Skip to main content

በከምባታ ዞን ሀደሮ ከተማ አስተዳደር በግል ባለሀብት በአቶ ተሰማ ሾቢሶ ከ150 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተገነባው ኤልሻዳይ ሕንፃ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።

በከምባታ ዞን ሀደሮ ከተማ አስተዳደር በግል ባለሀብት በአቶ ተሰማ ሾቢሶ ከ150 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተገነባው ኤልሻዳይ ሕንፃ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።

በከምባታ ዞን ሀደሮ   ከተማ  አስተዳደር  በግል  ባለሀብት  በአቶ ተሰማ ሾቢሶ  ከ150 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተገነባው ኤልሻዳይ ሕንፃ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።
ሕንፃው  የሆቴል  ፣ የንግድና    የስብሰባ አዳራሽ አገልግሎት መስጣት የሚችልና ከ150 በላይ ጊዜያዊና ቋሚ የሥራ እድል መፍጠር የሚችል መሆኑም ተመልክቷል።በሀደሮ ከተማ  ተገኝተው   ሕንፃውን   መርቀው አገልግሎት    ያስጀመሩት  የከምባታ   ዞን  ዋና  አስተዳዳሪ የተከበሩ ዶክተር ዳዊት ለገሠ ሕንፃው ተገንብቶ ለአገልግሎት ዝግጁ መሆኑ የባለሀብቱንና የህብረተሰቡን ተሳትፎ በማጠናከር የከተሞችን ልማትና እድገት ለማረጋገጥ እየተደረገ ባለው ጥረት እሴት የሚጨምር መሆኑን አብራርተዋል።ኢንቨስትመንት ሲስፋፋሰ የሥ እድል  ይፈጠራል የአካባቢው  ልማትና እድገት ይረጋገጣል ያሉት ክቡር የዞኑ አስተዳዳሪው ለዚህም ሠላምና ፀጥታ ወሳች በመሆኑ ለሠላማችን በጋራ ዘብ በመቆም ለአካባቢያችን ልማት መረባረብ ይገባናልም ነው ያሉት።
በዞናችን ያሉ ልማት ወዳድ ባለሀብቶች  ከተሞቻችንን በማልማት ህዝባችንን ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት ሊሠሩ እንደሚገባ በመጥቀስ ሌሎች በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ ያሉ ባለሀብቶች በዞኑ ኢንቨስት በማድረግ  የድርሻቸውን በመወጣት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ አለባቸው ብለዋል። ለዚህም መንግስት የመሠረተ ልማት ችግር ለመቅረፍ በህዝቡ ዘንድ ያለው እምቅ አቅም በማስተባበር ከመቼውም ጊዜ በላይ በትኩረት እየሠራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
የእንኳን ዳህና መጣችሁ  ንግግር ያደረጉት የሀደሮ ከተማ ከንቲባ ክቡር አቶ አበራ ታፈሳ ሀደሮ ከተማ በፍጥነት በማደግ ላይ ያለች ከተማ በመሆኗ ዛሬ ላይ የተመረቀው ኤልሻዳይ ህንፃ ሌላ እሴት የሚጨምር ኢንቨስትመንት መሆኑን ተናግረዋል።
ከተማዋ የልማት  ወዳድ  ህዝቦችና እምቅ የተፈጥሮ ሀብት  ያላት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በርካታ የኢንቨስትመንት ሥራዎች እየተሠሩ በመሆናቸው በርካታ ብሔር ብሔረሰቦች በፍቅር ፣ በመቻቻልና በሠላም የሚኖሩባት ከተማ በመሆኑ እንደ ኤልሻዳይ ሕንፃ ባለቤት ሁሉ ኢንቨስት ለማድረግ መሬት የወሰዱ ባለሀብቶች በውላቸው መሠረት በማልማት ለከተማዋ እድገት የድርሻቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።
የኤልሻዳይ  ሕንፃ   ባለቤትና የሀደሮ    ከተማ ተወላጅ የሆኑት አቶ ተሰማ ሾቢሶ በከተማ አስተዳዳሩ በንግድ ሥራ ላይ ተሰማርተው ከነበሩበት ኑሮ ለማሻሻል በሚደረገው ጥረት ወደ ደቡብ አፍሪካ በማቅናት ጥረው ግረው ባፈሩት ሀብት ሕንፃውን መገንባት መቻላቸውን ተናግረዋል።በአራት  ዓመት  ጊዜ   ውስጥ  ተገንብቶ የተጠናቀቀው ይህ ህንፃ 158 ሚሊየን ብር ወጪ የተደረገ ሲሆን የሆቴልና የስብሰባ አዳራሽ የንግድ አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑንም ነው ያብራሩት።ባለሀብቱ  አያይዛውም ህንፃው  ሙሉ በሙሉ   ሥራ ሲጀምር ለ150 ሰው ጊዜያዊና ቋሚ የሥራ እድል መፍጠር የሚችል መሆኑን ጠቅሰው ህንፃው ተገንብቶ ለምረቃ እስክደርስ ከጎናቸው በመሆን የረዳቸውን ፋጣሪያቸውን፣ ባለቤታቸውንና መላው ቤተሰቦቻቸውን እንዲሁም የሀደሮን ህዝብና መንግስት አመስግነዋል።
በምረቃ መርሃግብሩ  የከምባታ ዞን  ብልጽግና  ፓርቲ  ጽህፈት   ቤት   ኃላፊ አቶ ዳዊት  ሀንዲኖን ጨምሮ  የከምባታ ዞን አስተባባሪ አካላትና ከፍተኛ የመንግስት ሥራ ኃላፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሐይማኖት አባቶች፣ የንግዱ ማህበረሰብ የሀደሮ ከተማ ነዋሪዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳትፈዋል።

 

Image
photo