Skip to main content

በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ክብር ለጥበበኞች በሚል መሪ ቃል የባህል እና ጥበባት ባለሙያዎች የእውቅና መረሀ ግብር እና የባህል፣የኪነ ጥበብ እና የስነ ጥበብ ክልላዊ የንቅናቄ መድረክ ተካሄደ።

በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ክብር ለጥበበኞች በሚል መሪ ቃል የባህል እና ጥበባት ባለሙያዎች የእውቅና መረሀ ግብር እና የባህል፣የኪነ ጥበብ እና የስነ ጥበብ ክልላዊ የንቅናቄ መድረክ ተካሄደ።

ወልቂጤ፤ ታህሳስ 15/2017፡-

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ለኪነ ጥበብ ባለሙያዎች እውቅና የመስጠት መርሃ ግብር በወልቂጤ ከተማ ተካሂዷል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አዘጋጅነት "ክብር ለጥበብ" በሚል መሪ ሀሳብ በተካሄደው መርሃ ግብር ላይ በዘርፉ የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች እውቅና ተሰጥቷል።የክልሉ የባህል ቱሪዝም ሀላፊ አቶ ሳሙኤል መንገሻ በክልሉ የሚገኙ የብሔር ብሔረሰቦችን ባህል፣ ታሪክና ቅርስ የማልማት እና የማስተዋወቅ ብሎም የባህል እሴቶቻችን በማበልፀግ ክልሉ የታደላቸው ባህላዊ ፀጋዎች ጎልተው እንዲታዩ በማስቻል የክልሉ መልካም እሴት የመገንባት እና ባህላችን እንዲታወቅ በማድረግ የራሱን ድርሻ እየተወጣ ይገኛል ብለዋል።

በተጨማሪም የእውቅና መድረኩ በአንድ በኩል በስነ ጥበብ፣ በኪነ-ጥበብና በዘርፉ የተሰማሩ ባለድርሻ አካላት እና የጥበብ ሰዎች እስከአሁን ላበረከቱት አስተዋጽኦ እውቅና የሚሰጥበት መሆኑን ጠቁመው በቀጣይ የክልሉን የስነ ጥበብ ስራዎች ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ የንቅናቄ ስራዎችን በመስራት ሀገራዊና ክልላዊ ተልኮችን ከመወጣት ጎን ለጎን በቀጣይ አመት በከፍተኛ ድምቀት ለምናከብረው 20ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን እራሳችንን ከአሁኑኑ በማዘጋጀት መሠረት የምንጥልበት ነው ብለዋል።የኪነጥበብ ባለሙያዎቹ የክልሉ ባህል ተጠብቆ እንዲቆይ በሥራቸው በማስተዋወቅ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ያበረከቱና እያበረከቱ ያሉ ባለሙያዎች መሆናቸውም ተመላክቷል።

ከእውቅና መርሀ ግብር በተጨማሪ ክልላዊ የባህልና የኪነ ጥበብ ንቅናቄ ማስጀመሪያ መድረክም እንደሚካሄድ ታውቋልበመርሃ ግብሩ የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፋጤ ስርሞሎ፣የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል መንገሻ እንዲሁም የክልልና የዞን የባህልና ቱሪዝም አመራሮችና የተለያዩ አካላት ተገኝተዋል።

Image
photo