Skip to main content

የሀዲያ ብሔር የዘመን መለወጫ "ያሆዴ" በዓል በሆሳዕና ከተማ በከፍተኛ ህዝባዊ ትዕይንት ተከበረ

የሀዲያ ብሔር የዘመን መለወጫ "ያሆዴ" በዓል በሆሳዕና ከተማ በከፍተኛ ህዝባዊ ትዕይንት ተከበረ

​የሀዲያ ብሔር ወደ አዲስ ዓመት መሸጋገርን የሚያብሰረው የ2019 ዓ.ም "ያሆዴ" በዓል በሆሳዕና ከተማ "ሀዲይ ነፈራ" የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በተገኙበት በልዩ ልዩ ባህላዊ ዝግጅቶችና በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል።

​"ያሆዴ" በየዓመቱ በህብረተሰቡ ዘንድ እጅግ ተናፋቂና ትልቅ ቦታ የሚሰጠው የዘመን መለወጫ በዓል ሲሆን፣ የብሔሩ ተወላጆች ከተለያዩ አካባቢዎች ወደ ትውልድ ስፍራቸው በማቅናት በዓሉን አይረሴ በሆነ መንገድ ያከብሩበታል።

በዓሉ ከበዓልነቱ ባሻገር ህዝቡ እርስ በእርስ የሚጠያየቅበት፣ ፍቅርና አንድነቱን የሚያጠናክርበት እንዲሁም ማህበራዊ መስተጋብሩን የሚያድስበት ታላቅ ባህላዊና ታሪካዊ እሴት ሆኖ አልፏል።

​በሆሳዕና ከተማ በደማቅ ሁኔታ በተካሄደው በዚህ የዘመን መለወጫ በዓል ላይ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)፣ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የሀዲያ ዞን አመራሮች፣ የብሔረሰቡ ተወላጆች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው በርካታ እንግዶች ተገኝተው የበዓሉ ታዳሚ ሆነዋል።

Image
ያሆዴ ፎቶ