የየም ብሔረሰብ የአዲስ ዘመን መለወጫ “ሄቦ” በዓል በሳጃ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ነው
cerboct
Mon, 10/05/2026 - 09:24
የየም ብሔረሰብ የአዲስ ዘመን መለወጫ “ሄቦ” በዓል በሳጃ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ነው
ሳጃ፣ መስከረም 21/2019 ዓ.ም
የ2019 ዓ.ም የየም ብሔረሰብ የአዲስ ዘመን መለወጫ “ሄቦ” በዓል በተለያዩ የባህል ዝግጅቶች በሳጃ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።
በበዓሉ ላይ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ አመራሮች፣ የባህል አምባሳደሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የየም ብሔረሰብ ተወላጆች እንዲሁም የተጋበዙ እንግዶች ተገኝተዋል።
“ሄቦ” በዓል የየም ብሔረሰብን ባህል፣ ቋንቋ፣ ታሪክና ማንነት የሚያንጸባርቅ ሲሆን፣ በዓሉ የትውልድ ቅርስን ለማስተላለፍና የባህል እሴቶችን ለማስጠበቅ ያለው ሚና ከፍተኛ ነው።
በዓሉ በተለያዩ የባህል ዝግጅቶችና ስነ-ሥርዓቶች በሳጃ ከተማ ተከበረ።
Image
Saja, Ethiopia 

