የቢሮው ተግባርና ሀላፊነት
የክልሉ ብሔረሰቦች ቋንቋ፣ ባህል፣ ቅርስና ኪነጥበብ እንዲጠበቁ፣ እንዲጠኑና እንዲታወቁ ያደርጋል፣
የክልሉ ብሔረሰቦች ታሪካዊና ባህላዊ ቅርሶች፣ የፊልምና የትያትር ዘርፎች እንዲለሙና እንዲጠበቁ ያደርጋል፣
የቱሪዝም እንዱስትሪዎች እንዲስፋፉ በዘርፉ ለሚሰማሩ ባለሀብቶች፣ ድርጅቶችና ማህበራት የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ይሰጣል፣ ይቆጣጠራል በሕግ መሰረት ይሰርዛል፣
ማህበራዊ ዕድገትን የሚያጓትቱ አመለካከቶችን እና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለመከላከል የሚያስችሉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን ያከናውናል፣
በክልሉ የሚገኙ ቁሳዊና ቁሳዊ ያልሆኑ የባህል ቅርሶችን ያሰባስባል፣ ይመዘግባል፣ እንዲጠበቁ ያደርጋል፣
በክልሉ ተፈጥራአዊ የቱሪዝም መስህቦችና የዱር እንስሳት መገኛ ቦታዎችን ያጠናል፣ አዋጭነታቸውን አረጋግጦ እንዲከለሉና እንዲጠበቁ ያደርጋል፣ ይቆጣጠራል፣
የቱሪዝም አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች እንዲስፋፉና የአካባቢው ሕዝብ ከቱሪዝም ልማት ተጠቃሚ የሚሆንበትን ስልት ይቀይሳል፣ ተግባራዊም ያደርጋል፣
የክልሉን ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ባህል፣ ቋንቋ፣ ታሪክና ቅርስ የሚያሳይ ቤተ-መዘክርና ባህላዊ መንደሮች ያደራጃል፣ ያስተዳድራል፣
በክልሉ የሚተዳደሩ የዱር እንስሳት ጥበቃ ክልሎችና ሌሎች የቱሪስት መስህብ ስፍራዎች የሚገኙ ገቢዎችን ይሰበስባል፣
በክልሉ ለሚገኙ የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ክልላዊ ደረጃ ይሰጣል፣
በሰው ሃይል ሥልጠናና በሙያ ምክር አገልግሎት አማካይነት የቱሪዝም ዘርፍን የማስፈፀም አቅም ይገነባል፣
ለቱሪዝም ገበያ አስፈላጊ ሆነው የሚገኙ የዱር እንስሳት እርባታ ጣቢያዎችን እና ፓርኮችን ያቋቁማል፣ ያስተዳድራል፡፡
በክልሉ የሚገኙ ፓርኮችን እንዲጠበቁ ያደርጋል፤ ልማትና አስተዳደራዊ ስራዎቻቸውን ይከታተላል፣ ይደግፋል፣