Skip to main content

የባህል ሽማግሌዎች የየአካባቢዉን ባህላዊ እሴቶችና የእርቅ ሥርዓቶች መሠረት አድርገዉ ችግሮችን መፍታት ይጠበቅባቸዋል - ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር)

የባህል ሽማግሌዎች የየአካባቢዉን ባህላዊ እሴቶችና የእርቅ ሥርዓቶች መሠረት አድርገዉ ችግሮችን መፍታት ይጠበቅባቸዋል - ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር)

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር እንዳሻዉ ጣሰው፣ ከስልጤ ብሔረሰብ የባህል ሽማግሌዎች ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል ።በዉይይት መድረኩ ቀደም ሲል በስልጤ ዞን አሊቾ ዉሪሮ ወረዳ ዉስጥ ተከስቶ የነበረዉን አለመግባባት በብሔረሰቡ ባህላዊ እሴትና የእርቅ ስርዓት መሠረት በባህል ሽማግሌዎች አማከይነት እርቅ በመፈጸም እልባት ማግኘቱ ተገልጿል ።በአካባቢዉ ተፈጥሮ የነበረዉን ጊዜያዊ አለመግባባት በመፍታት የአብሮነት መንፈሱ ወደቀድሞዉ መልካም ሁኔታ እንዲሸጋገር የባህል ሽማግሌዎቹ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር እንዳሻዉ ጣሰዉ ምስጋና አቅርበዋል ።የየአካባቢዉ የባህል ሽማግሌዎች የየአካባቢዉን ባህላዊ እሴቶችና የግጭት መፍቻ ሥርዓቶችን መሠረት አድርገዉ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችንና አለመግባባቶችን መፍታት እንደሚጠበቅባቸውም ርዕሰ መስተዳድሩ አሳስበዋል ።

Image
photo