የሀላባ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ሀላፊ አቶ መሀመድ ከዲር ለ'ሴራ' በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
የሀላባ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ሀላፊ አቶ መሀመድ ከዲር ለ'ሴራ' በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
ታህሳስ 25/2017
የሀላባ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ሀላፊ አቶ መሀመድ ከዲር ለ'ሴራ' በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። ሀላፊው በመልዕክታቸው የሀላባ ሴራ በዓል በታህሳስ ወር 'መንገሳ' የሚከበር የሀላባ ህፃናት ከልጅነት ወደአዋቂነት የዕድሜ ሽግግር 'ሁሉቃ' ስነስርዓት የሚከወንበት ልዩ ትውፊታዊ በዓል ነው ብለዋል።ይህም የ'ሴራ' በዓላችን ከአያት ቅድመ-አያት ሲወራረስ የመጣው ቱባ ባህል መሠረቱን ጠብቆ ለቀጣዩ ትውልድ እንዲሸጋገር ትልቅ ሚና ያለው ባህላዊ በዓል እንደሆነም ሀላፊው አብራርተዋል።ሀላፊው አክለውም በቀጣይም ይህንን ድንቅ ባህላችንን አስጠብቀን ለቀጣዩ ትውልድ እንዲሸጋገርና በዩኔስኮ ለማስመዝገብ ሁሉም የራሱን ድርሻ እንዲያበረክት ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል። በመጨረሻም የዘንድሮ የሀላባ ሴራ በዓል ከቀበሌ እስከወረዳ ማዕከል በድምቀት እንደሚከበር የገለፁት የመምሪያው ሀላፊ ይህ የበዓሉ አከባበር በስኬት እንዲጠናቀቅ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ባህሉን በማስተዋወቅና በማክበር ለባህሉ መጠበቅ የራሱን አሻራ እንዲያሳርፍ ጥሪ አቅርበዋል።
