Skip to main content

የኢፌዲሪ ባህልና ስፖርት ሚንስቴር ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመተባበር በዕደ ጥበብ ሙያ ዘርፍ በሸክላ ስራዎች ዲዛይንና ቴክኖሎጂ የተግባር ስልጠና የማስጀመሪያ መርሃ ግብር በቡታጅራ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ መስጠት ተጀምሯል ።

የኢፌዲሪ ባህልና ስፖርት ሚንስቴር ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመተባበር በዕደ ጥበብ ሙያ ዘርፍ በሸክላ ስራዎች ዲዛይንና ቴክኖሎጂ የተግባር ስልጠና የማስጀመሪያ መርሃ ግብር በቡታጅራ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ መስጠት ተጀምሯል ።

በማስጀመሪያ መድረኩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ሀላፊ እና የባህል ዘርፍ ሀላፊ አቶ ደግነህ ቦጋለ የዕደ ጥበብ ሙያና የባህል ኢንደስትሪ ክልላችን እየተከተለች ካለችው የብልጽግና ዕቅድ አንጻር ለክልሉ ኢኮኖሚ ጉልህ አበርክቶ እንዳለው ገልፀዋል ።በዛሬው ዕለት የተጀመረው ስልጠና በዕደ ጥበብ ዘርፍ አምራችነት እሴት ሰንሰለት የተቀላቀሉ ባለሙያዎችን ለማፍራት ዓላማው ያደረገ በሸክላ ስራ ላይ የሚሰጥ የክህሎት ስልጠና መሆኑንም አቶ ደግነህ አስታውቀዋል ።ምክትል የቢሮ ኃላፊው በክልሉ የሚገኙ ስራ አጥ ሴቶች ፣ወጣቶችና አካል ጉዳተኞች መልምሎ በማሰልጠን በማህበር እንዲደራጁና ወደ ዘርፋ እንዲቀላቀሉ በማድረግ በሸክላ ስራ በዕሴት ሰንሰለት የተቀላቀሉ ባለሙያዎችን በማብቃት ዘርፋን በተደራጀ አግባብ በመምራት ተጨማሪ የቱሪስት መስህብ መፍጠርና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳውን ማሳደግ የስልጠናው ግብ መሆኑን አስገንዝበዋል ።

በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት በኢፌዴሪ ባህልና ስፖርት ሚንስቴር የዕደ ጥበብ ተቋማት አቅም ግንባታ ዴስክ ሀላፊ ወ/ሮ ታሪኳ ሀሰን የዕደ ጥበብ ሙያን ከቴክኖሎጂ ጋር በማስተሳሰር ጥራት ያለው ምርት ለማህበረሠቡ ተደራሽ ማድረግ እንደሚጠበቅ ገልፀዋል ።በተጨማሪ ለወጣቶች፣ ሴቶችና አካል ጉዳተኞች የሥራ ዕድል የሚፈጠርና ኢኮኖሚን የሚያነቃቃ መሆኑን ተናግረዋል ።በሙያው ዙሪያ ያሉ የግንዛቤ እጥረቶችን መቅረፍ እንደሚገባም ወ/ሮ ታርኳ አስታውቀዋል።በመድረኩ ላይ የቢሮ ምክት ሀላፊና ቱሪዝም ዘርፍ ሀላፊ አቶ ኑር ከድር፣ የምስራቅ ጉራጌ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ብሩክታዊት ጸጋዬን ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል ።

Image
photo