Skip to main content

የጠምባሮ ብሔረሰብ የባህል፣ የቋንቋ እና የመሳለ (መርሾ) ሲምፖዚየም ተካሄደ

የጠምባሮ ብሔረሰብ የባህል፣ የቋንቋ እና የመሳለ (መርሾ) ሲምፖዚየም ተካሄደ

የጠምባሮ ብሔረሰብ የባህል፣ የቋንቋ እና የመሳለ (መርሾ) ሲምፖዚየም "ባህላችንን ከትውልድ ወደ ትውልድ፤ አንድነታችንን ከዛሬ ወደ ነገ" በሚል መሪ ቃል ተካሂዷል።

የጠምባሮ ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ሀብታሙ በላይነህ በወቅቱ እንደገለጹት፤ መሳላ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የመጣ የፍቅር፣ የእርቅ፣ የአብሮነትና የመቻቻል ተምሳሌት ነው። መሳላ (መርሾ) የጠምባሮ ብሔረሰብ የዘመን ሽግግር ብቻ ሳይሆን የማህበራዊ አንድነት፣ የምስጋና፣ የፍቅር፣ የሰላምና የዕርቅ በዓል መሆኑን ኢንጂነር ሀብታሙ አስገንዝበዋል።

አክለውም የጠምባሮ ልዩ ወረዳ የማንሰራራት ዘመንን በሁሉም መስኮች በማጠናከር ጊዜን፣ እውቀትንና ጉልበትን በመጠቀም አካባቢውን ለማልማት ተደምሮ መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።

ይህ ታላቅ ሲምፖዚየም ዋና ዓላማው የጠምባሮ ብሔረሰብ የበለፀጉ ባህላዊ እሴቶች፣ የቋንቋ ሀብቶች እና ታሪካዊ ቅርሶች መጠበቅ፣ ማልማት እንዲሁም ለተከታይ ትውልድ ማስተላለፍ ሲሆን፤ በተጨማሪም የህዝቦችን አብሮነትና ወንድማማችነት በማጠናከር ዘላቂ አንድነትን መገንባት እንደሆነ ተገልጿል።

በዚሁ የጠምባሮ ብሔረሰብ የባህል፣ የቋንቋ እና የመሳለ (መርሾ) ሲምፖዚየም ላይ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የባህልና ታሪክ ተመራማሪዎች፣ የወጣቶችና የሴቶች ተወካዮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

Image
መርሾ ፎቶ