Skip to main content

ክብረ በዓላት ከሀይማኖታዊ ስርዓት በተጨማሪ የአንድን አካባቢ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ ሀብቶች ለማስተዋወቅ ሚናቸውን የጎላ በመሆኑ ሀብቶቹ ማልማት፣ ማደራጀትና ማስተዋወቅ እንደሚገባ ተገለፀ።

ክብረ በዓላት ከሀይማኖታዊ ስርዓት በተጨማሪ የአንድን አካባቢ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ ሀብቶች ለማስተዋወቅ ሚናቸውን የጎላ በመሆኑ ሀብቶቹ ማልማት፣ ማደራጀትና ማስተዋወቅ እንደሚገባ ተገለፀ።

የጥንታዊውና ታሪካዊው አብሬት 133ኛው የመውሊድ በዓል በድምቀት እየተከበረ ነው።

በበዓሉ የተገኙት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳይ ጠቅላይ ምክርቤት ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ሀጂ አብዱልከሪም ሼክ በድረዲን እንደገለጹት የአብሬት መውሊድ ከተጀመረ በርካታ አመታትን የተሻገረና ከመላው ሀገሪቱ የተውጣጡ የእምነቱ ተከታዮችና ከእምነቱ ውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በዘር፣ በጎሳ፣ በቀለምና በብሔር ሳይለያዩ በአንድነት የሚታደሙበት በዓል ነው።ኃይማኖታዊ በዓላት ከኢትዮጵያዊያን አልፎ የአፍሪካውያን እሴቶች፣ልዩልዩ ባህሎችና ቅርሶች ለማስተዋወቅ ያላቸው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ በየ ሀድራው የሚገኙ ቅርሶቹ ለትውልድ ለማስተላለፍ መስራት ይገባል ብለዋል፡፡

የአብሬት ሀድራ የአካባቢው ማህበረሰብ ልማት ተጠቃሚ ለማድረግ እያደረገ ያለው እንቀስቃሴ አበረታች ሲሆን ዘመኑን የዋጀ፣ ሁሉ አቀፍ አገልግሎት መስተት የሚችሉ ግንባታዎች ለማከናወን እየተሰራ መሆኑ አስረድተዋል፡፡

የጉራጌ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ መሰረት አመርጋ የአብሬት ሀድራ በዞኑ ከሚገኙ ሀይማኖታዊ ሰፍራዎች አንዱ ሲሆን በዓሉን ለመታደም ከሁሉም የሀገራችን ክፍል የእምነቱ ተከታዮች የሚታደሙበት በአል በመሆኑ የቱሪስት ፍሰቱ እንዲጨምር አድርጓል ብለዋል፡፡ይህን ዘመናትን የተሻገረው ታሪካዊ ሀድራ በዞኑ የቱሪዝም ዘርፍ መነቃቃት ጉልህ ሚና የሚጫወት ከመሆኑም ባሻገር የአብሮነት፣ የፍቅርና የመከባበር እሴቶች እንዲጎለብቱ ያለው ፋይዳ ከፍተኛ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡እንደ ወ/ሮ መሰረት ገለፃ ይህ ታሪካዊ ሀድራ በስነ ምግባር የታነፁ ወጣቶች በመቅረፅ ረገድ ሀላፊነቱ እየተወጣ ሲሆን በተጨማሪም የቀደምት እውቀትና ሥልጣኔ ታሪክ ያላቸው ኪታብ፣ቅዱስ ቁርአን በውስጡ ይገኛሉ፡፡የዞኑ ባህል ቱሪዝም ይህንን ታሪካዊ ስፍራ ከተለያዩ የሚዲያ አካላት ጋር በመቀናጀት የማስተዋወቅ ሚናው እየተወጣ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክርቤት ዋና ፀሀፊ ኡስታዝ ሳዲቅ ወጊቦ በበኩላቸው በክልሉ ከሚገኙ ሀድራዎች አንዱ የአብሬት መስጂድ ሲሆን ከሀይማኖታዊ ትምህርት በተጨማሪ ተከታዮቹ የአካባቢያቸው ሰላም በማስጠበቅ፣በልማት በመሳተፍ ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ መሆናቸው ገልፀዋል፡፡በመሆኑም በየሀድራዎቹ የሚካሄዱ መውሊዶች የእርስ በርስ ትስስር ከማጠናከርና መልካም ልምዶች ለመለዋወጥ እድል እንደሚፈጥሩ ተናግረዋል፡

፡የጉራጌ ዞን እስልምና ጉዳዮች ምክርቤት ሰብሳቢ ኡስታዝ አባስ ያሲን እንደተናገሩት የአብሬት ሀድራ የእምነቱ ተከታዮችን ሀይማኖታቸው ጠብቀው፣ በስነ ምግባር ታንፀው እንዲያድጉ፣ የአካባቢው ማህበረሰብ በልማት ተጠቃሚ ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ተናግረዋል፡፡ሀድራው በጎነት፣ መተባበርን፣ መረዳዳትን ጠንካራ የስራ ባህልን ያስተማረ ታሪካዊ ስፍራ ሲሆን ትውልዱ እነዚህ እሴቶችና በውስጡ የሚገኙ ልዩ ልዩ ቅርሶች ጠብቆ እንዲያቆይ ማድረግ ይጠበቅበታል ብለዋል፡፡የአብሬት ሀድራ ሼህ ኑረዲን ደሊል በበኩላቸው እንዳሁን ቴክኖሎጂ እንኳ በሌለበት ወቅት ምዕመኑ ማንም ሳይጠራው ወቅቱን አውቆ ከአራቱ የሀገሪቱ ማዕዘናት በመሰባሰብ የተቸገረ የሚረዳበት ለሀገር ሰላምና አንድነት ዱዓ የሚደረግበት በዓል እንደሆነ ተናረግዋል።አክለውም ህብረተሠቡም በዓሉን ሼሆች ባስቀመጡት ጥሩ ስነ ምግባር መሠረት እሴቱን ለትውልድ እንዲተላፍ መሠራት አለበት ብለዋል።

Image
photo