Skip to main content

Message

 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ መልዕክት

   አቶ ሳሙኤል መንገሻ

በዓለማችን በምጣኔ ሀብታዊ፣ ማህበራዊና አካባቢያዊ ጠቀሜታዎችን በማሳደግና ዘላቂ ልማት ለማፋጠን ቁልፍ ድርሻ ካላቸው ሴክተሮች መካከል አንዱ የባህልና ቱሪዝም ሴክተር እንደሆነ ጥናቶች ያረጋግጣሉ፡፡ አገራችን ኢትዮጵያ ባለፉት የለውጥና የሪፎርም ዓመታት ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ እድገት በብዙ ፈተናዎችም ውስጥ ሆና ማስመዝገብ የቻለች ሲሆን የአገልግሎት ሴክተሮች ለዚህ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል፡፡ ከአገልግሎት ሴክተሮች የባህልና ቱሪዝም ሴክተር ቁልፍ ድርሻ ይይዛል፡፡ ሴክተሩ ከኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ባሻገር ለብሔረሰቦች ባህል፣ ቋንቋ፣ ታሪክና ቅርስ ጥበቃ ና ልማት የሚኖረው ድርሻም ጉልህ ነው፡፡በባህልና ቱሪዝም ሴክተር ያሉ ዘርፎች በተናጠልም ሆነ በጋራ በመሆን በባለፉት ዓመታት በርካታ የልማት ተግባራት በተለያዩ መስኮች እንደ አገርም እንደ ክልልም አመርቂ ውጤቶች ተመዝግበዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ሴክተሩ መንግስት የተሰጠዉ ትኩረት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በአገርም ሆነ በክልል ደረጃ እየተከናወነ ባለው በአገራዊ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም ዘርፉ የማሻሻያው ዋነኛ ምሰሶ ሆኖ መወሰዱ በቂ ማሳያ Read More