Skip to main content

የስልጤ ዞን ባህላዊ መስህቦች

የስልጤ ዞን ባህላዊ መስህቦች

የስልጤ ብሔረሰብ ታሪክና ባህል የሚመዘዝባቸው ጥንታዊ መስጊዶች፣ ዋሻዎች፣ ትክል ድንጋዮችና ልዩ ባህላዊና ሀይማኖታዊ ገፅታ ያላቸው ወቅትን ጠብቀው የሚከናወኑ ክንውኖችና ፌስቲቫሎችም ይገኙበታል፡፡ የስልጤ ዞን የሚገኘው በታላቁ ስምጥ ሸለቆ ውስጥና ምዕራባዊ ክንፍ የሚገኝ በመሆኑ የአስደናቂ ሐይቆች፣ ፍልውሃዎች፣ ወንዞችና የተለያየ አይነት መገለጫ ያላቸው ተራሮች ባለቤት እንዲሆን አስችሎታል፡፡ ዞኑ ከሀገሪቱ ዋና ዋና ከተሞች (አዲስ አበባና ሀዋሳ) ከ170-210 ከ.ሜ. ባልበለጠ ርቀትና የኢትዮጰያ ደቡባዊ የቱሪስት መስመር (The South Tourist Route) ከአ.አ-አ/ምንጭ-ጂንካ በተዘረጋው አስፓልት መንገድ ላይ የሚገኝ በመሆኑና የተለያየ ዓይነት ባሕሪይ ባላቸው ቱሪስቶችና ተመራማሪዎች ተመራጭ እንዲሆን አቅም ፈጥሮለታል፡፡

 አረፋ /Arefa Festival/

የስልጤ ብሔረሰብ ከ99% በላይ የሚሆነው የህብረተሰብ ክፍል የእስልምና ሀይማኖት ተከታይ እንደመሆኑ የአረፋ (የኢድ አል አድሃ) በዓል በብሔረሰቡ በድምቀት ከሚከበሩ በዓላት ዋናውና ልዩ ባህላዊ ይዘት ያለው ክብረበዓል ነው፡፡ ተከብሮ የሚውለውም የረመዳን ጾም ከተፈታ በ2 ወር ከ10 ቀን ነው፡፡ የአረፋ በዓል አከባበር በብሔረሰቡ በ3 ደረጃዎች ከፍሎ ማየት የሚቻል ሲሆን ቅድመ አረፋ ፣ ዕለት አረፋና ድህረ አረፋ ብለን ልንከፍለው እንችላለን፡፡ እንጨት ፈላጣ ፣ እንሰት መፋቅ /ኡሳቻ/ ፣ ቤት በባህላዊ ቀለም ማስዋብ /ናዞዋበበርበሮ ጋር አንጣጦት/ ፣  የብሔረሰቡ የከተማ ነዋሪዎች (ፋኖዎች) ወደ ቀዬአቸው መትመም ፣ የቅቤና የእርድ ከብት ዝግጅት በቅድመ አረፋ አስገራሚ ትዕይንቶች ዋና ዋናዎቹ ሲሆኑ ርድ ፣ ሰላትና ልዩ ልዩ ባህላዊ ምግቦች ዝግጅት (በሴቶችና በወንዶች አረፋ) በዕለተ-አረፋ ከሚከናወኑ ተግባራት ይጠቀሳሉ፡፡ በድህረ-አረፋ የዘመድ ጥየቃ የፎላ ባህላዊ የምግብ ዝግጅትና አበላል ስርዓት መተጫጨት ክፍለ ጊዜ ነው፡፡ የሚጧጧፍበት  በዓሉ በዋናነት በደጋዎች የዞኑ ወረዳዎች (በአልቾ ውሪሮ ፣ በምዕራብና ምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳዎች) የሚከበር ነው፡፡በአረፋ ሰሞን የሚመጣ ጎብኚ ከመደሰትና ከመዝናናት ውጪ የምግብም ሆነ የሌላ ጉዳይ ማሰቢያ ጊዜ አይኖረውም፡፡

 

 

 

 

                 የስልጤ ባህላዊ የቤት ውስጥ መገልገያ ቁሳቁሶች

 

ስልጤ ማህብረሰብ የራሱ የሆነ የአመጋገብ ስርዓት፣የቤት ዉስጥ አጋጌጥ፣የቤት አሰራር፣የአስተራረስ ዘይቤ የአለባበስና በቤት ዉስጥ የሚጠቀማቸዉ በአካባቢዉ ቁሳቁሶች የተመረቱና ብዙ የክብር መገለጫነትም ያላቸውባህላዊ የቤት ቁሳቁሶች አሉት፡፡በመሰረቱ እነዚህ ቁሳቁሶችበዘመናችን ለሚገኙት ለዘመናዊ ቁሳቁሶች መሰረት የነበሩ መሆኑን በቀላሉ ዓይን አይቶ መመስከር ይቻላል፡፡ በእርግጥ የዞኑ ማህበረሰብ አብዛኛዉ የቤት ዉስጥ መገልገያቁሳቁሶች ተቀራራቢ ቢሆኑም በጥቂት መገልገያዎች ከቦታቦታ መለያየታቸዉ የማይቀር ነዉ፡፡ለመሆኑ እነዚህ የህብረተሰቡ ባለውለታ ቁሳቁሶች በዘመናቸዉ ፋሽን የነበሩ መሆኑን እንደመንዘነጋ ባለ ሙሉ ተስፋ ነን፡፡እነዚህን አገር በቀል የጥንት አባቶች የእጅ አሻራና ጥበብ የረፈበትን ቁሳቁስ በማየትና ለምርምር ስራ እንዲውሉ ማድረግና ታዋቂ እንዲሆኑ ጥረት ይደረግ እንላለን፡፡

 

 

 

 

                     የስልጤ ባህላዊ መንደር 

በሁሉም አካባቢዎች ማለት ይቻላል የስልጤ በህላዊ መንደር በዘመናችን የከተማ አመሰራረት ይዘትን በያዘ መልኩ  አንድ ላይ እጅብ ብሎ ሲታይ አይንን ያማልላል፤በእርግጥ ይህ ባህላዊ መንደር ለከተማ መንደር መሰረቱ መሆኑ የማይካድ ሃቅ ነዉ፡፡ይህ ባህላዊ መንደር በሁሉም አካባቢዎች ያለ ቢሆንም ውበት ባለዉ መልኩና  የስልጤን ማህበረሰብ ባህላዊ ይዘቱን ጠብቆና ለጉብኝት በሚመች ሁኔታ በዋናነት በምስራቅ አዘርነት በርበሬ፣በአሊቾ ውሪሮና በምዕራብ አዘርነት በርበሬ ወረዳዎች  በብዛት ይገኛሉ፡፡ሃገርን ማወቅ ከአካባቢ ይጀምራል  የሚለዉን መሪ ቃል በመያዝ እነዚህ ባህላዊ የመንደር አመሰራረቶች  ባአረቱም አቅጠጫዎች ተዛዙሮ በምናይበት ወቅት ልዩ የሆነ ዉበት አለው፡፡ በውስጣቸውም በርካታ ባህላዊ ክንዋኔዎች፣የረጅም  ጊዜ ታሪኮች፣ወጎች፣ በውስጣቸዉ አቅፈዉ  የያዙ በመሆኑ ለጉብኝት ራሳችንን፡፡

 

         

 

    የዳሎቻ ሰኞ ገበያ

የዳሎቻ ገበያ አመሰራረት ከከተማዋ አመሰራረት ጋር እጅጉን የተቆራኘና የዳሎቻ ከተማ የወረዳነት መዋቅር ያገኘው ከ1935 ዓ/ም እንደሆነ በርካታ የታሪክ አዋቂዎች እና የሀገር ሽማግሌዎች ይናገራሉ፡፡ ገበያውም የተመሰረተው በጊዜው እና በአካባቢው ገዢ በነበረው በአቶ አዘነ ውቤ በተባለ ግለሰብ እንደነበረም ይገልፃሉ፡፡ ይህ ግለሰብ ለገበያው መመስረት ከፍተኛ ሚና ነበረው፡፡ ገበያው በግብይት ስነ-ስርዓት እና በምርት አቅርቦት ከክልል ከትላልቆቹ የግብይት ስፍራዎች ተጠቃሽ ነው፡፡ በዕለቱ ከፍተኛ የሆነ ለኢንዱስትሪና ለፋብሪካ የሚሆን የግብርና ምርቶች የሚቀርቡ ሲሆን በግብይት ስርዓቱ በግምት ከ50.000 ህዝብ በላይ እንደሚገባይ ይጠቀሳል፡፡ ገበያው ተሳታፊዎች በአጎራባች ክልል ከኦርሚያ፣ ከጉራጌ እና ከሀዲያ ዞኖች ከአዲስ አበባ እንዲሁም የዞኑ ህዝብ በዋናነት ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ለማዕከል ገበያ አ/አ ከሚቀርቡት የበርበሬ፣ የስንዴ፣ የቀንድ ከብቶችና የበቆሎ ወዘተ ምርቶች 

 

የዳሎቻራጋኦዳና  የሳቦላ  ዝግባ የባህላዊዳኝነትስፍራ፡-/Dalocha  RagaOda  & Sabola Zigba Cultural Conflict Resolution Sites/

የዳሎቻራጋኦዳና የሳቦላ ዝግባ የባህላዊዳኝነትስፍራ፡-/Dalocha Raga Oda & Sabola Zigba Cultural Conflict Resolution Sites/እነዚህ ቦታዎችበስልጤብሄረሰብውስጥ በተለያዩምክንያቶችየሚነሱግጭቶችንለመፍታትየሚጠቀሙባቸውባህላዊቦታዎችሲሆኑየሚገኙትበዳሎቻከተማና በሁልባራግ ወረዳነው፡፡የባህላዊየዳኝነትሥርዓቱ 3 ደረጃዎች /ማጋ፣ራጋናፈረዝአገኘ/ ቢኖሩትምእነዚህ ቦታዎችከማጋ/የመጀመሪያደረጃ/ ከፍብሎያሉጉዳዮችበራጋሥርዓትየሚታዩበት ነዉ፡፡ሥርዓቱየሚካሄደው በዋርካ/ኦዳ/ና በዝግባስርሲሆንአንድጉዳይለማየትከ30 ደቂቃእስከ 1 ሰዓትየሚፈጅሆኖበቀንበአማካይከ10-15 ጉዳዮችሊታዩይችላሉ፡፡ጉዳዩየሚታይላቸውሰዎችየሚከፍሉትገንዘብአለ፡፡የዳሎቻ ራጋ ኦዳ የዳኝነት ስርዓቱ በመደበኛነት የሚካሄደው በሳምንቱ ሰኞ ሲሆን በሌሎችም ቀናት እንደጉዳዩ አስቸኳይነት ሊታይ ይችላል፡፡