ጠምባሮ ልዩ ወረዳ
ላሞ_ፏፏቴ
ላሞ ፏፏቴ የሚገኘዉ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጠምባሮ ልዩ ወረዳ በባዳ ቀበሌ ሲሆን ከአዲስ አበባ በ317 ኪ.ሜ ከልዩ ወረዳው ዋና ከተማ ሞዱላ በ4 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል።ርዝመቱ ከባህር ወለል 60 ሜትር ስፋቱ ደግሞ 8 ሜትር ነዉ። በፏፏቴዉ ዙሪያ የተለያዩ ዕድሜ ጠገብ አገር በቀል ዛሮች በዙሪያው ይገኛሉ።በዙሪያው ያሉ ዛሮች ላይ የወፍ ዝርያዎች እና በፏፏቴዉ በሁለቱም በኩል ለምልመዉ የሚገኙት ሀረጎችና ረጃጅም ስሮች ለፏፏቴዉ ልዩ ዉበት ናቸዉ። ፏፏቴዉ ወደ ታች ሲወረወር መንትያ ፏፏቴ ሆኖ ይወረወራል።