ለጉብኝት ምቹ በሆነ ስፍራ ላይ የሚገኝ በመሆኑ ይምጡ እና ይጎብኙ ስለ ቀቤና እና ስለ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህል እና ታሪክ ላይ ሰፊ አስተማሪ እና አዝናኝ መረጃ ያገኙበታል።