የስልጤን ቋንቋ ለማሳደግና ለማልማት የተለያዩ ስራዎችን መስራት እንደሚገባ የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የተከበሩ አቶ ዘይኔ ቢልካ ገለፁ
የስልጤን ቋንቋ ለማሳደግና ለማልማት የተለያዩ ስራዎችን መስራት እንደሚገባ የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የተከበሩ አቶ ዘይኔ ቢልካ ገለፁ ::
ዋና አስተዳዳሪው እንዳሉት የስልጤ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ከስልጤ ልማት ማህበር በመተባበር ለባለድርሻ አካላት በስልጥኛ ቋንቋ እድገት ዙሪያ በተዘጋጀ ስልጠና ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል።የስልጤ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ከስልጤ ልማት ማህበር በጋራ በመሆን ለዞን መምሪያ ፎካል ፐርሰኖች ለወረዳና ለከተማ አስተዳደር የቋንቋ ባለሙያዎችና ሀላፊዎች የስልጥኛ ቋንቋን ለማሳደግ ና ለማልማት የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና በወራቤ ከተማ በስልጤ ባህል አዳራሽ ሰጥቷል ።ዋና አስተዳዳሪው የስልጥኛ ቋንቋን ለማሳደግና ለማልማት የተለየ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል ።ቋንቋውን የዞኑ የስራ ቋንቋ አድርጎ በመጠቀም የማህበረሰቡን ባህል ታሪክ ከማሳደግ በተጨማሪ የተያዙ የልማትና የመልካም አስተዳደር ዕቅዶችን ግብ እንዲመታ ትልቅ ምን እንዳለው ዋና አስተዳዳሪው አረጋግጠዋል።የስልጤ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ሀላፊየሆኑት ዶ/ር ይርዳው ናሲር እንደገለፀጹት የስልጤን ማህበረሰብ ባህሉ፣ ታሪኩንና የተለያዩ ሀገር በቀል እውቀቶችንና እሴቶችን ለቀጣይ ትውልድ ለማሰተላለፈ የስልጥኛን ቋንቋን ማጠናከር አለብን ብለዋል፡፡ስልጠናውን የሰጡት የቋንቋ ምሁርና ተመራማሪ አቶ ሁሴን መሀመድ/ሁሴን ቃሙስ/ እንዳሉት ቋንቋን ለማሳደግና ለማልማት የአንድ ማህበረሰብ ማንነቱን ባህል ከመጠበቅ ባሻግር የሀገራችን ባህል ና ታሪክ መጠበቅ አለበት ብለዋል።
