ከኢፌድሪ ቱሪዝም ሚኒስቴርና ከሚዲያ ተቋማት የተወጣጡ የሚዲያ አባላት በየም ዞን የሚገኙ የቱሪስት መዳረሻዎችን ጎበኙ።
ከኢፌድሪ ቱሪዝም ሚኒስቴርና ከሚዲያ ተቋማት የተወጣጡ የሚዲያ አባላት በየም ዞን የሚገኙ የቱሪስት መዳረሻዎችን ጎበኙ።
ሣጃ:-ሰኔ 5/2017
ከኢፌድሪ ቱሪዝም ሚኒስቴርና ከሚዲያ ተቋማት የተወጣጡ የሚዲያ አባላት በየም ዞን በመገኘት ከቱሪስት መዳረሻዎች አንዱ የሆነውን ጥንታዊውን የአንገሪ ቤተ መንግስት ጎብኝቷል። የሚዲያ ባለሙያዎቹ ጉብኝት አላማ በክልሉ እና በዞኑ ያሉ የቱሪዝም መዳረሻ ስፍራዎች በመጎብኝት በሀገር እና ለአለም ማስተዋወቅ መሆኑን ተመላክቷል። የየም ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ አቶ መስፍን ሞጋ እንደገለፁት የየም ዞን የበርካታ የቱሪዝም ስፍራዎች መገኛ መሆኗን ጠቅሰው ጥብቅ ደኖች ፣ፏፏቴዎች ፣ጥንታዊ ገዳማትና መስጂዶች ፣የዳኝነት ስፍራዎች ፣ዋሻዎች ፣ፍል ውኃዎች፣የባህላዊ ምግቦች እና ሌሎች የልዩ ልዩ ቅርሶች ባለቤት በመሆኗ ለአብነት አንስተዋል። በተያታዘም ዞኑ በባህል ፣በቱሪዝም ፣በታሪክ እና በቅርስ እምቅ ሀብት ያለው መሆኑን ኃላፊው አመላክተዋል። ከቱሪዝም ሚኒስቴር የመጡ የሚዲያ ቱሮች በበኩላቸው በዞኑ ባደረጉት ምልከታ እጅግ መደሰታቸው እና የየም ዞን ታሪካዊ እንዲሁም አስደማሚ የቱሪዝም ስፍራዎች ባለቤት መሆኗ አይተናል ብለዋል። በቀጣይም በዞኑ የጎበኙትን ሌሌሎች በማስተዋወቅ የዞኑ የቱሪዝም ዘርፉ እንዲነቃቃ የበኩላቸው እንደሚወጡ አስታውቀዋል። በመጨረሻም ኃላፊው ለጉብኝቱ መሳካት ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ግለሰቦችንና ተቋማትን ያመሰገኑ ሲሆን፣ በተለይም የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ፣የየም ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት፣የየም ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት እና ጎኔር ፕሮሞሽንን አመስግኗል።
