Skip to main content

ሀላባ ዞን

 

                                                    የሀላባ ዞን ታሪካዊ ቦታዎች

የ ኑረላህመድ መካነ መቃብር 

የሀላባ ብሄረሰብ በሀላባ ዞን የሚገኝ ሲሆን ከርዕሰ መዲናችን አዲስ አበባ በ315 ኪ/ሜ ርቀት እና ከክልላችን ሆሳዕና በ80 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ትገኝለች፡፡ የኑረላ አህመድ መካነ መቃብርና የአምልኮ ስፍራ በሀላባ ዞን በዋንጃ ቀበሌ ገበሬ ማህበር በአብቾ ንዑስ ቀበሌ ከቁሊቶ ከተማ ወደ ወለይታ ሶዶ በሚወስደው መንገድ ላይ የሚገኝ ልዩ የሆነ ታሪካዊ የቱሪስት መስህብ ስፍራ ሲሆን  ከዞኑ ዋና ከተማ ቁሊቶ በሶስት ኪ/ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ፡፡ በሀላባ ዞን በርካት ባህላዊ፣ ታሪካዊና ተፈጥሮአዊ መስህቦች ይገኙባታል፡፡ ከነዚህም መስህቦች ውስጥ አንዱ 

 

የኑረላ አህመድ መካነ መቃብር ሰፍራ አንደኛው ነው፡፡ ከተለያዩ አፈ- ታሪኮች መረዳት እንደሚቻለው ስፍራው ከዚህ 350ዎቹ አመት ገደማ የተመሰረተ እንደሆነ ይነገራል፡፡   ለዚህም እንደ ምክንያት የሚጠቀሰው በ17 ኛው ክፍለ ዘመን በባሌና አከባቢው ይኖሩ የነበረ አንድ የሃይማኖት አባትና የእስልምና እምነት ሰባኪ እንደሆኑ ነው፡፡ 

እኚህ የሃይማኖት አባት/  የኑረላ አህመድ መነሻቸውና ባሌ አድርገው ሃይማኖቱን ለመስበክ ከአባታቸው ጋር የተለያዩ ሀገራትን እያቋረጡ ሀላባ ቁሊቶ ከደረሱ በኋላ ባደረባቸው ህመም ህይወታቸው ያለፈና በዚሁ ስፍራ የቀብር ስነ- ስርዓታቸው መፈጸሙን አፈ- ታሪኮች ይናገራሉ፡፡  የኑረል አህመድ አባት የሆኑት ኑር ሁሴንና ልጃቸው ኑረል አህመድ እምነቱን ለመስበክ መነሻቸውን ባሌ አድርገው  አሰላ ለተወሰኑ ጊዜያት ከቆዩ በኋላ ማረቆን፣ ስልጤን፣ሻሾጎን፣ከንባታን በመጨረሻም ካካለሉ በኋላ ወደ ሀላባ በመምጣት እንዳሳለፉይነገራሉ፡፡ 

የኑረላህመድ መካነ መቃብር የስሜ ትርጉዋሜ ያገኝው ከባሌ ሼክ ሁሴን የልጅ ስም ኑረል አህመድ እንደተሰየመ በአከባቢው የሚኖሩ የእድሜ ባለፀጎች ይመሰክራሉ፡፡ የኑር አህመድ መካነ መቃብር በብዙ ሺህ ጉብኚዎችና ተሳታፊዎች የሚጎበኝ ብዙን ግዜ በአረፋ በዓል ነው፡፡ በዚህ በአል ቀን ከተለያዩ አጎራባች ከተሞችና ክልሎች ጎብኚዎችና ተሳታፊዎች በመምጣት የተለያዩ የአምልኮና ፀሎት ስነ-ስርዓት ይከናወንበታል፡፡ 

 

የኑር መስጂድ

ኑር መስጂድ  ማለት ኑር የሚለው ቃል የዐረብኛ ቃል ሲሆን ትርጉሙም  ብርሃን ለማለት ነው፡፡ የኑር መስጂድ በሀላባ ቁሊቶ ከተማ  እጅግ በጣም ታሪካዊና ጥንታዊ መስጂዶች ውስጥ አንዱ ሲሆን ከአንዳንድ መረጃ ሰጪዎች በተገኘውመረጃ መሰረት በሁለተኛው የኢጣሊያ  ወረራ ጊዜ በቆርቆሮ  ክዳን  እንደተገነባ  እና በአሁን ሰዓት  በደቡብ ክልል በ1ኛ  እና በመለው ሀገሪቱ ካሉ ትላልቅ  መስጂዶች  በሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡

የኑር መስጂድ ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ የተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥርዓቶችን ለመፈፀሚያ፣ፈጣሪን ለማመስገንና ፀሎት ለማድረስ ከሚጠቀሙበት ባሻገር ዋና እና አብይ ጉዳይ ስለ እስልምና እምነት ለማስተማር የተለያዩ  ደረሳዎች (የእስልምና እምነት ተማሪዎች) ስለ ቅዱስ ቁርዓን እና ሌሎች  ሀይማኖታዊ ትውፊቶችን ጠብቆ ለማኖር  የሚያገለግል ቅዱስ ስፍራ ነው፡፡

የኑር መስጂድ  በአሁን ሰዓት የእስልምና  እምነት ተከታዮች ፈጣሪያቸውን ከማመስገኛ ባለፈ  በከተማችን ታሪካዊና  ታላቅ  መስጂድ መሆኑ ይበልጥ  እንዲጠበቅና ለቀጣይ ትውልድ እንዲተላለፍ በጥብቅ እየተጠበቀ  ይገኛል፡፡ መስጂዱ አሁን ካለበት ደረጃ ወደ ተሻለ የመታወቂያ ደረጃ  ለማድረስ  እንደ ጽ/ቤታችን ተልዕኮና  አላማ አንፃር በተለያዩ የመንግስተና የግል ሚዲያ ተቋማትን እና የተለያዩ የጥናትና ምርምር ሥራዎችን  ለሚሰሩ አጥኚዎች  አማካይነት እየሰራን  እንገኛለን፡፡

የመጎብኘት ደረጃ፡- መስጂዱ በተለያዩ ሀይማኖታዊ ክብረ-በዓላት ወቅት  በሺዎች የሚቆጠሩ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ዜጎች አልፎ አልፎ በመምጣት ሀይማኖታዊ ሥርዓትን በመፈፀምና  ላልጎብኙትና  ለላዩት ሰዎች መስጂዱን  እንዲጎበኙ ማድረግ ተችሎዋል፡፡ 

የኑር መስጂድ ከሀላባ ቁሊቶ ከተማ  ቡታጅራ በሚወስደው  ዋናው   የአስፓልት  መንገድ እና በከተማው የውስጥ  ለውስጥ  መንገድ  ወደ ዳንቦያ ተራ በሚወስደው  ዋናው መንገድ  ላይ መሆኑ ቱሪስቶች ቦታው ድረስ ቀላል በሚባል ዓይነት የትራንስፖርት መንገዶችን በመጠቀም የሚደረስበት መሆኑ ለሁሉም  ጎብኚዎች  ቅርብ ነው፡፡

መስጅዱ በከተማው ውስጥ የተለየ የቦታ መለያ መጠረያ  ከመሆኑም በላይ የግንባታው ዘመናዊነት ለከተማዋ ተጨማሪ ውበት ሆኗል።