Skip to main content

በሀድያ ዞን የሚገኙ ተፈጥሯዊ የቱሪስት መዳረሻዎች

                              በሀድያ ዞን የሚገኙ የቱሪስት መዳረሻዎች

የሀድያ ዞን በማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልላዊ መንግሥት ከሚገኙ ዞኖች አንዱ ሲሆን ከኢፌዴሪ ርዕሰ - ከተማ ከአዲስ አበባ በስተደቡብ ምዕራብ አቅጣጫ ይገኛል፡፡ የሀድያ ዞን በምሥራቅ ከሀላባ ዞን፣ ከስልጤ ዞንና ከኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት፤ በሰሜን ከጉራጌና ከስልጤ ዞኖች፤ በምዕራብ ከየም ዞንና ከኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት፤ እንዲሁም በደቡብ ከከምባታ ዞን፣ ከጠምባሮ ልዩ ወረዳና ከደቡብ ኢትዮጲያ ክልላዊ መንግሥት ጋር ይዋሰናል፡፡በሀድያ ዞን ተፈጥሯዊ፣ ታሪካዊና ባሀላዊ ተብለው የሚመደቡ በርካታ የቱሪስት መስህብ ዓይነቶች ይገኛሉ፡፡

 

    ሾንቆላ ተራራ

 

በሶሮ ወረዳ በሾንቆላ ቀበሌ የሚገኝ ሲሆን ከሆሳዕና በስተደቡብ አቅጠጫ ይገኛል፡፡ከፍታው ከባህር ጠለል በላይ 2800 ሜትር ነው፡፡ለተራራ መውጠት ስፖርት፤ለመዝናኛናትና ለትምህርታዊ ቱሪዝም የሚሆን መስህብ ነው

 

                                
                                      
 
 
 

 

 

 

ከላላሞ ተራራ

በጊቤ ወረዳ በአዎሳ ቀበሌ የሚገኝ ሲሆን ከሆሳዕና በስተምዕራብ አቅጠጫ ይገኛል፡፡ከፍታው ከባህር ጠለል በላይ 1880 ሜትር ነው፡፡ለተራራ መውጠት ስፖርት፤ለመዝናኛናትና ለትምህርታዊ ቱሪዝም የሚሆን መስህብ ነው፡፡
 

                          

 

 

   

 

 

 

ደኖች(ሁነሴ፤ አንድሴና ብዕለገላ ደን …) ይጠቀሳሉ፡፡

ሁነሴ ጥብቅ ደን

    በአምቦሮ ጎይነና ቀበሌ የሚገኝ ሲሀን ከሆሳዕና በስተምዕራብ አቅጠጫ ይገኛል፡፡ በውስጡ በርካታ የዱር እንሰሳት ተጠልለውበት ይገኛል፡፡ደኑን መሀል ለመሀል የዞተሬ ወንዝ አቋርጦት ስለሚያልፍ ለእይታ ምቹ እንድሆን አድርጎተል፡፡በውስጡ በርካታ የሀገር በቀል እጽዋቶችን የከታታ ደን ነው፡፡

 

 

 

 

ሐይቆች(ቦዮ፤ ጢዕሎ፤ ቡዳመደና  መጫፋራ)፤

ቦዮ-ሐይቅ

 በሸሾጎ ወረዳ በ16 ቀበሌያት መሀከል የሚገኝ ሲሆን ከሆሳዕና በስተምሥራቅ አቅጠጫ ይገኛል፡፡ሐይቁ የበርካታ ወፎች መኖሪያና ወቅቱን ጠብቀው የሚመጡ የወጭ ሀገራት ወፎች ማረፊያና መቆያ መስህብ ነው፡፡
 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

የሲራሮ ባዳዋቾ ሐይቆች፤ (ቡደመዳ፣ ጢዕሎና መጨፈራ)

ቡዳመደ ሐይቅ

  • በሲራሮ በዳዋቾ ወረዳ በሽርቆ ገፈርሶ ቀበሌ የሚገኝ ሲሆን ከሆሳዕና በምሥራቀው ደቡብ አቅጠጫ ይገኛል፡፡
    ሐይቁ ዙርያ ዳር ዳሩን የፍል ወኃ ምንጮች አሉት፡፡ለመዝናኛናትና ለትምህርታዊ ቱሪዝም የሚሆን መስህብ ነው፡፡

    ጢዕሎ ሐይቅ
  • በሲራሮ በዳዋቾ ወረዳ በኩቤ ዲምቱ ቀበሌ የሚገኝ ሲሆን ከሆሳዕና በምሥራቀው ደቡብ አቅጠጫ ይገኛል፡፡ሐይቁ ዙርያ ዳር ዳሩን የፍል ወኃ ምንጮች አሉት፡፡ለመዝናኛናትና ለትምህርታዊ ቱሪዝም የሚሆን መስህብ ነው፡፡.

      መጨፈራ ሐይቅ
  • በሲራሮ በዳዋቾ ወረዳ በዌራሞ ቦንኮያ ዲምቱ ቀበሌ የሚገኝ ሲሆን ከሆሳዕና በምሥራቀው ደቡብ አቅጠጫ ይገኛል፡፡ሐይቁ ዙርያ ዳር ዳሩን የፍል ወኃ ምንጮች አሉት፡፡ለመዝናኛናትና ለትምህርታዊ ቱሪዝም የሚሆን መስህብ ነው፡፡ሐይቁ የበርካታ ወፎች መኖሪያና ወቅቱን ጠብቀው የሚመጡ የወጭ ሀገራት ወፎች መረፊያና መቆያ መስህብ ነው፡፡በሐይቁ መሀከል ደግሞ ደሴት መኖሩ ለቱሪስቱ ቀልብ እንድስብ የደርገዋል፡፡

  መጫፈራ፣ጢዕሎናቡዳመደ ሐይቆች

 

ፏፏቴዎች(አገሜና ሆጄ፤ሀብቾ፤ዌራ…….)

 

አገሜና ሆጄ ፏፏቴዎች

  በጎምቦራ ወረዳ በኦርዴ ቦብቾ ቀበሌ የሚገኝ ሲሆን ከሆሳዕና በስተምዕራብ አቅጠጫ ይገኛል፡፡ፏፏቴዎቹ የሚወርዱበት የፊት ለፊቱ አካባቢ በደን የተሸፈነ በመሆኑ ለእይታ ውብና ማራክ ፏፏቴ ነው፡፡
 

 

 

 

 

ኦልዳ ዋሻ
 

ኦልዳ ዋሻ በፎንቆ ከተማ አስተዳደር የሚገኝ ሲሆን ከሆሳዕና በስተሰሜን ምሥራቅ አቅጠጫ ይገኛል፡፡የኦልዳ ዋሻ በጭንጎ ሰንሰለታማ ተራራ ላይ የተቆፈራ ሰው ሰራሽ ዋሻ ሲሆን ሶስት ደርቦች አሉት፡፡