Skip to main content

የቋንቋ ፣ ሀገር በቀል ዕውቀት እና ባህል ማዕከል በወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ተቋቁሟል ።

የቋንቋ ፣ ሀገር በቀል ዕውቀት እና ባህል ማዕከል በወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ተቋቁሟል ።በማቋቋሚያው ፕሮግራሙ ላይ የሀገር በቀል ዕውቀት ሀገረሰባዊ ትውፍት፣ የየም ባህላዊ መድኃኒት ሳሞ ኤታ፣ የቀቤና ባህላዊ ዳኝነት ኦገት፣ የጉራጌ ሀገር በቀል እውቀቶች እና እሴቶች፣ ጀፎረ፣ የጉራግኛ ቋንቋ ነባራዊ ሁኔታና ተቋማት ላይ ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት ተደርጓል ።

በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል መንገሻ ቢሮው ከዩኒቨርስቲው ጋር በቋንቋ፣ በሀገር በቀል ዕውቀት ጥናትና ምርምር፣ በሀገረሰባዊ ጉዳዮች እና የቱሪዝም መዳረሻ ቦታዎች ልማትና ተያያዥ ስራዎች በቅንጅት እንደሚሰራ ገልጸዋል ።በፕሮግራሙ ላይ የዩኒቨርስቲው ፕረዝዳንት ዶክተር ፋርስ ደሊልን ጨምሮ ተመራማሪዎች ከዞንና ልዩ ወረዳ የባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊዎች ተገኝተዋል ።

Image
photo