Skip to main content

ከምባታ ዞን

  • በከምባታ ዞን ተፈጥሯዊ፣ ታሪካዊና ባሀላዊ ተብለው የሚመደቡ በርካታ የቱሪስት መስህብ ዓይነቶች ይገኛሉ፡፡

                                ሀምበሪቾ 777

ሀምበሪቾ በከምባታ ጠምባሮ ዞን ከባህር ጠለል በላይ 3058 ሜትር ከፍታ ላይ የሚገኘው በማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ከፍተኛ ተራራ ነው። በዞኑ የሚኖሩ ህዝቦች ተራራውን እንደ መስህብ ብቻ ሳይሆን በዞኑ መሃል ካሉ የተፈጥሮ ፀጋዎች አንዱ አድርገው ይቆጥሩታል። እንዲሁም በአብዛኛው ከህዝቡ ማንነት ጋር የተያያዘ ነው። አብዛኞቹ ታላላቅ ታሪካዊ ስሞች እና ክስተቶች ከሐምባሪቾ ጋር የተያያዙ ናቸው። ለምሳሌ የቀድሞ ባህላዊ የፖለቲካ አስተዳደር ሀምበሪቾን የፖለቲካ መቀመጫ አድርጎ ይጠቀም ነበር። ከጥንት ጀምሮ እስከ ቅርብ ጊዜ ያሉ አብዛኞቹ ሃይማኖታዊ ክንውኖች በተራራው ላይ እየተፈጸሙ ነው።ተራራው የብዝሀ ህይወትን በመጠበቅ ለዕፅዋትና ለእንስሳት ምቹ የመኖሪያ አካባቢ ሆኖ ያገለግላል። ተራራው ማራኪ ሰንሰለቶች፣ በርካታ ምርጫዎች፣ የተዘረጋው የደጋ መልክዓ ምድር ከሸለቆዎች፣ ገደሎች እና ሸለቆዎች ጋር የሚያካትቱ የተለያዩ መስህቦች አሉት። እስካሁን ድረስ የቱሪስት መስህብ ሆኖ እያገለገለአይደለም።

የደረጃው ግንባታ የሚጀምረው ከታሪካዊው የፈረስ ግልቢያ ሜዳ በተለምዶ የፈረስ ግልቢያ ሜዳ (ፋር
 ገበራንቹ) እየተባለ እስከ ተራራው ጫፍ ድረስ ሲሆን የ777 ደረጃዎች የመጨረሻዎቹ 10 ደረጃ
ዎች በዋሻ ውስጥ ያልፋሉ። ደረጃው ከአካባቢው ስነምህዳር ጋር ተስማምቶ የተገነባ ሲሆን ከተራራው
ስር ተጓዦች የሚጎበኙባቸው7 የማረፊያ ቦታዎች አሉት።አጠቃላይ የደረጃዎች ርዝመት  581.7 ሜት
ር; ስፋቱ ከ1.6 ሜትር እስከ 3 ሜትር; እና የኮንክሪት መንገድ114 ሜትር መሬት፣ ጥርጊያ
መንገድ 520 ሜትር ነው።የጎግል መረጃ እንደሚያሳየው የኢትዮጵያው ሀምበሪቾ 777 ደረጃዎች ከአ
ፍሪካ አንደኛ ከአለም ደግሞ ሰባተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ። ከኛ ደረጃ በላይ የሆኑ ስድስት አገሮች
ስዊዘርላንድ 11,674 ደረጃዎች አሏት። ቻይና  5,164 ደረጃዎች አሏት; ፔሩ 3,000 ደረጃ
ዎች አሉት; ስሪላንካ 1,200 እርከን አላት; ዮሰማይት (አሜሪካ); እና ሁሼን (ቻይና) የሀም
በርቾ 777 ኢኮ-ቱሪዝም ደረጃዎች ተሠርተው የተሰየሙበት ሦስት ዋና ዋና ምክንያቶች፡-

1) በሀምበርቾ ተራራ ዙሪያ 7 ዋና ተራሮች

2) በሀምበርቾ ተራራ ዙሪያ አካባቢው የመጡነገዶች (ከምባቲ ለማ)

3) ከሀምበርቾ ተራራዎች  የወጡ 7 ወንዞች (ለመል-ለጋ)

 

               የአጆራ መንቲያ ፏፏቴ 

 

 የአጆራ መንቲያ ፏፏቴ በውበቱና በማራኪነቱ በዞናችን ብሎምበክልላችን ከሚገኙ መስህቦች ለየት ያለ ነው፤

ከሁለት ወንዞች ማለትም ከሶኬ ወንዝ እና ከአጃቾ ወንዞች የተፈጠረ መንያ ፏፏቴ ነው፤ሁለቱም ወንዞች መነሻቸው ከዞናችን ከቃጫቢራ ወረዳ ከመሳፌ እና ላዳቀበሌዎችሆኖየፏፏቴዎቹርዝመትበግምትየሶኬ 100ሜትር የአጃቾ 90 ሜትር ነው፡፡

ፏፏቴዎቹ በወላይታ ዞን በኩል መጎብኘት የሚቻል ቢሆንም በሀደሮ ጡንጦ በኩል ግን በጣም አመቺና ከወረዳ ከተማ ከሀደሮ በ8 ኪ/ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን በአሁን ሰዓት የመንገድ ጥገናና እድሳት ተደርጎ ያለምንም ውጣ ውረድ መጎብኘት ይቻላል፡፡

ፏፏቴዎቹ በአጆራ ገደል ውስጥ የሁለቱም ወንዞች ውኃ ተገናኝቶ አንድ ወንዝ በመፍጠር አረንጓዴና ለምለም ተፈጥሯዊ ውብ የመሬት አቀማመጥ ፈጥሮ ወደ ግቤ ወንዝ(አሁን ላይ ሰው ሰራሽ ሀይቅ ) ጋር ይቀላቀላሉ፡፡

 

የሶኬ ፏፏቴ

የጥስ ከወረዳው ዋና ከተማ በ6 ኪ/ሜ ርቀት ላይ የሚገኝ፤ በአጠገቡ ለፎቶግራፍ እና ለልዩልዩ መዝነኛዎች ምቹ የሆነ መስክ ያለበት ሲሆንለሠርግ ፎቶ ለመነሳትና ፍቅረኞች ሊዝናኑ የሚችሉበት ልዩ ትዝታ ሰንቀው ልመለሱ የሚችሉበት  ድንቅ መስህብ ነው፡፡ለሙዚቃ ዝግጅት ክሊፕ የሚሠሩ አካላት ሊጠቀሙ ይሚችሉበት ድንቅ የሆነ ተፈጥbዊ መስህብ ነው፡፡አባይ ፏፏቴን የሚመስል ልዩ ውበት ያለው ፏፏቴ ነው፡፡

 

 

 

 

 

 

 

 

                 

                              ኤሬራሞ ፏፏቴዎች

ይህን ፏፏቴ ልዩ የሚያደርገው አስደናቂና ለዓይን ዕይታ ሳቢ የሆነውን መልክዓ ምድር በሶስት አቅጣጫ እያቆራረጠ መጥቶ ድንቅ በሆነው በሳሮቢራ የመሬት አቀማመጥ ታጅቦ የተፈጠረ ሲሆን የተመልካቾችን ልቦና ከመማረኩም በላይ አምላካዊ ሥራ ምን ያህል ውስብስብና ለመገመት አዳጋች እንደሆነ የሚያሳይ መስህብ ነው፡፡

በሳሮቢራ ተፈጥሯዊ ውብ የመሬት አቀማመጥ  የታጀበ ሶስት ፏፏቴዎችን አካቶ የያዘ የፏፏቴዎች ጥምረት ያለበት መስህብ ነው::

 

 

 

ሳሮ ቢራ የመሬት አቀማመጥ

     

ውስጡ በደን የተሸፈነና ከላይ የኤሬራሞ ፏፏቴዎች ያሉበት፤የኦሞ ወንዝ ዉብና አረንጓዴ ሸለቆ ላይ ወንዙን ተከትሎ ግልገል ግቤ 3 ግድብ ምክንያት በተፈጠረው ሰው ሰራሽ ሀይቅ አሻግሮ   በርቀት የዳውሮ ዞንን እያዩ፣የጠምባሮ ወረዳንና የወላይታ ዞኖችን የሚያዋስን በመሆኑ በዚህ ድንቅ የተፈጥሮ የመሬት አቀማመጥ ተፈጥሮን እያደነቁ ከላይ የተጠቀሱ አካባቢዎችን መቃኘት ይቻላል፡፡

 

 

 

 

 

 

 

 

 

የእግዜር ድልድይ

    

  •  የመንዶዬንና የአጆራ ቀበሌዎችን በሚያዋስን በሳና ወንዝ ላይ የተፈጠረ፤ከስር ወንዙ የሚያልፍበት ድልድይ ነው፡:ዘመናዊ ድልድይ ባልተለመደበት ጥንት ዘመን ከተለያዩ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ ነጋዴዎች ይተላለፉበት የነበረ (የወላይታ፣የሀዲያ፣የዶንጋ፣የከምባታ፣የጠምባሮ እና የዳውሮ ነጋዴዎችና መንገደኞች ይተላለፉበት የነበረ )

    በመንዶዬም ሆነ በአጆራ ቀበሌዎች በኩል ለእይታ ምቹ ነው፤የፈጣሪን ድንቅ ስራ እያዩ የሚደመሙበት መስህብ ነው፡:

 

 

 

 

ቶራ ተራራ

በርዝመቱ ከቦሃ ተራራ የሚበልጥ ሲሆን አናቱ ላይ ከወጡ የወላይታ ዞንን የሀድያ ዞንንና የዳውሮ ዞኖችን እንዲሁም የዞናችንን አብዛኘውን ክፍል ማየት ያስችላል፤

በአናቱ ላይ ሰፊ ሜዳና በርካታ ሸኛ መሳይ ወጣ ገባነት የሚታይናበት ነው ፤

ከዶንጋ ብሄረሰብ ታሪካዊ አመጣጥ ጋር የተቆራኘ መሆኑና ዙሪያው በተፈጥሮና ሰው ሠራሽ ደኖች የተሸፈነና ከስሩም በርካታ ምንጮች መፍለቂያ ሆኖ ያገለግላል፡፡

 

 

 

 

 

 

 

ሶድቾ_ዋሻ

ሶድቾ ዋሻ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከምባታ ዞን በሀደሮ ጡንጦ ዙሪያ ወረዳ ሶድቾ ቀበሌ በሶድቾ ተራራ ላይ ይገኛል። 

ከከምባታ ዞን ዋና ከተማ ዱራሜ ወደ ሙዱላ በሚወስደው አስፓልት መንገድ በ41ኪሎ ሜትር ርቀት ከጡንጦ ከተማ በስተቀኝ ጥቂት የጠጠር መንገድ ከሄዱ በኋላ 400 ሜትር የተራራ እግር ጉዞ አድርገው ዋሻውን ያገኙታል።

የዋሻው ስፋት 28×28 ሜትር ሲሆን ከወለሉ እስከ ጣሪያው ያለው ርዝመት 15 ሜትር ነው። በድሮ ዘመናት በአካባቢው ይኖሩ የነበሩ ሰዎች  በተለያየ ጊዜ ከተካሄዱ ጦርነቶች ሲሸሸጉበትና እንደምሽግ ሲገለገሉበት ነበር ።

በአውሮፓውያኑ የዘመን አቆጣጣር ከ2015 ጀምሮ ከጀርመኑ ኮሎኝና ከሌሎች አውሮፓ ሀገራት ዩንቨርሲቲዎች የተወጣጡ የአርኪዎሎጂ ጥናትና ምርምር ቡድን ከኢትዮጵያ ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን እንዲሁ ከሚመለከታቸው በተዋረድ ካሉት ተቋማት ጋር በመተባበር ሲያደርጉት የቆዩት የጥናት ውጤት እንደሚያሳየው ሰዎች ከዛሬ 21000 ዓመታት በፊትም እንደመጠለያ (rockshelter) ሲጠቀሙ የኖሩበት የተፈጥሮ ዋሻ ነው። ዋሻው ከባህር ጠላል 1930 ሜትር ከፍታ ላይ የሚገኝ ሲሆን ከሀገራችን ዋንኞቹ የአርኪዎሎጂ ስፍራዎች አንዱ እንደሆነም ይታወቃል።